ዐውደ ምሕረት
3.69K subscribers
930 photos
24 videos
271 files
193 links
"ቤተ ክርስቲያን ባሕረ ጥበባት
አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት"
Download Telegram
#ቅድስት_ቤተ_ክርስቲያን በዐድዋ
_____________________________
ጦርነት አስከፊ ነው የጦርነት ደግ የለውም ሆኖም በዓለማችን ላይ ቅዱስ ጦርነት ፤የመስቀል ጦርነት ተብለው የተጠሩ የጦርነት ዐይነቶች ነበሩ።
በአለፉት ሺህ ዓመታት በጥንታዊ ሀገራችን ኢትዮጲያ ከተፈጸሙ ታሪካዊ ነገሮች አንዱ በሊቀ ሰማዕታት ቅዱስ ጊዮርጊ ተራዳኢነት ጀግኖች አባቶቻችን በፋሽሽት ኢጣልያ ላይ የካቲት ፳ ፫ ቀን ፲ ፰ ፻ ፹ ፰ ዓ.ም የተቀዳጁት የዐድዋ ድል ነው ይህ ድል የመላው አፍሪካ ጥቁር ሕዝቦች ድልና የነፃነት ብርሃን በመባል ይታወቃል።
#ጀግኖች_አባቶቻችንን በአድዋው ጦርነት የረዳቸው የሰማዕታት አለቃ ቅዱስ ጊዮርጊስ ሕገ ወንጌልን በማስተማርና አምልኮተ ጣኦትን በመንቀፍ ስለ ፈጣሪያችን ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ የባሕሪ አምላክነት እየመሠከረ ከግፈኖች አረማውያን ብዙ መከራ ተቀብሎ በአደባባይ መራራ ሞትን ፊት ለፊት በመጋፈጥ ሰባት ዓመታትን ከተጋደለ በኃላ ሚያዝያ ፳ ፫ ቀን የሰማዕትነትን አክሊል ተቀብሏል።
ሰማዕቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ ሚያዝያ ፳ ፫ ቀን ሰማዕትነትን ጊዮርጊስ በተቀበለበት ዕለት ከፈጣሪው ከኢየሱስ ክርስቶስ ልዮ ልዮ የምሕረት ቃል ኪዳን ተቀብሏል።ከተቀበለው ቃል ኪዳን መካከል በስምህ ተማጽኖ መታሰቢያህን የሚደርገውን እኔ በመከራው ቀን እረዳዋለሁ የሚል ይገኝበታል።
#ሊቀ_ሰማዕታት ቅዱስ ጊዮርጊስ የሰማዕትነትን አክሊለ ክብር ከተቀበለ በኃላ በአካለ ነፍስ ሆኖ ወደ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ተማኅጽኖ አቀረበ ይኸውም " ምስለ ፍልሠትኪ ደምርኒ እሙ" የፈጣሪየ የኢየሱስ ክርስቶስ እናት እመቤቴ ድንግል ማርያም ሆይ ሰማዕትነትን ከተቀበልኩባት ከፋርስ ምድር የአጽሜ ፍልሠት ቀን ከአንቺ የፍልሰትሽ በዓል ቀን ጋር ነሐሴ ፲ ፮ ቀን ተባብሮ እንዲከበርልኝ ፈቃድሽ ይሆን በማለት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ለመነ።
እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምም እንዳልከው ይሆንልሃል ስለሆነም አንተም ከእግዚአብሔር አስራት ሁና የተሰጠችኝን ኢትዮጵያን ገበዝ (ጠባቂዋ) ሆነህ ጠብቃት አለችሁ ሰማዕቱ ቅዱስ ጊዮርጊስም አንቺ እንዳልሽ ይሁን እመቤቴ አለ ስለዚህም ቅዱስ ጊዮርጊስ የኢትዮጵያ ገበዝ ወይም ጠባቂ ሁኖ ከእግዚአብሔር ተሹሟል።
#የቅዱስ_ጊዮርጊስ ፍልሰተ አጽም ከፋርስ ወደ ልዳ በነሐሴ ፲ ፮ ቀን ማለትም የእመቤታችን ቅዱስ ሥጋ ከጌቴ ሰማኒ ወደ መንግሥት ሰማያት በፈለሰበት (በዕርገቷ) ዕለት ተፈጽሞለታል። ይህን የቅዱስ ጊዮርጊስና የእመቤታችን ስምምነት በሚገባ የምታውቀው ሀገረ እግዚአብሔር ኢትዮጵያ ሰማዕቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከወራሪ ጠላት እና ከክፉ ነገር ሁሉ እንደሚጠብቃት ዘወትር ታምናለች።
በመሆኑም በጥንት ኢትዮጵያ የሚታወቅና ይደረግ የተበረ አንድ ነገር አለ ከቅድመ አያቶቻችን ጀምሮ የሚደረገውም ወጣት ኢትዮጵያዊን የሰማዕቱን የቅዱስ ጊዮርጊስ ማኅበርተኞች በመሆን በአንድነት ይሰበሰባሉ፤ በቅዱስ ጊዮርጊስ ስም በየጊዜው እየተሰበሰቡም ሰለ ፈረስ ግልቢያ ፣ስለ ጦር ጉግስ፣ የጦር ስልትና ወታደራዊ የጀግንነት ትምህርት እየተማሩ እንዲያድጉ ያደርጉ ነበር።
#አባቶቻችን በዚህ ዕድገታቸው የሰማዕቱ የቅዱስ ጊዮርጊስና የለገራቸው ኢትዮጵያ ፍቅር አብሮ ያድጋል የጀግንነት ወኔአቸውና ሥነ ምግባራቸውም የላቀ ይሆናል እንዲህ ሁነው የሚድጉት ኢትዮጵያዊያን በማናቸውም ነገር በቀላሉ የማይበገሩ ስለሆኑና የሰማዕቱን የቅዱስ ጊዮርጊስ ረድኤት ስለማይለያቸው በየትኛውም የጦርነት ታሪክ የተሸነፉበት ጊዜ የለም።
እንደሚታወቀው በኢትዮጵያ ታሪክ አፄ አምደ ጽዮን የጦር ሰው ነበሩ።በቅዱስ ጊዮርጊስ ላይ ያላቸው እምነትና ተማጽኖ በእጅጉ የላቀ እንደነበርም ይነገርላቸዋል። በኢትዮጵያ በቅዱስ ጊዮርጊስ ስም ቤተ ክርስቲያን መሥራት የተስፋፋውም በእርሳቸው ዘመን ነው።
#በኢትዮጵያ የሥልጣኔ ታሪክ ዘመናዊ አስተዳደር እንዲስፋፋ ከፍተኛ ጥረት ያደረጉት ዳግማዊ አፄ ምኒልክ እንደ ቀድሞዎ አባቶቻችን ከኢትዮጵያ ገበዝ(ጠባቂ) ከሰማዕት ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር የነበራቸው ፍቅር እጅግ የላቀ ነበር ። ዳግማዊ አፄ ምኒልክ የነገሱበት ዘመን በጊዜው የነበሩ የኢጣልያ ባለ ሥልጣኖች ቃላቸውን እየለወጡና እያታለሉ ሀገራችን ኢትዮጵያ በቀኝ ግዛት ለመያዝ ቆርጠው የተነሱበት ዘመን ነበር።
የኢጣልያን ጦር መረብን ተሻግሮ ወደ ትግራይ እየገሰገሰ መምጣቱ ዳግማዊ አፄ ምኒልክ በሰሙ ጊዜ በ ፲ ፰ ፻ ፹ ፰ ዓ.ም የክተት አዋጅ አድርገው በጥቅምት ወር ወደ ትግራይ ሄዱ ጣሊያንን ለመፋለም ወደ ትግራይ ሲሄዱ ሁል ጊዜ ኢትዮጵያን በመርዳት የሚታወቀውን የሰማዕቱን የቅዱስ ጊዮርጊስንእና የእመቤታችንን የቅድስት ድንግል ማርያምን ታቦት ይዘው ነበር የሄዱት ወቅቱም የዐቢይ ጾም መጀመሪ ስለነበር አብሯቸው የዘመተው አብዛኛው አርሶ አደር ገበሬ ጾሙን ሳይታ እየጾመ ነበር የተከተላቸው። እርሳቸውም ቢሆኑ ምንም እንኳ ዕለቱ እሁድ ቢሆንም ቅዳሴ ገብተው እስከ ረፋዱ ሦስት ሰዓት አስቀድሰው ነው ወደ ጦርነቱ የገቡት ።

..............ቀጣዮን የመጨረሻ ክፍል ይመልከቱ........
#ዐውደ_ምሕረት የእናንተ
👇👇👇👇👇👇👇👇
https://www.facebook.com/112544300256976/posts/277932900384781/?app=fbl