ዐውደ ምሕረት
3.67K subscribers
932 photos
24 videos
271 files
195 links
"ቤተ ክርስቲያን ባሕረ ጥበባት
አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት"
Download Telegram
" ሁለቱም አንድ ይሆናሉ "


Photo credit

26 - 05 - 2016 ዓ.ም አቤቶ ፕሮዳክሽን
0953856891
ላይ ይደውሉልን
መርሃግብርዎትን ከእኛ ጋር በመሆን ያሳምሩት !!!
አዲሱ ወይን

ይህ ቃል ለብዙዎቻችን አዲስ አይደለም።በቅዱስ ወንጌል ንባብ፣በሠርግ ዝማሬዎችና በመንፈሳዊ ስብከቶች ውስጥ ደጋግመን ሰምተነዋል።ምንም እንኳን "ቃና ዘገሊላ" የሚለው ቃል ለጆሮአችን አዲስ ባይሆንም አዲስ ምሥጢር የተፈጸመበት ቦታ ነው።

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በእደ ዮሐንስ በዮርዳኖስ ወንዝ ተጠምቆ፤በገዳመ ቆሮንጦስ ሦስቱን አርእስተ ኃጣውእ በሦስቱ አርእስተ ምግባራት ድል ነሥቶ፤ከገዳም በወጣ :

"በሦስተኛው ቀን በቃና ዘገሊላ ሠርግ ሆነ።የጌታችን የኢየሱስ እናትም በዚያ ነበረች።" ብሎ ፍቁረ እግዚእ ቅዱስ ዮሐንስ ጻፈልን።ይህቺን "ቃና" የተባለች ስፍራ "ዘገሊላ" ወይም በገሊላ አውራጃ የምትገኝ በማለት ከሌሎች ቃናዎች ለይቶልናል።

ይህቺ መንደር(ቃና ዘገሊላ)ድሆችና አሕዛብ የሚበዙባት መንደር ናት።ጌታችን ጥንቱንም ሰው የሆነው ድሆችን ባለጠጎች አሕዛብንም ሕዝብ ሊያደርግ ነውና።

"የጌታችን የኢየሱስም እናት በዚያ ነበረች" ሲል ወንጌላዊው ትረካውን ይቀጥላል።"ሙሽራዋ ንጹሕ የሆነ ንጽሕት የሠርግ ቤት" በሠርግ ቤት ተገኘች።ከሠርጉ በኋላ የተጠቀሰችው የመጀመሪያዋ አካል እመቤታችን ናት።እንግዲህ ቅዱስ ዮሐንስ ነባቤ መለኮት ነውና እርሷን ያስቀደመበት ምክንያት አለው።

ከእርሷ ለሚገኘው ፀሐይ ሰማይ፤ከእርሷ ለሚወለደው ፍሬ አበባ፤ከእርሷ ለሚፈስስልን ወንዝ ምንጭ ናትና መሠረቲቱን አስቀድሞ ሕይወትን ሊያስከትል ነው።እሷ መሠረተ ሕይወት ናትና።የምትሠራውም ግሩም ሥራ አለና እሷን አስቀደመ።የሠርግ ቤቷ ስንዱ ከሆነች ዘንድ ሙሽራውንና ሙሽሪትን፣መብልና መጠጥን፣ከበሮንና መዝሙርን፤የሙሽራውንና የሙሽሪትን ዘመዶች አንድ መሆን እንጠብቃለን።

"ጌታችን ኢየሱስም ደግሞ ደቀመዛሙርቱም ወደ ሠርጉ ታደሙ።" እናት ካለች ልጅ መምህርም ካለ ደቀመዛሙርት አሉና፤ሠርገኞቹ እናትን ከልጇ መምህሩንም ከተማሪዎቹ ጋር ጠሯቸው።ጉባኤ ሐዋርያት ቅድስት ቤተክርስቲያንም በሠርጉ ተገኘች።

"የወይን ጠጅም ባለቀ ጊዜ የጌታችን የኢየሱስ እናት የወይን ጠጅኮ የላቸውም አለችው።" ምልዕተ ጸጋ ናትና ማንም ሳይነግራት ዐውቃ፤ርኅርኂተ ኅሊና ናትና ለሙሽሮቹና ለቤተ ዘመዶቻቸው ራርታ፤ትምክህተ ዘመድነ ድንግል ማርያም ልጇን ለመነች።መስጠት ስትችል ልጇ እንዲሰጣቸው አሳሰበች።የራሷ ክብር ከሚገለጥ የልጇ ክብር ቢገለጥ ትወዳለችና።

"መስጠትማ አትችልም" የሚል ማንም ቢኖር ግን ለስም አጠራሯ ክብር ስግደት ይግባትና እንኳን የወይን ጠጅ አማናዊውን (እውነተኛውን) ወይን በሥጋ ወልዳ ሰጥታን የለም ወይ እንለዋለን።ልጇ በማይታበል ቃሉ "እውነተኛ የወይን ግንድ እኔ ነኝ" ብሎ ነግሮናልና።"የወይን ጠጅ እኮ የላቸውም" ባለችው አንዲት የልመና ቃል ብቻ ይህ ዓለም እስከሚያልፍ ድረስ እንደ ልጇ ፈቃድ ለሚጋቡ ሙሽሮች ሁሉ የፍቅር ወይንን ስታሰጥ ትኖራለች።

"ጌታችን ኢየሱስም አንቺ ሴት ከአንቺ ጋር ምን አለኝ?ጊዜዬ ገና አልደረሰም አላት።" የጠይቅሽኝን እንዳላደርግልሽ ከአንቺ ምን ጸብ አለኝ? ማለቱ ነው።ሴት ማለት ምትክ ማለት ነው፤እርሷም የቀዳሚት ሔዋን ምትክ ናትና ሴት አላት።ሴት ማለት "ሥጋሽ ከሥጋዬ አጥንትሽ ከአጥንቴ ነው" ማለት ነውና ይህን ሥጋ የነሣሁት ከአንቺ ነው ለማለት ሴት አላት።

"በአንተና በሴቲቱ በዘርህና በዘሯ መካከል ጠላትነትን አደርጋለሁ።እርሱ ራስህን ይቀጠቅጣል አንተም ሰኮናውን ትነክሳለህ።"(ዘፍ 3:15) የሚለው ትንቢተ እግዚአብሔር የተፈጸመባት፤ ዘሯ(ልጇ) ኢየሱስ ክርስቶስም የዘንዶውን ራስ የቀጠቀጠ(መዝ 73:14)
የሴቶች ሁሉ ራስ ናትና "አንቺ ሴት" አላት።

"ጊዜዬ ገና አልደረሰም" ወይኑ ፈጽሞ አላለቀምና፤ተአምሩን(ክብሩን) የሚገልጥበት ሰዓት አልደረሰምና፤እግዚአብሔር ሥራ የሚሠራበት ጊዜ አለውና፤እውነተኛ ወይን የሆነ ወርቀ ደሙን የሚያፈስስበት ጊዜ አልደረሰምና እንዲህ አለ።ዓለም ሳይፈጠር የወይን ጠጁን ማለቅ የሚያወቅ አምላክ የርኅርኂት እናቱን ምልጃ ጠበቀ።

"እናቱም ለአገልጋዮቹ የሚላችሁን ሁሉ አድርጉ አለቻቸው"።"መርዓቱ ለአብ"(የአብ ሙሽሪቱ) ናትና አብ በብሩህ ደመና በደብረ ታቦር "በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው እርሱን ስሙት" ብሎ የሚነግረንን ቃል እመቤታችን በቤተ ዶኪማስ ነገረችን።ሀሳቧ እንደ አምላክ ሀሳብ የሆነ፤መንፈሷም በልጇ በአምላኳ በመድኃኒቷ በኢየሱስ ክርስቶስ የምትደሰት(ሉቃ 1:47) እመቤታችን ማርያም "በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው የሚላችሁን ሁሉ አድርጉ" አለቻቸው።

እያንዳንዳቸው ከሁለት እስከ ሦስት እንሥራ የሚይዙ ስድስት የድንጋይ ጋኖችን ባቀረቡለት ጊዜ :

"ጌታችን ኢየሱስም ጋኖቹን ውኃ ሙሉአቸው አላቸው።እስከ አፋቸውም ሙሉአቸው አላቸው እስከ አፋቸውም ሞሏቸው።" አገልጋይነት እንዲህ ነው ሊቀ አእላፍ ጋሽ ተሰማ አየለ እንደሚሉት "ለምን?እንዴት?"
ሳይሉ፤ሳይማረሩ እግዚአብሔርን በፍጹም ትሕትና ማገልገል።በእንግድነት በሠርግ ቤት የተገኘ "እውነተኛ የወይን ግንድ" መድኃኔዓለም የወይን ጠጅ ለመስጠት ከአገልጋዮቹ ጋር ያገለግል ጀመር።

ለእግዚአብሔር ሰውን በሥራው ማሳተፉ ልማዱ ነው።ፍጥረቱን ሁሉ የሚጠብቅ ጌታ ለሰው ገነትን ፈጥሮ "ጠብቃት አበጃጃት" አለው፤ሰውን ፈጥሮ "ብዙ ተባዙ ምድርንም ሙሉአት" ብሎ የሰውን ዘር ለማብዛት ለሰው የድርሻውን ሰጠው፤ሁሉን በባሕርይው የሚገዛ አምላክ ሰው ፍጥረቱን በጸጋ እንዲገዛና እንዲነዳ ሰጥቶታል።በዚህ ሠርግ ቤትም አገልጋዮቹን የሥራው ተሳተፊ አደረጋቸው።ቸር መሐሪ ሰውን ወዳጅ ነውና።

"አሁን ቀድታችሁ ለአሳዳሪው ስጡት አላቸው። ሰጡትም" ፡ አንዲት ቃል ሳይወጣ በሀሳቡ ብቻ ውኃውን ወደ ወይን ጠጅ ለውጦ ሰጣቸው።አስቀድሞ በሀሳቡ ብቻ ሰባት ፍጥረታትን የፈጠረ ጌታ አሁንም በሀሳቡ ብቻ ድንቅን ሠራ።በሀሳብ ስንኳ ልሥራ ብል ይቻለኛል ሲል ነው።
ፍጥረትን የሚያስተዳድረውን ጌታ ተአምር ይሥራ እንጂ አስተዳደር አያውቅም እንዳይሉት "ለአሳዳሪው" ስጡት አላቸው።ክቡር ጌታ ክብረ ሥጋን ክብረ ነፍስን የሚያድል ሁሉን የሚያከብር ነውና፤ለአገልጋዮቹ "ለሕዝቡ አድሉ" ማለት ሲቻለው መምህረ ትሕትና ኢየሱስ ክርስቶስ አሳዳሪውን ሳይንቅ "ለአሳዳሪው ስጡት" አለ።ሰጡትም።

"አሳዳሪውም የወይን ጠጅ የሆነውን ውኃ በቀመሰ ጊዜ ከወዴት እንደመጣ አላወቀም፤ውኃውን የቀዱት አገልጋዮች ግን ያውቁ ነበር" : ሙሽሮቹን ለማገልገል የተሰየሙ አገልጋዮች ሰማያዊውን ሙሽራ ከፍጽምት እናቱ ጋር አገለገሉ።በዚህም የጌታ ምሥጢረኛ ሆኑ።አሳዳሪው የማያውቀውን አውቀዋልና።ሁሌም እንዲህ እግዚአብሔርን ከእናቱ ጋር በትሕትና የሚያገለግሉት ምሥጢርን ማወቅ ይሰጣቸዋል።

"አሳዳሪውም ሙሽራውን ጠርቶ ሰው ሁሉ አስቀድሞ መልካሙን የወይን ጠጅ ያቀርባል፤ከሰከሩም በኋላ መናኛውን፤አንተስ መልካሙን የወይን ጠጅ እስካሁን አቆይተሃል አለው።" የሰማያዊው ሙሽራ የክርስቶስ የወይን ጠጅ የሙሽራውን የወይን ጠጅ መናኛ ያሰኘ ነው።የጸሎት ጣዕም የስንፍናን ጣዕም፤የጾም ጣዕም የመብልን ጣዕም፤የምጽዋት ጣዕም የስስትን ጣዕም፤የትሕትና ጣዕም የትዕቢትን ጣዕም፤የቅዱስ ቁርባን ጣዕም የኃጢአትን ሁሉ ጣዕም መናኛ የሚያሰኝ ነው።የበለጠ ጣዕም እንዳለ ቢገባቸው "ሰማዕታት የዚህችን ዓለም ጣዕም በእውነት ናቁ፤ደማቸውንም ስለ እግዚአብሔር አፈሰሱ ስለ መንግሥተ ሰማያትም መራራ ሞትን ታገሱ።"
ከላይኛው የቀጠለ ...

"ጌታችን ኢየሱስ ይህንን የምልክቶች መጀመሪያ በገሊላ ቃና አደረገ።ክብሩንም ገለጠ።ደቀመዛሙርቱም በእርሱ አመኑ።" ለሥራው ሁሉ መግቢያ ካደረጋት ጥምቀትና የበጎ ሥራዎች ሁሉ ጥንት ከሆነችው ከጾሙ በኋላ የመጀመሪያው ተአምር(ምልክት) ይህ ነው ለማለት ነው እንጂ ጥንቱንስ ጌታ ከፅንሰቱና ከሕፃንነቱ ዕድሜ አንሥቶ ተአምር ያላደረገበት ጊዜ የለም።የባሕርይ ክብሩን ገለጠ።ደቀመዛሙርቱም በባሕርይ አምላክነቱ አመኑ።

ሰይጣን "እነዚህ ድንጋዮች እንጀራ እንዲሆኑ በል" ሲለው ባለማድረግ ያሳፈረው ጌታ፤"እናቱ የወይን ጠጅ እኮ የላቸውም" ስትለው ልመናዋን ተቀብሎ ውኃው የወይን ጠጅ በማድረግ ፈጽሞላታል።"ከእኔ ተማሩ"(ማቴ 11:29) ብሎናልና ዲያቢሎስ የሚለንን አምቢ እያልን(ያዕ 4:7) እመቤታችንን ግን እሺ እያልን እንኖራለን።እሷ "የሚላችሁን ሁሉ አድርጉ" አይደል እንዴ ያለቺው የሚለን ሰው ቢኖር አዎ እርሷም እኮ የምትለን እሱ የሚለንን ነው ብለን እንመልስለታለን።"የሚላችሁን ሁሉ አድርጉ" እንዳለችን አባቱም "እርሱን ስሙት" ብሎናልና።አብም የሚነግረን በወልድ ቃልነት ነውና(ዮሐ 1:1፤ዕብ 1:1-2) እሷን መስማት እርሱን መስማት ነው። ይቀጥላል ...

ኢዮብ ክንፈ
ጥር 29/2016 ዓ.ም
+++ ማዕበሉ ካልተረጋጋ አንተ ተረጋጋ +++

(በወጀብና በዐውሎ ነፋስ መካከል መንገድ ያለው የድንግል ልጅ ቅዱስ አማኑኤል ፍጹም መረጋጋትን ያድለን!!)

ስለ ኑሮ፣ ስለ ትዳር፣ ተጨማሪ ገቢ ስለማግኘት፣ የሥራ ዘርፍ ስለመቀየር ወይም አልሞላ ባለህ አንዳች ነገር ደግሞም በውል ባላወቅኽው ነገር እየተጨነቅህ ውስጣህ አልረጋጋ ብሎህ ተቸግረሃል፡፡

ይኽ ብቻ አይደለም የምታልመውና ልትደርስበት የምትፈልገው ቦታ አሁን ከሆንከውና ካለህበት ሁኔታ ጋር አለመግጠሙም ናላህን አዙሮት ይሆናል፡፡ ባንተ ዕይታና ከሰዎች በታች ሆኜበታለው ብለህ አምነህ በተቀበልከው ነገርም ውስጥህ በሚሰማህ የዝቅተኝነት መንፈስ እየተሰቃየህ ነው፡፡ ያመንከው ጓደኛ ፍቅረኛ ወይም ዘመድ ፊታቸውን አዙረውብህ ፈጣሪ የተወኽ መስሎህም ዕረፍት ዐልባ ሆነህ ይሆናል፡፡

የትኛውም ዓይነት ችግር ከውጭ ቢከብህ ይኽን አስተውል∶− ባልተረጋጋህ ልክ ችግሮች እየከፉ ይሄዳሉ እንጂ አይቀሉም፡፡ አለመረጋጋት የተከሰተን ደስ የማያሰኝ ነገር ከድጡ ወደ ማጡ ይቀይራል፡፡ እንኳን የማታውቀውን የምታውቀውንም ያጠፋብሃል፡፡

ስትረጋጋ የችግሮች መፍትሔ የጥልፍልፎች ውል ወለል ብሎ ይታይሃል፡፡ ስትረጋጋ የተዘበራረቀው ሁሉ እንዴት ሊስተካከል እንደሚችል የምታይበት ዐይን የምታስተውልበትን ልቡና ታገኛለህ፡፡ ዛሬ በቤተሰብም በመንደርም በሀገርም እየተከሰተ ያለው ይኼ ሁሉ ትርምስ ምንጩ ምን ይመስልሃል? ተረጋግቶ ላይ ታች ፊት ኋላ ቀኝ ግራ የሚመለከት ስለጠፋ ነው፡፡

በእርግጥ እንዳትረጋጋ የሚያደርጉ ተንኳሽ አሳቦች፣ ያልተጠበቁ ክስተቶች፣ አስቸጋሪ ሰዎች ከየስፍራው ሊተኮሱና ሊገጥሙህ ይችላሉ፡፡ ቢሆንም ተረጋጋ!! እግዚአብሔርም ያረጋጋህ ዘንድ ተማጸነው። ካልተረጋጋህ ራስህን ብቻ ሳይሆን ዙሪያህ ያሉትን ሁሉ ታውካለህ፡፡ በመዋከብ የሚበተን እንጂ የሚሠበሠብ የሚሰበር እንጂ የሚጠገን የሚጎድል እንጂ የሚሞላ አንዳች የለም፡፡

ጌታችን ወደ ቤታቸው በገባ ጊዜ ሁለቱ እኅትማማች ማርያምና ማርታ ያደረጉትንና ጌታችንም የተናገረውን አስተውል፡፡ ጌታችን ወደ ቤታቸው ከገባበት ጊዜ አንሥቶ ማርታ ደፋ ቀና፤ ወጣ ገባ፤ ቁጭ ብድግ ማለት አብዝታ እጅጉን ባከነች፡፡ ማርያም ግን ተረጋግታ በመቀመጥ የጌታችንን የቃሉን ትምህርት በማድመጥ ጸናች፡፡ ማርታ የማርያም ተረጋግቶ በመቀመጥ ቃለ እግዚአብሔርን መስማት አልተዋጠላትምና "ጌታ ሆይ እኔ እንድሠራ እኅቴ ብቻዬን ስትተወኝ አይገድህምን " አለችው፡፡ ጌታችንም መልሶ "ማርታ ማርታ በብዙ ነገር ትጨነቂያለሽ ትታወኪማለሽ የሚያስፈልገው ግን ጥቂት ወይም አንድ ነገር ነው፡፡" አላት፡፡ (ሉቃ 10:40) ማርያም የምትሻውን ሁሉ ለማግኘት ተረጋጋች፤ ማርታ ግን ያላትንም ለመልቀቅና ላማጣት ባከነች፡፡ ወዳጄ ብትረጋጋ ጤናህ እስኪታወክ ደርሰህ ወዳጆችህንም እያስቀየምክ ቤተሰብህንም ጭምር ረስተህ የምትባክነው ለሚያስፈልግህ ሳይሆን ለፍላጎትህ መሆኑን ትረዳለህና ተረጋጋ፡፡

የድንግል ልጅ ቅዱስ አማኑኤል ፍጹም መረጋጋትን ያድለን!!

©️ መምህር ቢትወደድ ወርቁ
የካቲት 2 ቀን 2016 ዓ ም
የዝማሬ ሰዓት

https://tttttt.me/zdk24_5_21_official

👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆በዚህ ማስፈንጠሪያ ገብተው
" ወቅታዊ እና አዳዲስ ወረቦችን ዝማሬዎችን ከነግጥሞቻቸው እና የቤተክርስቲያናችንን ወቅታዊ ትምህርቶችን ያገኛሉ !!!!! "
ይቀላቀሉን!!!!!
ዐውደ ምሕረት pinned «https://youtu.be/mYyKRMQ987U?feature=shared»
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
መዝሙር
       የዋኅ መልአክ
የእግዚአብሔር መልአክ ቅዱስ ሚካኤል
ታዳጊያችን ነህ ምክሩ ለልዑል
የአምላክ ኀይሉ መገለጫው ነህ
የእልፍ አእላፍ መላእክት መስፍናቸው ነህ
አዝ.........
ለሠራዊተ ሰማይ መላእክት አለቃቸው
ለፍጥረቱ ለባሕር ለየብሱ አጽንኦታቸው
የዋኅ ርኅሩህኅ መልአክ ኀዳጌ በቀል
በልመናው በጸሎቱ ያስምረናል ቅዱስ ሚካኤል
አዝ...........
የእግዚአብሔር የምክሩ አበጋዝ ቅዱስ ሚካኤል
ለሰው ልጆች የምታዝን ምታማልድ ከልዑል
እነሆ ሕይወታችንን ባርክልን አደራህን
በኑሯችን ሁሉ ጠብቀን ባለን ዘመን
አዝ............
ሳለን በዓለም ዲያብሎስ እንዳይጥለን ጥንተ ጠላት
ድል አድራጊው ጠብቀን ሚካኤል ሆይ ሊቀ መላእክት
መካሬ ጽድቅ እውቀትን ሙላን ግለጥልን
በእምነት በተስፋ በፍቅር መኖርን

🛑 በዘማሪ ዳዊት ክብሩ /ዘምክሐ/ 🛑


ሙሉ ዝማሬውን በዚህ ተጭነው ይመልከቱት ይዘምሩ 👇👇👇
https://youtube.com/watch?v=mXiS3w0dARg&feature=share7
🛑አዲስ ዝማሬ🛑

"የፋርስ ኮከብ"

በዘማሪት ሰብለ ስፍር


በቅርብ ቀን ይጠብቁን !!!