Forwarded from የዘማሪ ዳዊት ክብሩ Zemari Dawit Kibru Official Telegram Channel
YouTube
🛑 አዲስ ዝማሬ "ተመስገን" | ዘማሪ ዲያቆን ዘለዓለም ታከለ (ዘጎላ) ◈ New Mezmur"Temesgen" D Zelalem Takele Zegola
#newmezmur #orthodox_mezmur #zemari_zelalem #zegola #Temesgen #like #share #subscribe #ተመስገን #temesgen_mezmur#አዲስ_ዓመት #new_year
+ሸክማችሁ የከበደ ወደ እኔ ኑ።+
እመን እንጂ አትፍራ አትሸበር አትጨነቅ! ዛሬ ላይ በኑሮህ ውስጥ ያሉ የህይወት ህዋሳቶች ላይ በሁለት እግርህ አልቆምክም ይሆናል። በዙሪያህ ያሉ ሰዎች የደረሱበትን የስኬት ማማ እየተመለከትህ ነው። የራስህን ስትመለከት ገና አንድ እርምጃ አልተራመድህም ነገር ግን እየለፋህ ነው እየጣርህ ነው በእግዚአብሔር ቤት አገልግሎት ላይ ነህም። ለጸሎት በቆምክ ጊዜ አምላክህን ልፋትህንና አገልግሎትህን ተመልክቶ ለምን ሌሎች ከደረሱበት ቦታ እንዳላደረሰህ አጥብቀህ ትጠይቀዋለህ። ሌሎች ፈጥኖ የደረሰ ላንተ እጅግ የዘገየ እና የራቀ ይመስልሃል በዚህም ትከፋለህ። በሌላ ጎን ዓለም ያለማቋረጥ የምትወነጭፈው ቀስት አድክሞሃል። ዘወትር ከአምላክህ ፊት ለጸሎት ለመቆምም ታክቶሃል። ታዲያ ዘላቂ መፍትሄ ማገኝተ እንዳለብህ ከዚህ ማጥ መውጣት እንዳለብህ ዘወትር ታስባለህ። መፍትሄው ከወዲህ አለልህ፦
፨ አንተ ክርስቲያን ነህ!
ቤተክርስቲያን እናትህ ናት አንተም ቤተክርስቲያን ነህ ፤ ቤተክርስቲያን በደሙ የዋጃት ክርስቶስ በልዕልና እስኪመጣ ድረስ መስቀል ላይ ናት። መስቀል መከራ ነው ክርስቶስ እንደተናገረ “ በኋላዬ ሊመጣ የሚወድ ቢኖር፥ ራሱን ይካድ መስቀሉንም ተሸክሞ ይከተለኝ።”ማር8፥34 ስለዚህ በምድር ሳለህ ከአንተ መከራ እንደማይለይ እመን። “በፍም ላይ የሚሄድ፥ እግሮቹስ የማይቃጠሉ ማን ነው?” ምሳሌ 6፥28 እንዲል መጸሐፍ ዓለም ላይ እየኖርህ መከራ ለምን መጣብኝ አትበል ይልቁንስ እንደ ሐዋርያው “ኃይልን በሚሰጠኝ በክርስቶስ ሁሉን እችላለሁ።”ፊልጵስዩስ 4፥13 በል እንጂ።
፨ ለሁሉም ጊዜ አለው ታገስ!
“ከሰማይ በታችም ለሆነ ነገር ሁሉ ጊዜ አለው።” መክ 3፥1 እንደተባለ እግዚአብሔር ለሁሉም ነገር መልስ አለው። እስራኤላውያን በባርነት ሳሉ ህግ አልተሰጣቸውም ቢሰጣቸው ኖሮ አይጠብቁትም። በባርነት ያለ ሰው የጌታውን ፈቃድ ከመፈጸም ውጪ የራሱን ፈቃድ መፈጸም አይችልምና። ነገር ግን ከባርነት ከወጡ በኋላ ህግ ተሰጣቸው። እግዚአብሔር ነገሮች ለአንተ መቼ እንደሚያስፈልጉህ ከአንተ በላይ ያውቃል።ነቢዩ እንዲህ አለ “ሰው ዝም ብሎ የእግዚአብሔርን ማዳን ተስፋ ቢያደርግ መልካም ነው።” ሰቆ. 3፥26 አዎ የእርሱን የቸርነት ስራ በነገሮች ተስፋ ሳትቆርጥ የእርሱን ቸርነት ተስፋ በማድረግ በዕምነት ልትጠብቀው ይገባል። ዮሴፍ ወልደ ያዕቆብ ሀብት ሹመት ያገኘው ገና እንደተወለደ አይደለም ፣ 12 ዓመት ደም ይፈሳት የነበረች ሴት ደሟ የቆመው ከ 12 ዓመት በኋላ ነው።
፨ በየጊዜው ወደ እግዚአብሔር ተመልከት!
ብላቴናው ቅዱስ ዳዊት ፍልስጤማዊው ጎልያድን የመሠለ ታላቅ መከራ በፊቱ በተደቀነ ጊዜ ምን አለ 1ኛ ሳሙኤል 17፥43 "ዳዊትም ፍልስጥኤማዊውን አለው፦ አንተ ሰይፍና ጦር ጭሬም ይዘህ ትመጣብኛለህ፤ እኔ ግን ዛሬ በተገዳደርኸው በእስራኤል ጭፍሮች አምላክ ስም በሠራዊት ጌታ በእግዚአብሔር ስም እመጣብሃለሁ።" አለው። ጎልያድን ሳይሆን እግዚአብሔርን መከራውን ሳይሆን የእስራኤል አምላክን ተመለከተ እርሱም አላሳፈረውም ጎልያድን በትንሿ መሣርያ ወንጭፍ ጥሎ ገደለው። አንተም ፊትህ ያለውን መከራ ፈተና ፣ ጭንቀት ፣ ተስፋ የሚያስቆርጥ ፣ ክፉ ነገር ገለል ችላ አድርገህ ኃያሉን እግዚአብሔር ተመልከት ይሰማህማል ከገጠመህ ችግርም ነፃ አውጥቶ እንደ ዳዊት የንግስና የስኬት ዙፋን ላይ ቀብቶ ያስቀምጥሃል። ከነቢዮ ሚክያስ ጋር እንዲህ በል "እኔ ግን ወደ እግዚአብሔር እመለከታለሁ፥ የመድኃኒቴንም አምላክ ተስፋ አደርጋለሁ፤ አምላኬም ይሰማኛል። ጠላቴ ሆይ፥ ብወድቅ እነሣለሁና፥ በጨለማም ብቀመጥ እግዚአብሔር ብርሃን ይሆንልኛልና በእኔ ላይ ደስ አይበልሽ።ት ሚክ 7፥7-8
፨+፨ ይህንን እያሰብህ በመረዳት እና በማስተዋል አዲሱን ዓመት ተቀበል በጭንቀት እና በድካም ያሳለፍከው አሮጌው አመት ይብቃህ ።ዳግም ታድሰህ ዕድሜ ለንስሃ ዘመን ለፍስሐ የሰጠህን እግዚአብሔርን አመስግን ፨+፨
ቡሩክ መልሳቸው
6/13/2015
አ.አ ኢትዮጵያ
+ሠናይ አዲስ ዓመት+

NEW_MEZMUR_''ተክለ_ሥላሴ_ነህ''_ዘማሪ_ሳሙኤል_ተክሌ_#teklehaymanot_#newmezmu…
<unknown>
🙏ተክለ ሥላሴ ነህ
ግጥም:-ተርቢኖስ ሰብስቤ
ዜማ:-ዘማሪ ሳሙኤል ተክሌ
ተክለ ሥላሴ ነህ ጸድቀህ ያፈራህ
በታላቅ ተጋድሎህ ሀገር ያቀናህ
ትውልድ ይህን አውቆ ስምህን ይጠራል
ተክለ ሃይማኖት[፫] ብሎ ዝክርህን ይዘክራል
አዝ >> >> >>
አባ ሰላማ ሆይ ሰላምህን ስጠን
ጠብን እየጫረ ጠላት አይለያየን
እግዚአብሔርን ተከሎሃል ፍሬ እንድታፈራ
ዛሬም አለምልመን በወንጌል አዝመራ
አዝ >> >> >>
ጻድቃን የበዙለት ሕዝብ ደስ ይለዋል
ሰላምና ፍቅር ተስፋ ይታየዋል
ሲሰለጥኑ ግን እኩያን ኃጥአን
ወገን ተቸግሮ ያጣል መጠለያን
አዝ >> >> >>
ከሥርሽ ተነቅለሽ ነይ በላት ዛፏን
ሰይጣን እያደረ ያሳተባትን
በአምልኮተ ጣዖት ሕዝብህ ጠፍቷልና
በወንጌል ፈልገው በሃይማኖት ፋና
አዝ >> >> >>
ባርከህ እንደቀየርከው ገብረ ዋኅድን
እኛንም ለውጠህ ጳውሎስ አድርገን
ሳዉልነት ይብቃን ልጅህ እንሁን
በምግባር ትሩፋት አንተን እንምሰል
የዘማሪ ሳሙኤል ተክሌ የዩቲዩብ ቻናል👇👇👇
👉Zemari Samuel Tekle Official👈
ሰብስክራይብና ላይክ በማድረግ እንዲሁም ለወዳጅዎ በማጋራት ቤተሰብ እንድንሆን እጋብዛለሁ❤️
ግጥም:-ተርቢኖስ ሰብስቤ
ዜማ:-ዘማሪ ሳሙኤል ተክሌ
ተክለ ሥላሴ ነህ ጸድቀህ ያፈራህ
በታላቅ ተጋድሎህ ሀገር ያቀናህ
ትውልድ ይህን አውቆ ስምህን ይጠራል
ተክለ ሃይማኖት[፫] ብሎ ዝክርህን ይዘክራል
አዝ >> >> >>
አባ ሰላማ ሆይ ሰላምህን ስጠን
ጠብን እየጫረ ጠላት አይለያየን
እግዚአብሔርን ተከሎሃል ፍሬ እንድታፈራ
ዛሬም አለምልመን በወንጌል አዝመራ
አዝ >> >> >>
ጻድቃን የበዙለት ሕዝብ ደስ ይለዋል
ሰላምና ፍቅር ተስፋ ይታየዋል
ሲሰለጥኑ ግን እኩያን ኃጥአን
ወገን ተቸግሮ ያጣል መጠለያን
አዝ >> >> >>
ከሥርሽ ተነቅለሽ ነይ በላት ዛፏን
ሰይጣን እያደረ ያሳተባትን
በአምልኮተ ጣዖት ሕዝብህ ጠፍቷልና
በወንጌል ፈልገው በሃይማኖት ፋና
አዝ >> >> >>
ባርከህ እንደቀየርከው ገብረ ዋኅድን
እኛንም ለውጠህ ጳውሎስ አድርገን
ሳዉልነት ይብቃን ልጅህ እንሁን
በምግባር ትሩፋት አንተን እንምሰል
የዘማሪ ሳሙኤል ተክሌ የዩቲዩብ ቻናል👇👇👇
👉Zemari Samuel Tekle Official👈
ሰብስክራይብና ላይክ በማድረግ እንዲሁም ለወዳጅዎ በማጋራት ቤተሰብ እንድንሆን እጋብዛለሁ❤️
Forwarded from የዘማሪ ዳዊት ክብሩ Zemari Dawit Kibru Official Telegram Channel
YouTube
የኪዳን ጸሎት መቅደም ትርጓሜ በአቡነ ሰላማ | Abune Selama | kidan tirguwame | ortodox tewhdo sibket 2023 | EOTC
አቡነ ሰላማ
የብፁዕ አቡነ ሰላማ አጭር የሕይወት ታሪክ
ዜና ህይወቱ ለብፁዕ አቡነ ሰላማ (የብፁዕ አቡነ ሰላማ አጭር የሕይወት ታሪክ)
ብፁዕ አቡነ ሰላማ ከአባታቸው ከአቶ ገብረ ሥላሴ ገ/መድኀንና ከእናታቸው ከወ/ሮ ብዙነሽ ወንድሙ በትግራይ ክፍለ ሀገር በመቀሌ ከተማ ልዩ ስሙ በዓታ ለማርያም በተባለው ፲፱፴፬ ዓ/ም ተወለዱ።
ዕድሜያቸው ለትምህርት ሲደርስ በትውልድ ሀገራቸው ንባብና የቃል ትምህርት በሚገባ…
የብፁዕ አቡነ ሰላማ አጭር የሕይወት ታሪክ
ዜና ህይወቱ ለብፁዕ አቡነ ሰላማ (የብፁዕ አቡነ ሰላማ አጭር የሕይወት ታሪክ)
ብፁዕ አቡነ ሰላማ ከአባታቸው ከአቶ ገብረ ሥላሴ ገ/መድኀንና ከእናታቸው ከወ/ሮ ብዙነሽ ወንድሙ በትግራይ ክፍለ ሀገር በመቀሌ ከተማ ልዩ ስሙ በዓታ ለማርያም በተባለው ፲፱፴፬ ዓ/ም ተወለዱ።
ዕድሜያቸው ለትምህርት ሲደርስ በትውልድ ሀገራቸው ንባብና የቃል ትምህርት በሚገባ…
Forwarded from የዘማሪ ዳዊት ክብሩ Zemari Dawit Kibru Official Telegram Channel
+++ ስሙንም አማኑኤል ትለዋለች! +++
“ስለዚህ ጌታ ራሱ ምልክት ይሰጣችኋል፤ እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች፥ ወንድ ልጅም ትወልዳለች፥ ስሙንም አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች።” (ኢሳ7፥14)
አማኑኤል "እግዚአብሔር ምስሌነ - እግዚአብሔር ከኛ ጋር ሆነ" የሚል ትርጉም እንዳለው መልአኩ ለቅዱስ ዮሴፍ ነግሮታል፡፡
+ እግዚአብሔር ከኛ ጋር ሆነ ማለት ምን ማለት ነው ? +
እግዚአብሔር ከፍጥረቱ ተለይቶ አያውቅም ሁልጊዜም በረድኤት በቸርነት በጠብቆት በመግቦት ከፍጥረቱ ጋር ነበረ አሁንም አለ፡፡ ልበ አምላክ ክቡር ዳዊት በመዝሙሩ "እግዚአብሔር ከኛ ጋር ባይሆን እስራኤል እንዲህ ይበል እግዚአብሔር ከኛ ጋር ባይሆን ጠላቶቻችን በተነሡብን ጊዜ አለን አለን ስንል እንደ ጥህሎ በዋጡን እንደ እንቅትም በጠጡን ነበር።'' ብሎ መዘመሩ እግዚአብሔር ከፍጥረቱ ፍጹም እንደማይለይ ያስረዳናል፡፡ ታዲያ እግዚአብሔር ከኛ ጋር ሆነ የሚለው አማኑኤል የሚለው ስም ትርጉም ምን ያሳየናል? ቢሉ አካላዊ ቃል ከሥጋችን ሥጋ ከነፍሳችን ነፍስን ነሥቶ ከኛ ጋር በተዋሕዶ አንድ መሆኑን በኩነተ ሥጋ (ሰው በመሆን) መገለጡን ያስረዳናል፡፡ (መዝ 123:1-3፣ ኤፌ 2:14-16) ቅዱስ ዮሐንስ "ቃል ሥጋ ሆነ ጸጋንና እውነትን ተመልቶ በኛ አደረ አንድ ልጅም በአባቱ ዘንድ እንዳለው ክብር ክብሩን አየን፡፡" ማለቱሞ ለዚህ ነው፡፡ (ዮሐ 1:14-15)
እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምም መለኮት ከኛ ጋር የሆነባት ታላቅ ምሥጢር የተገለጠባት የአካላዊ ቃል መዲና መገለጫ ናት፡፡ እግዚአብሔር ወልድ ኢየሱስ ክርስቶስ ከእርሷ ተወልዶ ከኛ ጋር ሆነ በዓይናችን አየነው እጆቻችንም ዳሰሱት ከኛም ጋር ተመላለሰ። በዚህም "አምላክ የለም" የሚሉ ሰነፎች ስንፍናቸው ምክንያትን አጣ፡፡ ሥጋ ለባሽ ሁሉ የእርሱን ክብር አይቷልና። (1ዮሐ 1:1-3፣ ኢሳ 40:1-5)
ከኛ ጋር ሆኖ የቁስአካላውያንን (Materialists) ክሕደት ስላጠፋም "ማንም ሰው ያላደረገውን ተአምራት ባላደርግ ኃጢአት ባልሆነባቸው ነበረ አሁን ግን እኔንም አባቴንም አይተውማል ጠልተውማል፡፡" በማለት ተናገረ:: (ዮሐ15:24) ቅዱስ አማኑኤል ፈጣሪያችን ሀገራችንን ከጥፋት ይጠብቅልን!!!
መምህር ቢትወደድ ወርቁ
መስከረም 28 ቀን 2016 ዓ ም

Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
🛑አዲስ ዝማሬ🛑 " ታቦተ ሥላሴ "
በዘማሪ ክብሮም ግደይ /ዘደብረ አሚን/
😲😲😲 በቅርብ ቀን ይጠብቁን❕❕❕😲😲😲
በዘማሪ ክብሮም ግደይ /ዘደብረ አሚን/
😲😲😲 በቅርብ ቀን ይጠብቁን❕❕❕😲😲😲
Forwarded from የዘማሪ ዳዊት ክብሩ Zemari Dawit Kibru Official Telegram Channel
✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝
“ስለ እናንተ ሲያማልዱ፥ በእናንተ ላይ ከሚሆነው ከሚበልጠው ከእግዚአብሔር ጸጋ የተነሣ ይናፍቁአችኋል።” (ቅዱስ ጳውሎስ 2ኛ ቆሮ 9፥14)
--------------------------------
☞ ጻድቃን "አያማልዱም" የሚለውን ክርክር ተወውና የዘፍጥረትን መጽሐፍ ገልጠህ ፈጣሪህን ጠይቅ። ደጋጎች አይደለም ማልደው ለጥፋት በተዘጋጀች ከተማ ቢኖሩ እንኳን በከተማይቱ ስለመኖራቸው ብሎ ምሕረትን ያወርዳል።
☞ እግዚአብሔር ሰዶምና ገሞራን በኃጢአታቸው ምክንያት በእሳትና በዲን አቃጥሎ ከመቅጣቱ አስቀድሞ ለወዳጁ ለአብርሃም "እኔ የማደርገውን ከአብርሃም እሰውራለሁን? አብርሃም በእውነት ታላቅና ብርቱ ሕዝብ ይሆናልና፥ የምድር አሕዛብም ሁሉ በእርሱ ይባረካሉና። ጽድቅንና ፍርድን በማድረግ የእግዚአብሔርን መንገድ ይጠብቁ ዘንድ ልጆቹንና ከእርሱ በኋላ ቤቱን እንዲያዝዝ አውቃለሁና፤ ይህም እግዚአብሔር በአብርሃም ላይ የተናገረውን ነገር ሁሉ ያመጣ ዘንድ ነው።" ካለ በኋላ "የሰዶምና የገሞራ ጩኸት እጅግ በዝቶአልና፥ ኃጢአታቸውም እጅግ ከብዳለችና፥ እንግዲህስ ወደ እኔ እንደ መጣች እንደ ጩኸትዋ አድርገው እንደ ሆነ ወርጄ አያለሁ፤ እንዲሁም ባይሆን አውቃለሁ።" በማለት ነገረው። ይህ ነገር በእግዚአብሔር የተነገረው አብርሃም ደጋግሞ ምን ብሎ እንደጸለየ ታስተውላለህን? "አምሳ ጻድቃን በከተማይቱ ውስጥ ቢገኙ በውኑ ሁሉን ታጠፋለህን? ከተማይቱንስ በእርስዋ ስለሚገኙ አምሳ ጻድቃን አትምርምን?"….... ዳግመኛም "ከአምሳው ጻድቃን አምስት ቢጐድሉ ከተማይቱን ሁሉ በአምስቱ ምክንያት ታጠፋለህን? "… ሦስተኛም "ጌታዬ አይቆጣ እኔም እናገራለሁ፤ ምናልባት ከዚያ ሠላሳ ቢገኙሳ?… አራተኛም፦ "እኔ ደግሞ አንድ ጊዜ ብቻ ብናገር ጌታዬ አይቆጣ፤ ምናልባት ከዚያ አሥር ቢገኙሳ?" አለ።" ቅዱሱ ሰው አብርሃም በመጨረሻ የጸለየውን ጸሎት ልብ በል "በእነዚህ በሁለት ታላላቅ ከተሞች አሥር ጻድቃንን ብታገኝ አትምርምን?" የሚል ነው። እግዚአብሔር ምን ብሎ የመለሰ ይመስልሃል? "አምሳ ሳይሆን አሥርም ጻድቃን ባገኝ እምራለሁ!!!" (ዘፍ 18:17-25)
☞ እስቲ ልጠይቅህ ዛሬ ግብረ ሰዶማዊነት የት ደርሶዋል? በደጅህ አልደረሰምን? ለቀደሙት ስለገባው ቃልኪዳን ታግሦዋል እንጂ ሰዶማውያኑ በጠፉበት ግብረ ሰዶም ዓለሙ ይጠፋ እንደነበር የታወቀ ነው። ጠቢቡ ሰሎሞን “ጻድቃን በበዙ ጊዜ ሕዝብ ደስ ይለዋል።” (ምሳ 29፥2) ብሎ ለምን ተናገረ? በጻድቃን ብዛት ሀገር እንደምትድን በተረዳ ነገር ስላወቀ አይደለምን?
☞ የጻድቃን ልመና ብቻ ሳይሆን መኖር እንኳን ከጥፋት ይታደግሃል። ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ “እነዚያ ቀኖችስ ባያጥሩ ሥጋ የለበሰ ሁሉ ባልዳነም ነበር፤ ነገር ግን እነዚያ ቀኖች ስለ ተመረጡት ሰዎች ያጥራሉ።” ብሎ በምሥጢረ ምጽዓት ትምህርቱ እንዳስተማረ። (ማቴ 24፥22) እግዚአብሔር ለወዳጆቹ በሚገባው ቃልኪዳን ቁጣውን በምሕረት በትእግሥት እንደሚለውጥ መከራውን እንደሚያሳጥር ይህ የጌታ ቃል ምስክር ነው። ዓለም አልገባውም እንጂ ሐሳዊ መሲሕ የሚሠለጥንባቸው እነዚያ አስጨናቂ ወራት እንኳን የሚያጥሩት በጽኑ እምነታቸው በቀና ምግባራቸው እርሱን ላስደሰቱት ወዳጆቹ በገባው ቃልኪዳን ነው።
መድኅን ዓለም ክርስቶስ ሕያዋን ቅዱሳኑን "ሙታን" ለሚሉ ሰዱቃውያን “እኔ የአብርሃም አምላክ፥ የይስሐቅም አምላክ የያዕቆብም አምላክ ነኝ የሚል ከእግዚአብሔር ዘንድ ወደ እናንተ የተባለውን አላነበባችሁምን? የሕያዋን አምላክ ነው እንጂ የሙታን አይደለም።” ብሎ የተናገረውን ቃል ልብ በልና ሙታን እንደሌሉን አውቀህ ወደ ሕይወት የተሻገሩበትን የዕረፍታቸውን ቀን እንደ ዳዊት “የቅዱሳኑ ሞት በእግዚአብሔር ፊት የከበረ ነው።” (መዝ116፥15) እያልክ እየዘመርክ አክብር። (ማቴ 22፥31-32)
እባክዎን ቃለ እግዚአብሔርን በማጋራት ለወዳጆችዎ ያድርሱ።
መምህር ቢትወደድ ወርቁ
ጥቅምት 05 ቀን 2016 ዓ ም

++ አንበሳውንና ዘንዶውን ትረግጣለህ! ++ (መዝ 91:13)
☞ ሞተ ሥጋ ሳያገኛቸው እግዚአብሔር የሠወራቸው ብዙ ቅዱሳን አሉ። ከነዚህም መካከል ከአዳም ጀምሮ ሰባተኛ የሆነ ሄኖክ አንዱ ነው። መጽሐፍ ቅዱሱ ሰው ሄኖክ ሞት ሳያገኘው የተሰወረበትን ምክንያት ሲገልጽ “ሄኖክም አካሄዱን ከእግዚአብሔር ጋር ስላደረገ አልተገኘም፤ እግዚአብሔር ወስዶታልና።” ይላል አካሄድን ከእግዚአብሔር ጋር ማድረግ እስከምን እንደሚያደርስ ተመልከት። (ዘፍ 5፥24) አካሄዳቸውን ከእርሱ ጋር ባደረጉ ወዳጆቹ ቅዱሳን የእግዚአብሔር ቸርነትና ከኃሊነት ተገልጦአልና ነቢዩ “እግዚአብሔር በጻድቁ እንደ ተገለጠ እወቁ።” በማለት ተናገረ። (መዝ 4፥3) በቅዱስ ሰው ሃይማኖት፣ በጎ ምግባርና መልካምነት ኢየሱስ ክርስቶስ ይገለጣል እንጂ አይሸፈንም።
☞ ከቅዱሱ ሰው ከሄኖክ ሌላ ቀናተኛው ነቢዩ ኤልያስም ሞት ሳያገኘው በእሳት ሠረገላ ወደ ሰማይ ተነጥቆዋል። ይህንም መጽሐፍ ሲነግረን “ሲሄዱም፦ እያዘገሙም ሲጫወቱ፥ እነሆ፥ የእሳት ሰረገላና የእሳት ፈረሶች በመካከላቸው ገብተው ከፈሉአቸው፤ ኤልያስም በዐውሎ ነፋስ ወደ ሰማይ ወጣ።” ከነቢዩ ጋር የነበረ ይህን የተመለከተና ለእግዚአብሔር የተገዛ ኤልሳዕም የነቢዩ ኤልያስ በረከት አድሮበት ተመሷል። (2ኛ ነገ 2፥11) መጽሐፍ በቅድስናቸው ለዚህ የበቁ እንዳሉ ሲነግርህ ዕፁብ ድንቅ ብለህ ማመን ማሰብም አንተንም ለክብር ያበቃሃል። ክርስቶስን በእነርሱ ሕይወት ትመለከተዋለህ እንጂ አይሠወርብህም። እንዲያም ባይሆን “የእግዚአብሔርን ቃል የተናገሩአችሁን ዋኖቻችሁን አስቡ፥ የኑሮአቸውንም ፍሬ እየተመለከታችሁ በእምነታቸው ምሰሉአቸው።” ባላለህም ነበር። (ዕብ 13፥7)
👇ይቀጥላል 👇
https://tttttt.me/zdk24_5_21_official

---የቀጠለ---
☞ ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ከደቀመዛሙርቱ መካከል ወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስ የሥጋ ሞት እንደማያገኘው ደጋግሞ ፍንጭ ሰጥቶ ነበር። በዚህም ቃሉ መሠረት ወንጌላዊው እንደተሠወረ የቤተክርስቲያን ታሪክ ይመሰክራል። (ማቴ 16:28፣ ዮሐ 21:23)
☞በዚህ መልኩ የተሠወሩ ቅዱሳን እነዚህ ብቻ ናቸው ማለት አይደለም። እግዚአብሔር የዘመናት ባለቤት ነውና በየዘመኑ እንዲህ አይነቱን የቸርነቱን ሥራ የሚሠራላቸው የሠራላቸውም ብዙ ወዳጆቹ አሉ። ከእነዚህም ወዳጆቹ በመለካውያን ተሰደው ወደ ኢትዮጵያ ምድር መጥተው የነበሩት ጻድቁ አቡነ አረጋዊ አንዱ ናቸው። እንደ ሄኖክ አካሄዳቸውን ከእግዚአብሔር ጋር አድርገዋልና እግዚአብሔር ከሞተ ሥጋ ሰውሮ ወስዷቸዋል። ጻድቁ አቡነ አረጋዊ አምላካችን እግዚአብሔር "በተኵላና በእባብ ላይ ትጫማለህ፤ አንበሳውንና ዘንዶውን ትረግጣለህ። በእኔ ተማምኖአልና አስጥለዋለሁ፤ ስሜንም አውቆአልና እጋርደዋለሁ።" በማለት አስቀድሞ የተናገረው ቃል እንዲሁም በኋለኛው ዘመን ጌታችን “ያመኑትንም እነዚህ ምልክቶች ይከተሉአቸዋል፤....... እባቦችን ይይዛሉ፥” ብሎ የተናገረው ቃል በተግባር የተፈጸመባቸውና የተፈጸመላቸው ጻድቅ ናቸው። (ማር16፥17፣ መዝ 90:13) ልዑል አምላክ ክርስቶስ ከወዳጆቹ የምንደመርበትን መልካም ሥራ ለመሥራት ያብቃን!!
ቢትወደድ ወርቁ
ጥቅምት 14 ቀን 2016 ዓ ም