ዐውደ ምሕረት
3.66K subscribers
932 photos
24 videos
271 files
195 links
"ቤተ ክርስቲያን ባሕረ ጥበባት
አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት"
Download Telegram
#የእግዚአብሔር_ሰው_ሆይ_በሚቻልህ እርዳኝ


እግዚአብሔር ከመረጣቸውና ከ አከበራቸው ቅዱሳን አባቶች አንዱ የሆኑት ጻድቁ አቡነ ተክለሃይማኖት አንዱ ናቸው ።
እኚ ቅዱስ አባት በኖሩበት ዘመን ሁሉ የሰው ልጅ ጠላት የሆነውን ዲያቢሎስ ከምድር አጥፍተዋል ከእግዚአብሔር በተሰጣቸው ጸጋ በአጋንንት ላይ ፅኑ መከራን አደረገባቸው። መሄጃ አጥተናል እስኪሉ ድረስ አባታችን ቅዱስ ተክለሃይማኖት አጋንንትን ላይ በረታባቸው ይህም ድንቅ አይደለ ክብር ይግባውና ጌታችን በወንጌሉ እንዲህ ብሉ ለቅዱሳኑ እንደተናገረ ማር 16÷ 17_ 18 " ያመኑት እነዚህ ምልክቶች ይከተሉአቸዋል በስሜ አጋንንት ያወጣሉ………… እጆቻቸውን በድውዮች ላይ ይጭናሉ እነርሱም ይድናሉ" እንዳለ ጻድቁ አባታችንም በአካለ ሥጋ እያለ ያደረገውን ድንቅ ነገር እንናገራ። ክቡር አባታችን መላ ኢትዮጵያን ሲያስተምሩ በአንዲት ቀን ዞረሬ ከምትባል ሀገር ደረሰ በዛም ከቀድሞ ጀምሮ ሴሰኛ የነበረች አንዲት ሴት አየ። እንዲህም አላት አንቺ ሴት እስከ መቼ እንደዚህ ባለ ጒስቁልና ትኖሪያለሽ ይህ መሰሰኑ አይበቃሽምን አላት ። እርሶም መልሳ እንዲ አለች ቅዱስ አባቴ ሆይ ይህ የዝሙት ነገር ለማቆም አልችልም በልቤ ውስጥ እንደ እሳት ይነዳልና ያለ ፍቃዴም ያሰራኛል አባቴ #የእግዚአብሔር ሰው ሆይ በሚቻልህ እርዳኝ አለቸው ። አባታችም ከእግዚአብሔር በተሰጠው ሐዋርያዊ ስልጣን በውስጧ የደረውንን እና ያለ ፍቃዷ እንድትሰስን ያደረገውን ጋኔን በመስቀል አማትቦ አስወጣው ። ያቺም ሴት ባለ ዘመኑ ሁሉ እግዚአብሔርን በመፍራትና በማመስገን ኖርች የአባታችን የቅዱስ ተክለ ሃይማኖት በረከት ረድኤት ከመከራ ሥጋ ከመከራ ነፍስ ይሰውረም አሜን ። ይህቺ ሴት ምንኛ ታላቅ እምነት አላት በሚቻለው ሁሉ የሚረዳ ቅዱስ ተክለሃይማኖትን ረዳትነት አምና ለምናለች እና የለመኑትን መስጠት ልማዱ የሆነ ቅዱስ ተክለ ሃይማኖትም የምትሻውን አደረገላት ።
ዛሬም እኛ ልጆቹ አባታችንን በሚቻልህ ሁሉ እርዳን ብንለው እሱ ሁሉን የሚችል ቅዱስ ነውና ሁሉ ያደርጋል ።
እንዴት ቢባል ክብር ይግባውና የሚሳነው የሌለው ጌታችን በወንጌል እንደተናገረ ዮሐ 14÷12 "በእኔ የሚያምን እኔ የማደርገው ሥራ እርሱ ደግሞ ያደርጋል ከዚህም የበለጠ ያደርጋል ብሏልና" ስለዚህ ዛሬም ለልጆቹ በአካለ ነፍስ ድንቅ የሚደርገውን አባት ተክለሃይማኖት ልንጣበቅ ይገባል ። እርሱ ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት በክንፉ ጋርዶ አስፈሪ ከተባለ ነገር ይጠብቀን ዘንድ የእርሱ ቅዱስ ፍቃድ ይሆን እኛም ልጆቹን በሚቻለው ሁሉ ይርዳን… … አሜን የአባታችን ረድኤት በረከት ምልጃ ከሁላችን ጋር ይሁን አሜን


ወስብሐት ለእግዚአብሔር

አዘጋጅ ።#እንግዳ ወርቅ ብርሃኑ ኃ/ሚካኤል

23/ 2012 ዓ.ም