ዐውደ ምሕረት
3.67K subscribers
932 photos
24 videos
271 files
195 links
"ቤተ ክርስቲያን ባሕረ ጥበባት
አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት"
Download Telegram
የመዘምራን አለቃ መንፈስ ቅዱስ ወደ እርሱ በመጣ ጊዜ የዘመረው #የዳዊት_መዝሙር

ተዛማች ጥቅስ #መዝ 50÷1
#እንኳን_አደረሳችሁ !

#መልካም_ማዕዶት

ያሻግራል ያልነው እያሰማመጠን
ሙሴና ፈርዖንን መለየት አቃተን

#መልካም ሽግግር #ለእናት_ኢትዮጵያ
+ሸክማችሁ የከበደ ወደ እኔ ኑ።+

እመን እንጂ አትፍራ አትሸበር አትጨነቅ! ዛሬ ላይ በኑሮህ ውስጥ ያሉ የህይወት ህዋሳቶች ላይ በሁለት እግርህ አልቆምክም ይሆናል። በዙሪያህ ያሉ ሰዎች የደረሱበትን የስኬት ማማ እየተመለከትህ ነው። የራስህን ስትመለከት ገና አንድ እርምጃ አልተራመድህም ነገር ግን እየለፋህ ነው እየጣርህ ነው በእግዚአብሔር ቤት አገልግሎት ላይ ነህም። ለጸሎት በቆምክ ጊዜ አምላክህን ልፋትህንና አገልግሎትህን ተመልክቶ ለምን ሌሎች ከደረሱበት ቦታ እንዳላደረሰህ አጥብቀህ ትጠይቀዋለህ። ሌሎች ፈጥኖ የደረሰ ላንተ እጅግ የዘገየ እና የራቀ ይመስልሃል በዚህም ትከፋለህ። በሌላ ጎን ዓለም ያለማቋረጥ የምትወነጭፈው ቀስት አድክሞሃል። ዘወትር ከአምላክህ ፊት ለጸሎት ለመቆምም ታክቶሃል። ታዲያ ዘላቂ መፍትሄ ማገኝተ እንዳለብህ ከዚህ ማጥ መውጣት እንዳለብህ ዘወትር ታስባለህ። መፍትሄው ከወዲህ አለልህ፦

፨ አንተ ክርስቲያን ነህ!
ቤተክርስቲያን እናትህ ናት አንተም ቤተክርስቲያን ነህ ፤ ቤተክርስቲያን በደሙ የዋጃት ክርስቶስ በልዕልና እስኪመጣ ድረስ መስቀል ላይ ናት። መስቀል መከራ ነው ክርስቶስ እንደተናገረ “ በኋላዬ ሊመጣ የሚወድ ቢኖር፥ ራሱን ይካድ መስቀሉንም ተሸክሞ ይከተለኝ።”ማር8፥34 ስለዚህ በምድር ሳለህ ከአንተ መከራ እንደማይለይ እመን። “በፍም ላይ የሚሄድ፥ እግሮቹስ የማይቃጠሉ ማን ነው?” ምሳሌ 6፥28 እንዲል መጸሐፍ ዓለም ላይ እየኖርህ መከራ ለምን መጣብኝ አትበል ይልቁንስ እንደ ሐዋርያው “ኃይልን በሚሰጠኝ በክርስቶስ ሁሉን እችላለሁ።”ፊልጵስዩስ 4፥13 በል እንጂ።

፨ ለሁሉም ጊዜ አለው ታገስ!
“ከሰማይ በታችም ለሆነ ነገር ሁሉ ጊዜ አለው።” መክ 3፥1 እንደተባለ እግዚአብሔር ለሁሉም ነገር መልስ አለው። እስራኤላውያን በባርነት ሳሉ ህግ አልተሰጣቸውም ቢሰጣቸው ኖሮ አይጠብቁትም። በባርነት ያለ ሰው የጌታውን ፈቃድ ከመፈጸም ውጪ የራሱን ፈቃድ መፈጸም አይችልምና። ነገር ግን ከባርነት ከወጡ በኋላ ህግ ተሰጣቸው። እግዚአብሔር ነገሮች ለአንተ መቼ እንደሚያስፈልጉህ ከአንተ በላይ ያውቃል።ነቢዩ እንዲህ አለ “ሰው ዝም ብሎ የእግዚአብሔርን ማዳን ተስፋ ቢያደርግ መልካም ነው።” ሰቆ. 3፥26 አዎ የእርሱን የቸርነት ስራ በነገሮች ተስፋ ሳትቆርጥ የእርሱን ቸርነት ተስፋ በማድረግ በዕምነት ልትጠብቀው ይገባል። ዮሴፍ ወልደ ያዕቆብ ሀብት ሹመት ያገኘው ገና እንደተወለደ አይደለም ፣ 12 ዓመት ደም ይፈሳት የነበረች ሴት ደሟ የቆመው ከ 12 ዓመት በኋላ ነው።

፨ በየጊዜው ወደ እግዚአብሔር ተመልከት!
ብላቴናው ቅዱስ ዳዊት ፍልስጤማዊው ጎልያድን የመሠለ ታላቅ መከራ በፊቱ በተደቀነ ጊዜ ምን አለ 1ኛ ሳሙኤል 17፥43 "ዳዊትም ፍልስጥኤማዊውን አለው፦ አንተ ሰይፍና ጦር ጭሬም ይዘህ ትመጣብኛለህ፤ እኔ ግን ዛሬ በተገዳደርኸው በእስራኤል ጭፍሮች አምላክ ስም በሠራዊት ጌታ በእግዚአብሔር ስም እመጣብሃለሁ።" አለው። ጎልያድን ሳይሆን እግዚአብሔርን መከራውን ሳይሆን የእስራኤል አምላክን ተመለከተ እርሱም አላሳፈረውም ጎልያድን በትንሿ መሣርያ ወንጭፍ ጥሎ ገደለው። አንተም ፊትህ ያለውን መከራ ፈተና ፣ ጭንቀት ፣ ተስፋ የሚያስቆርጥ ፣ ክፉ ነገር ገለል ችላ አድርገህ ኃያሉን እግዚአብሔር ተመልከት ይሰማህማል ከገጠመህ ችግርም ነፃ አውጥቶ እንደ ዳዊት የንግስና የስኬት ዙፋን ላይ ቀብቶ ያስቀምጥሃል። ከነቢዮ ሚክያስ ጋር እንዲህ በል "እኔ ግን ወደ እግዚአብሔር እመለከታለሁ፥ የመድኃኒቴንም አምላክ ተስፋ አደርጋለሁ፤ አምላኬም ይሰማኛል። ጠላቴ ሆይ፥ ብወድቅ እነሣለሁና፥ በጨለማም ብቀመጥ እግዚአብሔር ብርሃን ይሆንልኛልና በእኔ ላይ ደስ አይበልሽ።ት ሚክ 7፥7-8
፨+፨ ይህንን እያሰብህ በመረዳት እና በማስተዋል አዲሱን ዓመት ተቀበል በጭንቀት እና በድካም ያሳለፍከው አሮጌው አመት ይብቃህ ።ዳግም ታድሰህ ዕድሜ ለንስሃ ዘመን ለፍስሐ የሰጠህን እግዚአብሔርን አመስግን ፨+፨

ቡሩክ መልሳቸው
6/13/2015
አ.አ ኢትዮጵያ
+ሠናይ አዲስ ዓመት+
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
NEW_MEZMUR_''ተክለ_ሥላሴ_ነህ''_ዘማሪ_ሳሙኤል_ተክሌ_#teklehaymanot_#newmezmu…
<unknown>
🙏ተክለ ሥላሴ ነህ

ግጥም:-ተርቢኖስ ሰብስቤ
ዜማ:-ዘማሪ ሳሙኤል ተክሌ

ተክለ ሥላሴ ነህ ጸድቀህ ያፈራህ
በታላቅ ተጋድሎህ ሀገር ያቀናህ
ትውልድ ይህን አውቆ ስምህን ይጠራል
ተክለ ሃይማኖት[፫] ብሎ ዝክርህን ይዘክራል
አዝ    >>        >>        >>
አባ ሰላማ ሆይ ሰላምህን ስጠን
ጠብን እየጫረ ጠላት አይለያየን
እግዚአብሔርን ተከሎሃል ፍሬ እንድታፈራ
ዛሬም አለምልመን በወንጌል አዝመራ
አዝ    >>        >>        >>
ጻድቃን የበዙለት ሕዝብ ደስ ይለዋል
ሰላምና ፍቅር ተስፋ  ይታየዋል
ሲሰለጥኑ ግን  እኩያን ኃጥአን
ወገን ተቸግሮ ያጣል መጠለያን
አዝ   >>       >>        >>
ከሥርሽ ተነቅለሽ ነይ በላት ዛፏን
ሰይጣን እያደረ  ያሳተባትን
በአምልኮተ ጣዖት ሕዝብህ ጠፍቷልና
በወንጌል ፈልገው በሃይማኖት ፋና
አዝ    >>        >>        >>
ባርከህ እንደቀየርከው ገብረ ዋኅድን
እኛንም ለውጠህ ጳውሎስ አድርገን
ሳዉልነት ይብቃን ልጅህ እንሁን
በምግባር ትሩፋት አንተን እንምሰል

የዘማሪ ሳሙኤል ተክሌ የዩቲዩብ ቻናል👇👇👇
👉Zemari Samuel Tekle Official👈
ሰብስክራይብና ላይክ በማድረግ እንዲሁም ለወዳጅዎ በማጋራት ቤተሰብ እንድንሆን እጋብዛለሁ❤️
+++ ስሙንም አማኑኤል ትለዋለች! +++

“ስለዚህ ጌታ ራሱ ምልክት ይሰጣችኋል፤ እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች፥ ወንድ ልጅም ትወልዳለች፥ ስሙንም አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች።” (ኢሳ7፥14)

አማኑኤል "እግዚአብሔር ምስሌነ - እግዚአብሔር ከኛ ጋር ሆነ" የሚል ትርጉም እንዳለው መልአኩ ለቅዱስ ዮሴፍ ነግሮታል፡፡

+ እግዚአብሔር ከኛ ጋር ሆነ ማለት ምን ማለት ነው ? +

እግዚአብሔር ከፍጥረቱ ተለይቶ አያውቅም ሁልጊዜም በረድኤት በቸርነት በጠብቆት በመግቦት ከፍጥረቱ ጋር ነበረ አሁንም አለ፡፡ ልበ አምላክ ክቡር ዳዊት በመዝሙሩ "እግዚአብሔር ከኛ ጋር ባይሆን እስራኤል እንዲህ ይበል እግዚአብሔር ከኛ ጋር ባይሆን ጠላቶቻችን በተነሡብን ጊዜ አለን አለን ስንል እንደ ጥህሎ በዋጡን እንደ እንቅትም በጠጡን ነበር።'' ብሎ መዘመሩ እግዚአብሔር ከፍጥረቱ ፍጹም እንደማይለይ ያስረዳናል፡፡ ታዲያ እግዚአብሔር ከኛ ጋር ሆነ የሚለው አማኑኤል የሚለው ስም ትርጉም ምን ያሳየናል? ቢሉ አካላዊ ቃል ከሥጋችን ሥጋ ከነፍሳችን ነፍስን ነሥቶ ከኛ ጋር በተዋሕዶ አንድ መሆኑን በኩነተ ሥጋ (ሰው በመሆን) መገለጡን ያስረዳናል፡፡ (መዝ 123:1-3፣ ኤፌ 2:14-16) ቅዱስ ዮሐንስ "ቃል ሥጋ ሆነ ጸጋንና እውነትን ተመልቶ በኛ አደረ አንድ ልጅም በአባቱ ዘንድ እንዳለው ክብር ክብሩን አየን፡፡" ማለቱሞ ለዚህ ነው፡፡ (ዮሐ 1:14-15)

እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምም መለኮት ከኛ ጋር የሆነባት ታላቅ ምሥጢር የተገለጠባት የአካላዊ ቃል መዲና መገለጫ ናት፡፡ እግዚአብሔር ወልድ ኢየሱስ ክርስቶስ ከእርሷ ተወልዶ ከኛ ጋር ሆነ በዓይናችን አየነው እጆቻችንም ዳሰሱት ከኛም ጋር ተመላለሰ። በዚህም "አምላክ የለም" የሚሉ ሰነፎች ስንፍናቸው ምክንያትን አጣ፡፡ ሥጋ ለባሽ ሁሉ የእርሱን ክብር አይቷልና። (1ዮሐ 1:1-3፣ ኢሳ 40:1-5)

ከኛ ጋር ሆኖ የቁስአካላውያንን (Materialists) ክሕደት ስላጠፋም "ማንም ሰው ያላደረገውን ተአምራት ባላደርግ ኃጢአት ባልሆነባቸው ነበረ አሁን ግን እኔንም አባቴንም አይተውማል ጠልተውማል፡፡" በማለት ተናገረ:: (ዮሐ15:24) ቅዱስ አማኑኤል ፈጣሪያችን ሀገራችንን ከጥፋት ይጠብቅልን!!!

መምህር ቢትወደድ ወርቁ
መስከረም 28 ቀን 2016 ዓ ም
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
🛑አዲስ ዝማሬ🛑 " ታቦተ ሥላሴ "
በዘማሪ ክብሮም ግደይ /ዘደብረ አሚን/
😲😲😲 በቅርብ ቀን ይጠብቁን😲😲😲
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#ጥቅምት 4 ቀን ይጠብቁን 🙏 !
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
#በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሠረተ #ወቅታዊና ድንቅ መንፈሳዊ ጭውውት

#ደጅሽ ላይ ቆሟል !