ዐውደ ምሕረት
3.68K subscribers
930 photos
24 videos
271 files
193 links
"ቤተ ክርስቲያን ባሕረ ጥበባት
አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት"
Download Telegram
Audio
#መዝሙር
#ለንስሐ_ሞት_አብቃኝ

በዘማሪት #ሰብለ_ስፍር

ለንስሓ ሞት አብቃኝ /2/ 
በሂሶጵ እርጨኝ እጠበኝ 
እንደ በረዶ አንጻኝ /2/ 

አመፃዬ በዛ ኃጢአትን ጨመርኩኝ 
ልቤ ደነደነ ክፋትን ፈጸምኩኝ 
እንደ ፈርዖን ልቤ እንዳይጸናብኝ 
አድነኝ እንደ ኖኅ አምላክ ራራልኝ 
አድነኝ /3/ ስለ ድንግል ብለህ አድነኝ 
አድነኝ /2/ ስለ ጻድቃን ብለህ አድነኝ 

ኃጢአቴም በረታ ሰለጠነብኝ 
ከቃልህ አስወጣኝ ሕግህን ጣስኩኝ 
እንደ ነነዌ ሕዝብ ንስሓን ስጠኝ 
ምሕረትህን ልከህ ልቤን ስበርልኝ 
አድነኝ /3/ እንደ ቸርነትህ አድነኝ 
አድነኝ /2/ እንደ ምሕረትህ አድነኝ 

ያደፈዉ ገላዬን አንተ አጥራልኝ 
ከሰዶም ገሞራ እንዳይብስብኝ 
መንገድና ሕይወት አንተ ነህ ምራኝ 
የቅዱስ ጴጥሮስን ንስሓ ስጠኝ 
አድነኝ /3/ እንደ ቸርነትህ አድነኝ 
አድነኝ /3/ ስለ እናትህ ብለህ አድነኝ 
አድነኝ /2/ ስለ ጻድቃን ብለህ አድነኝ

                    
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit