"እነሆ፥ መንገድህ በፊቴ ጠማማ ነውና እቋቋምህ ዘንድ ወጥቼአለሁ፤ "
ኦ. ዘኍ22÷32
ይህን ኃይለ ቃል የተናገረው ሊቀ መላእኩ ቅዱስ ሚካኤል ነው የተናገረውም ለተራጋሚው በልዓም ስለተባለ ሰው ነው:: ቃሉን ጽፎ ያስቀመጠልን ሊቀ ነብያት ቅዱስ ሙሴ ነው::
በልዓም አብተ መርገምና ያለው የረገመው በቶሎ የሚደርስለት ሰው ነበር :: በዚህም ፀጋው ተጠቅሞ እስራኤልን ይረግም ዘንድ እጅ መንሻ ገንዘብን እንዲሰጡት ባላቅ ሰዎች ላከበት "፤ የሞዓብ ሽማግሌዎችና የምድያም ሽማግሌዎችም የምዋርቱን ዋጋ በእጃቸው ይዘው ሄዱ፤ ወደ በለዓምም መጡ፥ የባላቅንም ቃል ነገሩት። " ኦሪ.ዘኍ 22÷ 7 በልዓምም የተሰጠውን አብተ መርገም በገንዘብ ቀይሮ ሕዝበ እግዚአብሔርን እስራኤልን ለመርገም በአህያው ላይ ተቀምጦ ሽማግሌዎቹንም ከዋላው አስከትሎ ጉዞ ጀመረ ::ጥቂት እንደሄደ ግን አህያው አንድ ባታ ላይ ቆማ አልንቀሳቀስም አለችሁ:: የእግዚአብሔር መላእክ የተመዘዘ ሰይፍ ይዞ ከፊቷ ቆሞ አይታዋለችና:: በልዓም ግን አህያይቱን አብዝቶ ደበደባት አህያይቱም ወደፊት ላለመሄድ ወደጉን ወደ እርሻው ተጠጋች
"፤ አህያይቱም የእግዚአብሔርን መልአክ አይታ ወደ ቅጥሩ ተጠጋች፥ የበለዓምንም እግር ከቅጥሩ ጋር አጣበቀች፤ እርሱም ደግሞ መታት። " ኦሪ.ዘኍ 22÷25
እግዚአብሔር አምላክ የሚረግሙህን እረግማለው የሚባእኩህንም እባርካለው ብሎ ቃል የገባላቸው የነ አብርሃም የነ ይስሐቅ የነ ያዕቆብ ዘር ናቸውና ሕዝበ እስራኤል እንዲረገሙ አልፈቀደም::ዘፍ 12÷3
የበላዓም ዓይኖች አሁንም አልተከፈቱም ልቦናውም ከአህያይቱ ልብ አልተሻለም አሁንም አብዝቶ ደበደባት ይህን ጊዜ በሰው አንደበት እንዲ ብላ ተናገረችው ሦስት ጊዜ የመታኸኝ ምን አድርጌብህ ነው? አለችው። "፤ በለዓምም አህያይቱን። ስላላገጥሽብኝ ነው፤ በእጄስ ሰይፍ ቢኖር አሁን በገደልሁሽ ነበር አላት። "፤ አህያይቱም በለዓምን። ከብዙ ዘመን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ የምትቀመጥብኝ አህያህ አይደለሁምን? በውኑ እንዲህ አደርግ ዘንድ ልማዴ ነበረን? አለችው። እርሱም። እንዲህ አላደረግሽብኝም አላት። እግዚአብሔርም የበለዓምን ዓይኖች ከፈተ፤ የእግዚአብሔርን መልአክ በመንገድ ላይ ቆሞ የተመዘዘም ሰይፍ በእጁ ይዞ አየ፤ ሰገደም፥ በግምባሩም ወደቀ።
የእግዚአብሔርም መልአክ። አህያህን ሦስት ጊዜ ለምን መታህ? እነሆ፥ መንገድህ በፊቴ ጠማማ ነውና እቋቋምህ ዘንድ ወጥቼአለሁ፤ አህያህ አይታኝ ከፊቴ ፈቀቅ ባትል ኖሮ በገደልኩ ነበር አለው ደግሞም በለዓምን ከሰዎቹ ጋር ሂድ፥ ነገር ግን የምናገርህን ቃል ብቻ ትናገራለህ አለው። በለዓምም ከባላቅ አለቆች ጋር ሄደ መልአኩ እየነገረው እስራኤልን ሊረግም ሄዶ መርቆ ተመለሰ::
የእግዚአብሔር ሥራ ይገርማል ። የበልዓም አህያ የመላእኩን ክብር በማወቋና በመገንዘቧ የበላህምን ሕይወት ታድጋለች ዛሬ የቅዱሳን መላእክትን ክብር የማያውቁ የጸጋ ስግደት የማይሰግዱ አማላጅነታቸውን የማይቀበሉ ከአህያ ያነሱ ሰዎች በዝተዋል እግዚአብሔር አምላክ እንደ በልዓም ዓይነ ልቦናቸውን ከፍቶ ክብረ መላእክትን አውቀው ቅዱሳንን መርገም ትተው አንገታቸውን ደፍተው እንዲሰግዱ ያድርጋቸው ... .....ሌላ ምን እንላለን ከጌታችን የተማርነው ይህን ነውና
"፤ የሚረግሙአችሁንም መርቁ፥ ስለሚበድሉአችሁም ጸልዩ። "
(የሉቃስ ወንጌል 6: 28)
....ይቆየን......
የሊቀ መላእኩ የቅዱስ ሚካኤል ረድኤትና ምልጃው አይለየን ለዘለዓለሙ 👉 "❤️ አሜን"
በወንድማችን #ተርቢኖስ_ሰብስቤ
👉 @AwediMeherit

ዛቲ ዕለት ቅድስት ይዕቲ
(ይህቺ ቀን የተቀደሰች ናት)
*****************************
ቅዱስ ያሬድ ጾመ ድጓ
ቅድስት ማለት የተለየች የጸናች ክብርት ማለት ነው:: ቤተ ክርስቲያንም በዚህ በዐብይ ጾም ሁለተኛውን ሳምንት ቅድስ ብላ በመሰየም የሰንበትን ቅድስና ታስባለች ::
:ሰንበትን ቅድስት ያሰኛት ምንድነው???
ፈጣሪ ዓለማት ልዑል እግዚአብሔር በሰድስቱ ዕለታት ፍጥረታትን ከፈጠረ በኃላ በሰባተኛው ዕለት ከሰራው ሥራ ሁሉ አረፈ "ለሙሴም የሰንበትን ቀን ትቀድሳት ዘንድ አሰብ "የምትለውን ትዕዛዝ ሰጠ ስለዚህ ሰንበትን ቅድስት ያሰኛት ከስራ ሁሉ የሚታረፍባት ሕመምተኛ የሚጠየቅባት ወደ ቤተ እግዚአብሔር የሚገሰገስባት ቀን በመሆኗ ነው ::
በግብራቸው የተነሳ ዕረፍት እየተባሉ የሚጠሩ
*********************************
አካላት
*
1) ♥ እራሷ (ሰንበት )ዕለት እሁድ :- ዕረፍት ተብላ ትጠራለች: ዕለተ እሁድ በሌላ ስሟ ሰንበተ ክርስቲያንም ተብላ ትጠራለች :: አንዳንድ ጊዜ ሰንበት እሁድ ከሆነች ቅዳሜ ታድያ ምንድነች??? ተብሎ ሊጠየቅ ይችላል :: አስቀድሞ ዕለተ ቅዳሜ የአይሁድ ሰንበት ነበረች ጌታችንም እንደተናገረው ሕግ ና ነቢያትን ልፈጽም እንጂ ልሽራቸው አልመጣውም እንዳለ የአይሁድ ሰንበት ቅዳሜም አልተሻረችም ስለዚህ ቤተ ክርስቲያን ቀዳዊት ሰንበት የቀደመች ሰንበት ብላ ታስባታለችች :: ማቴ5÷17 አንድም ደግሞ የኦሪት ሥርዓቶች ሁሉ ለአዲስ ኪዳን ሥርዓቶች ምሳሌ ጥላ መርገፍ ናቸውና ቅድስት ቤተ ክርስቲያንም ቅዳሜን እንደ ምሳሌ አድርጋ እሁድን አማናዊት ሰንበት አድርጋ ታስባቸዋለች ::
ዕለተ እሁድ( ሰንበተ ክርስቲያን)
♦ ጥንተ ዕለት ናት :- ፍጥረታት መፈጠር የጀመሩባት ዕለት ናትና "ይህቺ ዕለት ከ7ቱ ዕለታት ቀድማ የተገኘች ናት እንጂ በኃላ የተገኘች አይደለችም " እንዳለ ቅዱስ አትናቲዮስ
♦ በኩረ በዓላት ናት :- የበዓላት ሁሉ መጀመሪያ ናትና
♦ ዓለም የተገኘባት
♦ ወልድ ሰው የሆነባት
♦ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተነሳባት
♦ ዳግመኛ ለፍርድ የሚመጣበት ዕለት ጭምር ናት::
2) ♥ እመቤታችን ዕረፍት ተብላ ትጠራለች ከ5500 ዘመን የድካም የመከራ ጊዜ ሁሉ በእርሷ እረፍትን አግኝተናልና :: እንዴት ቢሉ መላእኩ ቅዱስ ገብርኤል መጥቶ ባበሰራት ጊዜ ለዓለም መዳን ምክንያት ትሆኚ ዘንድ መርጦሻል ብሎ ፍቃዷን በጠየቀ ጊዜ "ይኩነኒ በከመ ትቤለኒ "እነሆኝ የጌታ ባርያ እንደ ቃልህ ይሁንልኝ" በማለት ለድኅነተ ዓለም ምክንያት እረፍት ሆናለች:: ሉቃ 1÷26
3)♥ ቅዱሳን :- እረፍት ተብለው ይጠራሉ::ቅዱሳን በሳኦል መንፈስ ለተያዘችው ደካማዋ ዓለም እረፍት ናቸው " እንዲህም ሆነ፤ ከእግዚአብሔር ዘንድ ክፉ መንፈስ በሳኦል ላይ በሆነ ጊዜ ዳዊት በገና ይዞ በእጁ ይመታ ነበር፤ ሳኦልንም ደስ ያሰኘው ያሳርፈውም ነበር፥ ክፉ መንፈስም ከእርሱ ይርቅ ነበር። (መጽሐፈ ሳሙኤል ቀዳማዊ 16÷23) አንድም ጻድቃን በጸሎታቸው ሕዝብ የሚያሳርፉሁ ናቸው ጻድቃንም በበዙ ጊዜ ሕዝብ ደስ ይለዋልና በመወለዳቸውም ብዙዎች ደስ ተሰኝተዋልና ምሳ 29÷2 ሉቃ 1÷14 ያዕ 5÷16
4)♥ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን እረፍት ትባላለች :- ልበ አምላክ ክቡር ዳዊት እግዚአብሔር እረኛዬ ነው የሚያሳጣኝም የለም በለመለመ መስክ ያሰማራኛል በእረፍት ውኃ ዘንድ ይመራኛል " ብሎ ቤተ እግዚአብሔርን እንደ እረፍት ሥፍራ በውስጧ የሚፈሰውን ቃለ እግዚአብሔርን ደግሞ እንደ መብል እንደ መጠጥ አድርጎ ተናግሯል:: መዝ 22(23)÷1 አንድም የእረፍት ቦታ የሆነችው የመንግስተ ሰማያት የሰማያዊት ኢየሩሳሌም ምሳሌ ናትና እረፍት ተብላ ትጠራለች ::
5) ♥ መንግስተ ሰማያት ራሷ እረፍት ትባላለች እስራኤል ዘሥጋ ድካም ከበዛባት ከምድረ ግብጽ ወተው እረፍት የሆነችውን ምድረ ከንዓንን ወረሰዋል እኛም እስራኤል ዘነፍሶች ከዚህች ድካም ከበዛባት ዓለም እረፍት የምናገኘው በመንግስተ ሰማያት ነውና መንግስተ ሰማያት እረፍት ትባላለች ::
" ነገር ግን። ዓይን ያላየችው ጆሮም ያልሰማው በሰውም ልብ ያልታሰበው እግዚአብሔር ለሚወዱት ያዘጋጀው ተብሎ እንድተጻፈ፥ እንዲህ እንናገራለን።" (1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 2:9)
6) ♥ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ራሱ እረፍት ይባላል :- " እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ፥ ወደ እኔ ኑ፥ እኔም አሳርፋችኋለሁ።" ብሏልና እረፍታችን ነው (የማቴዎስ ወንጌል 11:28) አንድም የእግዚአብሔር መንግስት(የእረፍት ሥፍራ) ከወድየት አለች ብለው በጠየቁት ጊዜ " ደግሞም። እንኋት በዚህ ወይም። እንኋት በዚያ አይሉአትም። እነሆ፥ የእግዚአብሔር መንግሥት በመካከላችሁ ናትና አላቸው።" (የሉቃስ ወንጌል 17:21) ይህን ያለው በመካከላቸው የነበረው እርሱ መንግስተ ሰማያት የእረፍት ሥፍራ ወይም እረፍታችን በመሆኑ ነው ::
ስለዚህ እኛ ክርስቲያኖች የሰንበትን ቅድስና ስናስብ እግዚአብሔርን እመቤታችንን ቅዱሳንን መንግስተ ሰማያትን ሁሉ ታሳቢ ማድረግ ይገባናል ማለት ነው::
ማሳሰቢያ
********
እረፍትን ለማግኘት አስቀድሞ ሥራ ሊኖር ይገባል ሥራ በሌለበት እረፍት የለም:: እንድ ሰው አረፈ ለማለት አስቀድሞ ሥራ ሰራ ሊባል ይገባዋል:: እግዚአብሔርም ከሰራው ሥራ ሁለ አረፈ ተብሎ ተጻፈ እንጂ አረፈ ተብሎ ብቻ አልተጻፈልንም በመሆኑም እኛ ክርስቲያኖች እረፍተ መንግስተ ሰማያትን እረፍት እግዚአብሔርን እረፍት እመቤታችንን እረፍት ቅዱሳንን ለማግኘት በጎ ሥራን ሁሉ ልንሰራ ያስፈልጋል ::
አንድ ሊቅ በሰንበት አንድ ሥራ ሲሰሩ የኔ ቢጤ ጨዋ መቶ ምነው አባ እግዚአብሔር እንኳን ባረፈበት ቀን በሰንበት ለምን ሥራ ይሰራሉ አላቸው ሊቁም ፈገግ ብለው አዮትና ልጄ እርሱ ኮ ያረፈው ሥራውን ሁሉ ጨርሶ ነው እኔ ምን ሰርቼ ነው የማርፈው አሉት ይባላል ::
በሰንበት ለሰንበት የሚገባ ሥራ ልንሰራበት ይገባል እንጂ ሥራ ፈተን መቀመጥ አይገባንም ሥራ የፈታ አህምሮ የሰይጣን ቢሮ ነውና ያለ ሥራ የተቀመጠ ሰው ሊስት ሊሳሳት ይችላል:: በሰንበት ዝም ብሎ ከመቀመጥ ወደ ቤተ እግዚአብሔር መሄድ የታመመ ካለ መጠየቅ መጸለይ ሌላም ሌላም የትሩፋት ሥራ ልንሰራ ይገባል :: ይህን ካደረግን ቅድስት ከሆነችው ከሰንበት ረድኤትና በረከትን እናገኛለን::
.........ይቆየን...........