ዐውደ ምሕረት
3.69K subscribers
930 photos
24 videos
271 files
193 links
"ቤተ ክርስቲያን ባሕረ ጥበባት
አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት"
Download Telegram
#እመቤታችን_ቅድስት_ድንግል_ማርያም_መድኃኒታችን_ናት

የድኅነት ምክንያት በራሱ መድኃት ነው፡፡ የመድኃቱ መገኛ መሆን በራሱም መድኃኒት ያሰኘዋል፡፡ አዳኝ እግዚአብሔር መሆኑ እሙን ነው፡፡ እግዚአብሔር ደግሞ በምክኒያትም አለምክኒያትም ያድናል፡፡ ይህ ማለት ሌላ የማዳኛ መንገድ ተጠቅሞ ሊያድን ይችላል፡፡ ሳይጠቀምም ሊያድን ይችላል፡፡ ቅዱሳኑን ተጠቅሞ ሊያድን ይችላል፣ በጠበል ሊያድን ይችላል አልያም ሌላ መንገድ ተጠቅሞ ሊያድን ይችላል፡፡ በተቃራኒው ደግሞ ምንም አይነት የማዳኛ መንገድ ሳይጠቀም ሊያድን ይችላል፡፡ ለምሳሌ ዮሐ 5፡1-9 ላይ ስንመለከት በቤተ ሳይዳ 38 ዓመት ሙሉ አልጋው ላይ ተኝቶ የነበረውን ሰው ያዳነው ምንም ምክኒያት ሳይጠቀም ነው፡፡ ‹‹ልትድን ትወዳለህን›› አለው ከዛም ‹‹አልጋህን ተሸክመህ ሂድ፡፡›› አለው፡፡ በዮሐ 9፡1-7 በዚህ ክፍል ስንመለከት ደግሞ ጌታችን የእውሩን ዐይን ያበራለት በጠበል ሄዶ እንዲጠመቅ በማዘዝ ነበር፡፡ አዳኙ እግዚአብሔር ነው፡፡ ምክንያተ ድኅነቱ ደግሞ ጠበል፡፡ ጠበሉ ምክንያተ ድኂን በመሆኑ መድኃኒት ነው፡፡
መዝ 3፡8 ‹‹ማዳን የእግዚአብሔር ነው፡፡›› ይላል፡፡ በመሳ 3፡9 ላይ ደግሞ ‹‹የእስራኤል ልጆች ወደ እግዚአብሔር ጮኹ፡፡ እግዚአብሔርም የሚያድናቸውን የቄኔዝን ልጅ ጎቶንያልን አዳኝ አድርጎ አስነሳላቸው፡፡›› እነዚህ ሁለት ቃላት እርስ በራሳቸው የሚገጩ ይመስላሉ፡፡ ነገር ግን በፍጹም አይጋጩም፡፡ ማዳን የእግዚአብሔር ቢሆንም እንዲሁም አዳኝ ተብሎ ሊጠራ የሚገባው አርሱ ሆኖ ሳለ ስለምን ጎቶንያል አዳኝ (መዳኒት) ተብሎ ተጠራ ቢሉ ምክንያቱም እስራኤልን እግዚአብሔር ያዳናቸው ጎቶንያልን ምክንያት አድርጎ ስለሆነ ነው፡፡ ስለዚህ ጎቶንያል ምክንያተ ድኂን ስለሆነ አዳኝ ተብሎ ተጠርቷል፡፡
ከላይ ባነሳናቸው ምሳሌዎች መሰረት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምም የሰው ልጆች የድኅነት መፈጸሚያ ምክንያተ ድኂን በመሆኑዋ መድኃኒት ትባላለች፡፡ ለዚህ ነው በተዓምረ ማርያም መቅድም ላይ ‹‹መድኃኒታችሁ ናት›› ተብላ የተጠራችው፡፡ ለአዳም የተገባት ቃል ኪዳን ዘመኑ ሲፈጸም እግዚአብሔር ሰው ሆኖ እንደሚያድነው ነው፡፡ ገላ 4፡4 ይህ የመዳን ቃል ኪዳን እንዲፈጸም የግድ አምላክ ሰው መሆን አለበት፡፡ አምላክ ሰው እንዲሆን ደግሞ የግድ የሰውን ሥጋ መዋሐድ አለበት፡፡ ያንን ሥጋ ደግሞ ያገኘው ከንጽሕት ዘር ከእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ነው፡፡ በአጭሩ የአዳም መድኃኒት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ናት ማለት ይቻላል፡፡ አዳም ለመዳን የግድ የተገባለት ቃል ኪዳን መፈጸም አለበት፡፡ ያ ቃልኪዳን እንዲፈጸም የግድ እመቤታችን ቅደስት ድንግል ማርያም መኖር አለባት፡፡ ከእመቤታችን የተገኘው ሥጋ ነው በቀራንዮ የተሰቀለው፡፡ ከእመቤታችን የተገኘው ነፍስ ነው በአካለ ነፍስ ሲዖል ወርዶ አዳምና የልጅ ልጆቹን ከሲዖል ወደ ገነት ያስገባቸው፡፡ ከእመቤታችን የተገኘው ሥጋ ወደም ነው የዘላለም ሕይወትን ሥረይተ ኃጢአትን አሰጥቶ ድኅነት መንግሥተ ሰማይን የሚያስወርሰው፡፡ ዮሐ 6፡53-54 ለመዳናችን ምክኒያት የሆነው መድኃኒቱ የተገኘው ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም በመሆኑ ለአዳም የድኅነቱ ምክንያት መድኃኒቱ፣ የቃልኪዳኑ መፈጸሚያ የድኅነቱ ማረጋገጫ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ናት፡፡ በመሆኑም ዓለም ያለ እመቤታችን አልዳነም፡፡
ድኅነቱ ተፈጸመ ማለት ደግሞ ገነት ተከፈተ ማለት ነው፡፡ ጌታችን እስኪሞት በአካለ ነፍስ ሲዖል እስኪወርድ ድረስ የሞቱት አዳም እና የልጅ ልጆቹ ጌታችን እመቤታችንን ምክኒያት አድርጎ በፈጸመላቸው ድኅነት ተጠቅመው ገነትን አግኝተዋል፡፡ ጥያቄው ከዛ በኋላ ላሉ ሰዎችስ ድኅነቱ ምንድን ነው ቢሉ የገነት መከፈት ነው፡፡ ገነት ተከፍቷል ማለት ደግሞ ገነት ለመግባት የሚደረጉ ሥራዎች አሉ ማለት ነው፡፡ ከነዛም መካከል የሰዎች ልጆች እንዲድኑ ቅዱሳን በምልጃቸውና በተገባላቸው ቃልኪዳን መሰረት ወደ መዳን የሚያደርሱ መድኃኒቶች ይሆናሉ፡፡ ጌታችን አንድ ጊዜ ድኅነቱን ከፈጸመ በኋላ ሁሉንም አዲስ አደርጓቸው ነበር፡፡ ነገር ግን የሰው ልጅ በኃጢያት ምክንያት ስለሚያረጅ ድጋሚ የማዳን ስራውን ከሰማይ ወርዶ አይፈጽምልንም፡፡ ይልቁንም ቅዱሳኑን ምክንያት አድርጎ ያድነናል እንጂ፡፡ ዕብ 2፡14 ‹‹ሁሉ መዳንን ይወርሱ ዘንድ ስላላቸው ለማገዝ የሚላኩ የሚያገለግሉም መናፍስት አይደሉምን;›› እንዲል በሌላም ስፍራ 2ኛቆሮ 5:15-20 ‹‹በሕይወትም ያሉት ስለ እነርሱ ለሞተውና ለተነሣው እንጂ ወደ ፊት ለራሳቸው እንዳይኖሩ ስለ ሁሉ ሞተ። ስለዚህ እኛ ከአሁን ጀምሮ ማንንም በሥጋ እንደሚሆን አናውቅም፤ ክርስቶስንም በሥጋ እንደ ሆነ ያወቅነው ብንሆን እንኳ፥ አሁን ግን ከእንግዲህ ወዲህ እንደዚህ አናውቀውም። ስለዚህ ማንም በክርስቶስ ቢሆን አዲስ ፍጥረት ነው፤ አሮጌው ነገር አልፎአል፤ እነሆ፥ ሁሉም አዲስ ሆኖአል። ነገር ግን የሆነው ሁሉ፥ በክርስቶስ ከራሱ ጋር ካስታረቀን የማስታረቅም አገልግሎት ከሰጠን፥ ከእግዚአብሔር ነው፤ እግዚአብሔር በክርስቶስ ሆኖ ዓለሙን ከራሱ ጋር ያስታርቅ ነበርና፥ በደላቸውን አይቆጥርባቸውም ነበር፤ በእኛም የማስታረቅ ቃል አኖረ። እንግዲህ እግዚአብሔር በእኛ እንደሚማለድ ስለ ክርስቶስ መልክተኞች ነን፤ ከእግዚአብሔር ጋር ታረቁ ብለን ስለ ክርስቶስ እንለምናለን።›› ብለው ከአሁን ወዲያ ቅዱሳን የሰዎች የመዳኛ መንገድ እነርሱ መሆናቸውን ተናገሩ፡፡
ጌታችን በወንጌል ማቴ 10፡41 ‹‹ጻድቅን በጻድቅ ስም የሚቀበል የጻድቁን ዋጋ ይቀበላል፡፡ ነቢይንም በነቢይ ስም የሚቀበል የነቢዩን ዋጋ ይወስዳል፡፡ ማንም ከእነዚህ ለታናናሾች በደቀ መዝሙሬ ስም ጥቂት ውሃ ቢሰጥ እውነት እውነት እላችኋለው ዋጋው አይጠፋበትም፡፡›› ብሎ ለነድያን በቅዱሳን ስም ጥርኝ ውሃ መዘከር እንኳን ዋጋ መንግሥተ ሰማይን እንደሚያስወርስ እንዲሁም እንደሚያድን ተናግሯል፡፡

በወንድማችን #አቤኔዘር

👉 @AwediMeherit