ይጠጣ ነበር።(1ኛ ነገ 17:2-6) በጥቂት ብቻ በእግዚአብሔር ተአምር የኖሩ ቅዱሳን ብዙ ናቸው።በተለይም ርእሰ ባሕታውያን አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ለዚህ ትልቅ ማሳያ ናቸው።562 ዓመት ሙሉ የእናታቸውን ጡት ጨምሮ ያለ ምግብ ፣ ያለ ልብስና ያለ መጠለያ በጾምና በጸሎት ያውም ከብዙ ሺ ስግደቶችና ተጋድሎዎች ጋር ተጸምዶ መኖር ያልተደነቀ ምን ይደነቃል!?ይኸውም የሆነው ከእግዚአብሔር አፍ በሚወጣ ቃል (በተአምር) ነው እንጂ በሌላ አይደለም።እግዚአብሔር "ይሁን" ያለው ይሆናል፤"ይሁን" ያላለውም አይሆንምና።በተፈጥሮ ለሰው ምግብ እንዲያስፈልገው ያደረገ አምላክ እንዳያስፈልገውም ማድረግ ይችላል።አሁንም ቢሆን በጥቂት ብቻ በበረከቱ የሚያኖራቸው ደጋግ ክርስቲያኖች ሞልተዋል።
"ከእግዚአብሔር አፍ የሚወጣ ቃል" አካላዊ ቃል ወልደ አብ ወልደ ማርያም ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።ስለዚህ በእርሱ በማመን በሃይማኖት በር ገብተን፤በቀጠነችው መንገድ በፈቃደ ነፍስ ተጉዘን፤ሕይወት የሆነው እርሱ ጋር ደርሰን በሕይወት እንኖራለን።ይህንን ሐሳብ ራሱ አምላካችን እንዲህ ሲል ገልጦታል።"በጠበበው ደጅ ግቡ፤ ወደ ጥፋት የሚወስደው ደጅ ሰፊ፥ መንገዱም ትልቅ ነውና፥ ወደ እርሱም የሚገቡ ብዙዎች ናቸው፤ ወደ ሕይወት የሚወስደው ደጅ የጠበበ፥ መንገዱም የቀጠነ ነውና፥ የሚያገኙትም ጥቂቶች ናቸው።" (ማቴ 7:13) ስለዚህ ሰው ጠባብ በር በተባለው በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እውነተኛ አምላክነትና የዘለዓለም ሕይወትነት (1ኛ ዮሐ 5:20) አምኖ ፤ በቀጠነው መንገድ በእግዚአብሔር ፈቃድ ተጉዞ ፤ የአካላዊ ቃል የኢየሱስ ክርስቶስን ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ተቀብሎ፤ራሱ ሕይወት የሆነው እግዚአብሔር ጋር ይደርሳል።መነሻውም መገስገሻውም መዳረሻውም እውነተኛ አምላኩ ኢየሱስ ክርስቶስ ይሆናል ማለት ነው።እግዚአብሔር በቸርነቱ ጾሙን ስስትን ድል የምንነሣበት ያድርግልን!!!
መጋቢት 2/2016 ዓ.ም
#ኢዮብ ክንፈ

Forwarded from የዘማሪ ዳዊት ክብሩ Zemari Dawit Kibru Official Telegram Channel
http://www.youtube.com/@ZemariDawitkibru2405 Youtube channel - Zemari Dawit kibru | Official ዘማሪ ዳዊት ክብሩ
ሰላም የፌስቡክ ጓደኞቼ እና ወንድም እህቶቼ ለአገልግሎት መስፋፋት የዩትዩብ ገጽ መክፈቴን ያውቃሉ? ካላወቁስ መክፈቴን ላብስርዎ አገልግሎቱ እንዲበረታ እና የእኔን የዝማሬ አዳዲስ ሥራዎች በፍጥነት ያገኙ ዘንድ ከዚህ በታች ያለውን ማስፈንጠሪያ በመጫን እንዲቀላቀሉና ሌሎችም ቤተሰቦችን እንዲቀላቀሉ እንድታደርጉልኝ በአምላከ ተክለሃይማኖት ስም እጠይቃለሁኝ። ስለምታደርጉልኝ ሁሉ ጥረት እግዚአብሔር ይስጥልኝ ፤ እግዚአብሔር ያክብርልኝ!
Youtube channel - Zemari Dawit kibru | Official ዘማሪ ዳዊት ክብሩ
http://www.youtube.com/@ZemariDawitkibru2405

"ከዚህ በኋላ ዲያብሎስ ወደ ቅድስት ከተማ ወሰደውና እርሱን በመቅደስ ጫፍ ላይ አቁሞ፤መላእክቱን ስለ አንተ ያዝልሃል እግርህንም በድንጋይ ከቶ እንዳትሰናከል በእጃቸው ያነሡሃል ተብሎ ተጽፎአልና የእግዚአብሔር ልጅስ ከሆንህ፤ ወደ ታች ራስህን ወርውር አለው።"(ማቴ 4:5-6)
በፈቃዱ ሄደለት ለማለት ነው እንጂ ዲያቢሎስስ ጌታን መውሰድ አይቻለውም።ዲያቢሎስ ካህናትን ድል በምነሣበት መቅደስ ቢሆን እኔ ነበርኩ የማሸንፈው ብሎ ቢያሰብ ጌታችን ፈቃዱን ዐውቆ ሄደለት።መዝ 90:11-12 ላይ የተጻፈውን ቃል ጠቅሶ ፈተነው፤ዳዊት ደጋሚ አይመስልም!?ዳዊት ሲደገም ብን ብሎ የሚጠፋ ጠላት ለፈተና ግን ከዳዊት ጠቀሰ።
አስቀድሞ በማኅበረ መላእክት ውስጥ ትዕቢትን ከልቡናው አመንጭቶ ሐሰትን በአንደበቱ የተናገረ "የሐሰት አባቷ" ዲያቢሎስ ነው።የሌለውን የባሕርይ አምላክነት ፈልጎ በትዕቢት ወድቋል።ትዕቢት ማለትም ራስን ብቅ (ከፍ) ሌላውን ዝቅ ማድረግ ነው።ሳጥናኤል በልቡ ራሱን ከፍ አድርጎ ከሥላሴ እንደ አንዱ ለመሆን ከጅሏል።ለዚህ ነው ያልፈጠራቸውን መላእክት ፈጠርኳችሁ ብሎ "ሐሰትን" የተናገረው።ትዕቢትና ሐሰት ጓደኛሞች ናቸው፤ተለያይተውም አያውቁም።
እሱ በወደቀበት ትዕቢት እናታችን ሔዋንን ፈትኗታል።ከትዕቢት የማትለይ ሐሰትንም ነግሯታል።"እባብም ለሴቲቱ አላት፦ ሞትን አትሞቱም፤ከእርስዋ በበላችሁ ቀን ዓይኖቻችሁ እንዲከፈቱ እንደ እግዚአብሔርም መልካምንና ክፉን የምታውቁ እንድትሆኑ እግዚአብሔር ስለሚያውቅ ነው እንጂ።" (ዘፍ 3:4-5) ዲያቢሎስ ቀድሞም ለሔዋን ኋላም ለጌታችን ያቀረበው ፈተና ያልኳችሁን ብታደርጉ ምንም አትሆኑም የሚል ነው።ዛሬም ይህ ፈተና አይቀርልንም። "ይህን ኃጢአት ብታደርግ ምን ትሆናለህ?የእግዚአብሔር ልጅ ከሆንህ ራስህን ወደ ፈተና ወርውር እግርህ በኃጢአት እንዳትሰነካከል መላእክቱን ስለ አንተ ያዝዝልሃል።" በማለት በትዕቢት ይፈትነናል።
ከሌሎች የተሻለ ጥበቃና ከለላ እንደሚደረግልን ማሰብ፤ወይም በአንዳች ነገር ከሌሎች እንደምንሻል መገመት፤ይህን ኃጢአት ብሠራ ማን ያየኛል?ማንስ ከልካይ አለብኝ? ማለት ትዕቢት ነው።ትዕቢት ከእግዚአብሔር ለይቶ ከሰይጣን ያወዳጃል።"በዓይኑ ትዕቢተኛ የሆነውና በልቡ የሚሳሳው ከእኔ ጋር አይተባበርም"(መዝ 100:5) ተብሎ የተጻፈውም ለዚህ ነው።ይህ ማለት በትዕቢትና በስስት የተሸነፈ ሰው ከእግዚአብሔር ጋር አንድ አይሆንም ማለት ነው።በዘመነ ፍዳ "የባለጠጎችን ስድብና የትዕቢተኞችን ንቀት ነፍሳችን እጅግ ጠገበች" ተብሎ እስኪጻፍ ድረስ ባለጠጎችና ትዕቢተኞች የተባሉ አጋንንት እጅጉን በርትተውብን ነበር።(መዝ 122:4)
"ጌታችን ኢየሱስም፦ ጌታን አምላክህን አትፈታተነው ተብሎ ደግሞ ተጽፎአል አለው።" (ማቴ 4:7)መምህረ ትሕትና ኢየሱስ ክርስቶስ ትዕቢተኛውን በትሕትና አዋረደው።"ምንም አይሳነኝም" ብሎ ራሱን ከመቅደሱ ጫፍ ላይ አልወረወረም።በተአምር ሳይሆን በመጽሐፍ ቃል ድል ነሣው።ልበ አምላክ ክቡር ዳዊትም "አንተ የተጠቃውን ሕዝብ ታድናለህና፤የትዕቢተኞችን ዓይን ግን ታዋርዳለህ" (መዝ 17:27) በማለት እንደዘመረው 5500 ዘመን ሙሉ በአጋንንት የተጠቃውን ሕዝብ ለማዳን የትዕቢተኞቹን (የአጋንንትን) ዓይን በትሕትና አዋርዷል።
እመ ትሕትና ድንግል ማርያም"ትዕቢተኞችን በልባቸው ሐሳብ በትኖአል ...ትሑታንንም ከፍ አድርጎአል"(ሉቃ 1:51-52) ስትል ቅዱስ ጴጥሮስና ቅዱስ ያዕቆብ በአንድ ቃል "እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማል ለትሑታን ግን ጸጋን ይሰጣል"(1ኛ ጴጥ 5:5፤ያዕ 4:6) በማለት ከአምላካቸው እናት ጋር አንድ ዓይነት ሐሳብን ገልጠዋል።ቅዱስ ጳውሎስ "አንተ እንድትበልጥ ማን አድርጎሃል?ያልተቀበልኸውስ ምን አለ?የተቀበልኽ ከሆንክስ እንዳልተቀበለ የምትመካ ስለ ምንድነው?"(1ኛ ቆሮ 4:7) በማለት ከሌላው እንደማንበልጥ፤ያለን ነገር ሁሉ ተሰጥቶን እንጂ ከራሳችን የሆነ እንዳልሆነ፤ባለን ነገርም መመካት እንደማይገባ የትሕትናን ነገር አስተምሮናል።
በትዕቢት (ሌሎችን በመናቅ) የምናገለግለውን አገልግሎት እግዚአብሔር ስለማይቀበለው እጅግ ጠንቃቆች ልንሆን ያስፈልገናል።"ከነዚህ ከታናናሾቹ አንዱን እንዳትንቁ ተጠንቀቁ፤ መላእክቶቻቸው በሰማያት ዘወትር በሰማያት ያለውን የአባቴን ፊት ያያሉ እላችኋለሁና።"(ማቴ 18:10)ጌታችን እኛ ታናሽ ናቸው ብለን ልንንቃቸው የምንፈልጋቸውን ሰዎች ክብራቸውን በማሳየት "ከመናቅ" እንድንጠነቀቅ አሳስቦናል።ትዕቢት የተሸነፈበትን የጌታችንን ጾም እየጾምን እንኳን የምንታበይ ብዙዎች ነን።ከሌሎች በተሻለ ረዘም ላለ ሰዓት ከእህል ከውኃ ስለተከለከልን የተሻልን ጿሚዎች አይደለንም።ብዙ ገንዘብ ስለመጸወትንም የተለየን መጽዋቾች አይደለንም።በየዕለቱ ለረጅም ሰዓት የተለያዩ ጸሎቶችን ስለጸለይንም ልዩ ክርስቲያኖች አይደለንም።ይህንን ከልብ ማመን ያስፈልጋል።እግዚአብሔር የሚያውቃቸው እኛ የማናውቃቸው በዙሪያችን ያሉ (ከምንም የማንቆጥራቸውን) ወዳጆቹን ትሩፋት ቢገልጽልን፤ገና የጽድቅን "ሀ ፡ ሁ" እንደማናውቅ ይገባን ነበር።ለዚህ ነው "እያንዳንዱ ባልንጀራው ከራሱ ይልቅ እንዲሻል በትሕትና ይቁጠር" (ፊል 2:3) በማለት ሐዋርያው ያስጠነቀቀን!!!ጾሙን የትሕትና ያድርግልን አሜን!!!
ኢዮብ ክንፈ
መጋቢት 17/2016 ዓ.ም

Forwarded from የዘማሪ ዳዊት ክብሩ Zemari Dawit Kibru Official Telegram Channel (Dawit Kibru)
ለዚህ የበረከት ሥራ ዝግጁ የሆናችሁ በዕለቱ በመገኘት እንድትሳተፉ እንላለን !!!
Forwarded from የዘማሪ ዳዊት ክብሩ Zemari Dawit Kibru Official Telegram Channel (Dawit Kibru)
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የቁርሳችንን በማስገባት የበረከቱ ተካፋይ ይሁኑ ወዳጆች !!!!
Forwarded from የዘማሪ ዳዊት ክብሩ Zemari Dawit Kibru Official Telegram Channel (Dawit Kibru)
Forwarded from የዘማሪ ዳዊት ክብሩ Zemari Dawit Kibru Official Telegram Channel (Dawit Kibru)
http://www.youtube.com/@ZemariDawitkibru2405 Youtube channel - Zemari Dawit kibru | Official ዘማሪ ዳዊት ክብሩ
Forwarded from የዘማሪ ዳዊት ክብሩ Zemari Dawit Kibru Official Telegram Channel
YouTube
🛑አዲስ ዝማሬ "አንቺ ነሽ " ዘማሪ ዳዊት ክብሩ ◈New Mezmur "Anchi Nesh" Z Dawit Kibru (Lyrics)
መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ያመሰገነሽ፤
ወላዲተ አምላክ ድንግል አንቺ ነሽ።
የመለኮት ማደሪያ ነሽ የብርሃን ድንኳን፤
ለመላእክት እኅት መሪ የኾንሽ ለጻድቃን።
የሕዝብ ሁሉ ኸኸ እናት ኸኸ የሁሉ እመቤት፤
የዓዳም ተስፋ ስንቅ የሆንሽ የዳነብሽ ከሞት
አንቺ ነሽ /2/ ብፅዕት ኪዳነ ምሕረት፤
ለዓለም ሁሉ መዳን ምክንያት የቃል እናት ታቦት
ለዓለም ሁሉ መድኃኒት የቃልኪዳኑ ታቦት።
ወርቅ የተጎናጽፈሽ፥…
ወላዲተ አምላክ ድንግል አንቺ ነሽ።
የመለኮት ማደሪያ ነሽ የብርሃን ድንኳን፤
ለመላእክት እኅት መሪ የኾንሽ ለጻድቃን።
የሕዝብ ሁሉ ኸኸ እናት ኸኸ የሁሉ እመቤት፤
የዓዳም ተስፋ ስንቅ የሆንሽ የዳነብሽ ከሞት
አንቺ ነሽ /2/ ብፅዕት ኪዳነ ምሕረት፤
ለዓለም ሁሉ መዳን ምክንያት የቃል እናት ታቦት
ለዓለም ሁሉ መድኃኒት የቃልኪዳኑ ታቦት።
ወርቅ የተጎናጽፈሽ፥…
Forwarded from የዘማሪ ዳዊት ክብሩ Zemari Dawit Kibru Official Telegram Channel (Dawit Kibru)
http://www.youtube.com/@ZemariDawitkibru2405 Youtube channel - Zemari Dawit kibru | Official ዘማሪ ዳዊት ክብሩ
Forwarded from የዘማሪ ዳዊት ክብሩ Zemari Dawit Kibru Official Telegram Channel (Dawit Kibru)
ከደመና በታች
አዲስ ዝማሬ
እግዚአብሔር ቢፈቅድ ነገ እሁድ ምሽት
በዩትዩብ ቻናል ላይ ይጠብቁን !!!!
http://www.youtube.com/@ZemariDawitkibru2405
Youtube channel - Zemari Dawit kibru | Official ዘማሪ ዳዊት ክብሩ
👆👆👆
Subscrib Here
#Zemari_Dawit_kibru
#ዘማሪ_ዳዊት_ክብሩ
#ከደመና_በታች
#newvideo
#mezmur
#orthodoxmezmur