ዐውደ ምሕረት
3.69K subscribers
930 photos
24 videos
271 files
193 links
"ቤተ ክርስቲያን ባሕረ ጥበባት
አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት"
Download Telegram
#በእግዚአብሔር ፊት የምቆም ገብርኤል ነኝ ሉቃ ፩÷፲፱

ቅዱስ ገብርኤል በኦርቶዶክሳውያን ምእመናን ዘንድ ከፍ ያለ መወደድ ያለው መልአክ ነው::ኦርቶዶክሳውያን የክርስቶስ የሆነ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ገብርኤልን አብዝተን የምንወድበት ብዙ ምክንያቶች አሉን

፩. ቤተሰብኡን የሚጠላ ማን አለ ?

ክርስቲያኖች ከቅዱሳን መላእክት ጋር የአንድ ቤተሰብእ ሀገር አባላት አካላት ነን:: በሐዋ ፱÷፲፭ መምህረ አሕዛብ ብርሃነ ዓለም ተብሎ የተመሠከረለት ቅዱስ ጳውሎስ "እናንተ ከቅዱሳን ጋር ባላገሮችና (ባለሀገሮችና) ቤተሰቦች ናችሁ እንጂ እንግዶችና መጻተኞች አይደላችሁም" እንዳለ ኤፌ ፪:፲፱:: ሐዋርያው በዚህ ክፍል ቅዱሳን ከተባሉ መላእክት ጋር ቤተሰብእ እንደሆንን ነገረን ሀገራችንም አንድ መሆኑን ሲመሠክር "ከእነርሱ ጋር ባለሀገሮች ናችሁ " አለን:: ሀገራችን የት ነው ? ብለን ብንጠይቅም ራሱ በፊልጵዩስ መልእክቱ "ሀገራችን በሰማይ ነው" ብሎናል ፊልጵ ፫፥፲፰-፲፱ ::የመላእክት ሀገር መንግሥተ ሰማይ እንደሆነ የእኛም ሀገር በሰማይ ነው::ሐዋርያው "እንግዶችና መጻተኞች አይደላችሁም" ያለው ቅዱስ ጴጥሮስ "እንግዶችና መጻተኞች ናችሁ" ፩ጴጥ ፪:፲፩ ብሎ በዚህ ኃላፊ ዓለም እንግዶች መሆናችንን የገለጠበትን የዚህ ዓለም እንግዳነታችንንና መጻተኛነታችንን ሳይሆን በሰማይ መንግሥት እንግዶች አለመሆናችንን ለመግለጥ ነው:: ይህ ዓለም ቢበዛ 70 ቢበረታም 80 ዘመን ብቻ የምንኖርበት ጊዜያዊ መኖሪያችን ነው መዝ 89÷10 ::ቅዱሳን መላእክት ቤተሰቦቻችን (እንደ ወንድም አባት እናት እህት) ስለሆኑ በአንዳችን የልብ ንስሐና መመለስ እንኳን ተደስተው በሰማይ ሀሴትን ያደርጋሉ ይዘምራሉ ያሸበሽባሉም :: ይህም የጌታችን በሥጋዌው ወራት ምሥክርነት ነበር ሉቃ ፲፭:፲::ቅዱሳን መላእክት ከምእመናን የማይለዩ እንደ እውነተኛ ወንድም አሳቢ እንደ አባት ጠባቂና ከክፉ የሚያድኑ አገልጋዮችም ናቸው:: መዝ 90÷11 ዳን 4÷12 የሐዋ 12÷5 የሐዋ 27÷23

2. ቅዱስ ገብርኤል መምህራችንም ነው

ቅዱስ ገብርኤል በቅዱሳት መጻሕፍት ከተገለጡልን ሥራዎቹ አንዱ የቅዱሳን ነቢያት እንዲሁም ምእመናን አስተማሪ መካሪ ጥበብ ገላጭ መሆኑ ነው :: እስከ ምጽአተ ክርስቶስ ሊሆን ያለውን ነገር በምልአት በስፋት የተናገረ ነቢዩ ዳንኤል "ገብርኤል ወደ እኔ እየበረረ መጣ በማታም በመሥዋእት ጊዜ ተናገረኝ አስተማረኝም እንዲህም አለኝ ዳንኤል ሆይ ጥበብና ማስተዋልን እሰጥህ ዘንድ አሁን መጥቻለሁ" ዳን 9:22 እንዳለ :: ቅዱስ ገብርኤል ምሥጢርን ጥበብን የመግለጥ ጸጋ ሀብት እንደተሰጠው ትመለከታላችሁን ? ዛሬ ላለን ምእመናን የክርስቶስ እናቱ እመቤታችንን "ጸጋን የሞላብሽ ሆይ ደስ ይበልሽ" እያልን እናመሰግናት ዘንድ ያስተማረን እርሱ አይደለምን ? ሉቃ 1:26-40 :: "በገብርኤል ሰላምታ ሰላም እንልሻለን" ማለታችንም ለዚሁ ነው::

3 . አረጋጊ አጽናኝ ፍርሃትንም የሚያርቅ መልአክ ነው

አንዱ የቅዱስ ገብርኤል ሥራ ፍርሃትን ማራቅ የታወኩትንም ማረጋጋት ነው :: ስለሆነም ወደ ሰዎች በመጣ ጊዜ "አትፍሩ" እያለ ያረጋጋቸዋል :: እንኮዋ በዚህ ዓለም ሀሳብና የሥጋ ነገር የታወክነውን ቀርቶ መንፈሳዊውን ሰው ነቢዩ ዳንኤልን "አትፍራ" ብሎ ፍርሃትን አርቆለታል ዳን 8:15 ; 10:12 :: የአምላክ እናት ድንግል ማርያምንም ሲያበሥራት "ማርያም ሆይ አትፍሪ በእግዚአብሔር ፊት ጸጋን አግኝተሻልና" ሉቃ 1:29-40 እያለ ነበር ::

4 . ስለ ምእመናን በእግዚአብሔር ፊት በባለሟልነት የሚቆም (የሚለምን የሚማልድ) መልአክ ነው "እኔ በእግዚአብሔር ፊት የምቆም ገብርኤል ነኝ" እንዳለ ሉቃ 1:19

5 . ደጋግ ሰዎችን ለንስሐ እንዲበቁ ከስህተታቸው እንዲታረሙ እንደ አባት የሚቀጣ መልአክ ነው :: ካህኑ ዘካርያስን ዲዳ እንዲሆን እንደቀጣውና ልጁ በተወለደ ጊዜም አንደበቱ እንደሚፈታለት እንደነገረው መጽሐፍ ይነግረናል ሉቃ 1:19-25 :: "ኃጢአት ብትሠሩ ይቅር አይልምና አታስመርሩት በፊቱም ተጠንቀቁ" ተብሎም ከኃጢአታቸው የማይመለሱትን እንደሚቀጣ ተነግሮናል ዘጸ 23:20

6 . በእባቦች ላይ በገነትም ባሉ ጻድቃን ላይ በኪሩቤልም ላይ የተሾመ ከከበሩ መላእክት አንዱ ገብርኤል ነው ተብሎም ተነግሮናል ሔኖክ 6:7-8 :: እንግዲህ ምን እንላለን ? የመላእክት አለቃ የአብሣሬ ትስብእት የቅዱስ ገብርኤል ጥበቃ አይለየን አሜን!!

#ቢትወደድ ወርቁ
የካቲት 18 ቀን 2011 ዓ ም
ድጋሚ የተለጠፈ
Audio
ዐውደ ምሕረት
Audio
ርዕስ :- #ሚተራሊዮን
ደራሲ :- #ዶ/ር ዓለማየሁ ዋሴ እሸቴ
ምዕራፍ :- #11
ተራኪ :- #ተርቢኖስ ሰብስቤ
ቆይታ :- #21ደቂቃ ከ41 ሰከንድ ብቻ
የቦታ ይዞታ :- #2.6 mb ብቻ
#ዐውደ_ምሕረት_የእናንተ 🙏
_°°°°°°°°°°°___
Audio
ርዕስ :- #ሚተራሊዮን
ደራሲ :- #ዶ/ር ዓለማየሁ ዋሴ እሸቴ
ምዕራፍ :- #12
ተራኪ :- #ተርቢኖስ ሰብስቤ
ቆይታ :- #9ደቂቃ ከ38 ሰከንድ ብቻ
የቦታ ይዞታ :- #1.7 mb ብቻ
#ዐውደ_ምሕረት_የእናንተ 🙏
_°°°°°°°°°°°___
#ሰላም ለበድነ ሥጋከ
__________________
" #ተክለ_ሃይማኖት_ሆይ መዐዛው እጅግ ጣፋጭ በሆነ ሽቱ መምህር ኤልሳዕ ለገነዛት በድነ ሥጋህ ሰላም እላለው"
|መልክዐ ተክለ ሃይማኖት
#እንደ_ልቤ ከሆነ ከጻድቁ ልጅ #ከዳዊት ሃብታት አንዱ ሲገለጥ !

#ሃብተ_ዝማሬ
|በስባረ ሐጽምህ በፈሰሰው ደምህ
በፈጸምከው ገድልህ ባማላጅነትህ
ተክለ አብ ተክለ ወልድ ተክለ መንፈስ ቅዱስ እርዳን በጸሎትህ

ሐዲስ ዝማሬ #በዘማሪ ዳዊት ክብሩ
Audio
ርዕስ :- #ሚተራሊዮን
ደራሲ :- #ዶ/ር ዓለማየሁ ዋሴ እሸቴ
ምዕራፍ :- #13
ተራኪ :- #ተርቢኖስ ሰብስቤ
ቆይታ :- #21ደቂቃ ከ32 ሰከንድ ብቻ
የቦታ ይዞታ :- #2.6 mb ብቻ
#ዐውደ_ምሕረት_የእናንተ 🙏
_°°°°°°°°°°°___
❝...#ጌታ_ቢፈቅድ ብንኖርም ይህን ወይም ያንን እናደርጋለን ማለት ይገባችኋል።❞
ያዕቆብ 4: 15
ክፍል 1

ሰላም ወዳጆች...
እንዴት ነው ?
ዓመቱ እንዴት እየተጠናቀቀ ነው?

እግዚአብሔር ፈቅዶ 2014 ዓ.ም ዘመነ ማርቆስን ለማገባደድ በጣት የሚቆጠሩ ቀናት ቀርተውናል ። እስቲ ዘወር ብለን ያለፈውን ጊዜያቶች እንዴት እንዳሳለፍን እንመርምር። መመርመር በጥያቄ ይጀምራል እና ይህንን ልጠይቅ... !

ስንቱን አተረፍንበት.... ?
ስንቱን ከሰርንበት.... ? ለምን ?
ስንቱንን በሚጠቅመን ነገር አሳለፍንበት ...?
ስንቱን በማይጠቅም ነገር አሳለፍንበት.... ? ለምን?
ምን ያህሉን ጊዜ አዲስ ዕውቀት ለመጨመር ተጋንበት ?
ስንት መጽሃፍትን አነበብን ? ስንቱን ኖርነው ?
በዚህ ዓመት ልንፈጽመው #ካቀድነቸው ነገሮች ውስጥ ምን ያህሉን አሳካናቸው ? ምን ያህሉን አላሳካነውም? ለምን ?
ከሁሉም ከሁሉም ግን ወሳኙ ጥያቄ ምን ያህሉን ጊዜ ለእግዚአብሔር ሰጠነው ? ምንያህሉን ጊዜ ከእግዚብሔር ጋር ተገናኘንበት ? የሚለው ነው ?

በእርግጥ ይህንን ጥያቄ ሙሉ ለሙሉ ለመመለስ ጊዜ ቢያስፈልገውም እንዲው የግምገማ ጊዜ ቢኖረን ከሚል ወንድማዊ ፍቅር ጠየኩኝ ። በእርግጠኝነት መናገር የምችለው ግን ለሁሉም ላላሳካነቸው ነገሮች ያሳምንም አያሳምንም ? ይብዛም ይነስም አዕምሮአችን ምክንያት ይሰጠናል ።

#ንግባኬ_ሀበ_ጥንተ_ነገር እንዲል ሊቁ ወደ ቀደመ ነገሬ ስመለስ ከላይ ላሉት ጥያቄዎች ለምን ሙሉ ለሙሉ ማሳካት አልቻልኩም ብለን ስንጠይቅ መልሱ ወደ አንድ ነገር ያመራናል ።
የጊዜ አጠቃቀም እና ምክንያታዊነት!

ስለ ጊዜ አጠቃቀም በሌላ ርዕስ ብመለስበት ስለሚሻል ስለ ምክንያታዊነት ይህንን ልበል! ቅዱስ መጽሀፍ እንደሚያስተምረው ለየትኛውም ስንፉናችን ምክንያት ሊያድነን አይችልም።

❝እኔ መጥቼ ባልነገርኋቸውስ ኃጢአት ባልሆነባቸውም ነበር፤ አሁን ግን ለኃጢአታቸው #ምክንያት የላቸውም።❞ ዮሐንስ 15: 22
ጌታችን መድኅኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሲያስተም ስላደረገው ተዓምር እስራኤላውያን እንዳይሰናከሉ አንድም ለሰው ልጅ ተዐምራቱ ላይ እንዳንሰናከል ምክንያትን ለማስወገድ አንድን ተዐምር በአራት ወንጌላውያን ሲያስመሰከር ሲያጽፍ እንገኘዋለን። ይህም ተዐምር...
• ቅዱስ ማቴዎስ... ቦታው የተመቸ (ሳር እና ለምለም) እንደነበር ይገልጣል። ለምን ይህንን መግለጥ አስፈለገው ቢሉ አይሁዳውያን ቦታው አልተመችንም ስለዚህም አልበላንም እንዳይሉ!
ማቴዎስ 14 :19
ሕዝቡም #በሣር ላይ እንዲቀመጡ አዘዘ፥ አምስቱንም እንጀራና ሁለቱን ዓሣ ይዞ ወደ ሰማይ አሻቅቦ አየና ባረከ፥ እንጀራውንም ቆርሶ ለደቀ መዛሙርቱ ሰጠ፥ ደቀ መዛሙርቱም ለሕዝቡ።

• ቅዱስ ማርቆስ ደግሞ ቦታው ምድረ በዳ (ከከተማ ወጣ ያለ ስፍራ) እንደነበር ይገልጻል ። ለምን ይህንን ገለጠ ቢሉ ከከተማ ገዝተው አበረከትን ይላሉ እንዳይሉ!
ማርቆስ 8 ፡ 4
ደቀ መዛሙርቱም፦ በዚህ #በምድረ_በዳ እንጀራ ከየት አግኝቶ ሰው እነዚህን ማጥገብ ይችላል? ብለው መለሱለት።
• ቅዱስ ሉቃስ ወቅቱን ይገልጽልናል። መሽቶ እንደነበር ። ተዐምሩን ለምን በቀን አላደረገም ቢሉ በጠዋት ቢያደርገው በልተን መጥተናል ባሉት ነበር በምሳ ቢያደርገው የጠዋቱ አለ ባሉት ነበር ። ስለዚህ አብረው ውለው ማታ አድርጎ ምክንያት አሳጣን።
ሉቃስ 9: 12
❝ቀኑም ይመሽ ጀመር፤ አሥራ ሁለቱም ቀርበው፦ በዚህ በምድረ በዳ ነንና በዙሪያችን ወዳሉ መንደሮችና ገጠሮች ሄደው እንዲያድሩና ምግብ እንዲያገኙ ሕዝቡን አሰናብት አሉት።❞
• ቅዱስ ዮሐንስ ደግሞ አካባቢውን በመግለጽ ይጀምራል። ምክንያት ቢሉ አይሁድ የማንጻት ለማዳ ነበራቸው እና! ሳይታጠቡ አይበሉም ነበር እና !
ዮሐንስ 6: 1
❝ከዚህ በኋላ ኢየሱስ ወደ ገሊላ ባሕር ማዶ ተሻገረ፤ እርሱም የጥብርያዶስ ባሕር ነው።❞
ይህ የሚያስተምረን ለየትኛውም ድክመታችን ምክንያት እንደሌለን ነው።

ከምክንያተኝነት በመቀጠል ትልቁ ችግር ከእቅዳችን እግዚአብሔርን ማስወጣት ነው ። ምንም ነገር ስንጀምር ፈቃደ እግዚአብሔርን ካላስቀደምን ጦርነት ሳይጀምር እንደተሸነፈ ወታደር ነን !

ሊቁ እንደተናገረው። " እግዚአብሔር የሌለበት ዕቅድ እና መስመር የሳተ መንገደኛ አንድ ነው " ሁለቱም መድረሻቸው አያታወቅም እና!

እንቀጥላለን... !

መ/ር ዲ/ን እስጢፋኖስ ደ.
26/12/2014
.....የቀጠለ
❝...#ጌታ_ቢፈቅድ ብንኖርም ይህን ወይም ያንን እናደርጋለን ማለት ይገባችኋል።❞
ያዕቆብ 4: 15
ክፍል 2

ሰላም ወዳጆች ? ትላንት በክፍል 1 ቆያታችን እያገባደድን እየመጣን ስላለው ዓመት አጭር የግምገማ እና ለምን አላሳካነውም ለሚሉ ጥያቄዎች መልስ መስጠት ጀምረን ነበር ።

ምክንያተኝነትን እና ምክንያትን ለዓላማ እንዲሁ ለ መንፈሳዊ እድገት መቀጨጭ ዋና አስተዋጽዖ እንዳለው በግርድፉ ተመልክተን ነበር ።
ዛሬም በዚህ በክፍል ሁለት አንድ አንድ ነገር እንነገራለን ።

ዓመቱን እንዴት እንዳሳለፍን ለራሳችን ስንጠይቅ ብዙ ነገሮች በአእምሯችን እንደተመላለሱ ለመገመት ሊቅነትን አይጠይቅም ። ዋናው ነገር ግን እርሱ አይደለም ።
መልሶቹ ውጫዊው አጋደለ ወይስ ውስጣዊው???
ወደ ሌላ ወይስ ወደራሳችን ?
ወደ ሰፊው ዓለም ወይስ ወደ ራሳችን ዓለም ?

መልሱ ወደ ወጪ ካመዘነ አሁንም ደግመን የምንጠይቅበት ሰዐት ነው ። ምክንያቱም መልሱን አላገኘነውም ! አለቀ።

ብዙ ጊዜ የችግራችን (መንፈሳዊ ይሁን ዓለማዊ) መንስኤ ውጫዊ እንደሆነ ካሰብን ውጫዊ መፍትሔ ስንፈልግለት እንደ ባዘንን ሳንንድን ሌላ የተሰጠንን ጊዜ እናባክናለን ። ቅዱሱ መጽሃፍ ❝...የመዳን ቀን አሁን ነው።❞ 2ኛ ቆሮ 6: 2 ሲል አሁን የመለወጫ የመወሰኛ ጊዜ ነው እያለን እንደሆነ ልብ ይሏል።

ቅዱስ ጳውሎስ እንደተናገረው
❝ነገር ግን በዚያ በሚመኩበት እንደ እኛ ሆነው ሊገኙ፥ #ምክንያትን ከሚፈልጉቱ #ምክንያትን እቆርጥ ዘንድ አሁን የማደርገውን ከዚህ ወዲህ ደግሞ አደርጋለሁ።❞
—2ኛ ቆሮ 11: 12
ምክንያተኝነትን እያስወገድን ራሳችንን መመልከት ያስፈልጋል። ሌላው ብዙ ስንጠይቅ መራቀቅን ለጊዜው እያስቀመጥን ቢሆን ደግሞ መልካም ያደርገዋል ።
ሁለት የፍልስፉና መጽሀፍ ያነበበ ወዳጄ" ሰላም ነው?" ስለው የመለስልኝ መልስ ፈገግ ቢያሰኘኝ ነው ይህን ማለቴ !
ጓደኛዬ :- ውስጣዊ ነው ውጫዊ ???

በገድለ አቡነ ተክለሃይማኖት ያለች ልትራቀቅ ወድዳ ፍዳ ያመጣች አንዲት መነኩሲት ሰው ላስታውሳት። አባታችን ጸሀይ ዘኢትዮጲያ አቡነ ተክለሃይማኖት በደብረሊባኖስ በነበሩበት ወቅት አራዊት እየመጡ የልጆቻቸውን አዝመራ እየበሉ አስቸገሯቸው ። ልጆቹም ሄደው " አባታችን! እንስሳት አራዊት አትክልታችንን እየበሉ አስቸገሩን " አሏቸው።
ቅዱስ አባታችንም "ልጆቼ ተውአቸው ። እኛ ወደ ጫካ መጣንባቸው እንጂ እነርሱ አልመጡብንም" ሲሉ መለሱላቸው ።

እንዲህ ሆነው ሳለ ከዕለታት በአንድ ቀን አንዲት አረጋዊት መናኝ ስተመገብ አንድ ዝንጀሮ መጥቶ በጥፊ ጠርቅሞ ቀምቷት በላ ። አባታችንም ይህንን አይተው :- " የተሰጡትን ትቶ ሌላ ያልተሰጡትን መሻት የያዙትን ያሳጣል። እኔ በዱር የተዘራውን ትበሉ ዘንድ ብፈቅድ ከሰው እጅ እየቀማችሁ መብላት ጀመራችሁ?" ብለው "ወንጌልን በምሰክለት በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አፋችሁን የታሰረ ይሁን! " በቃለ ማእሰር ዘጓቸው ። ከዚያን ቀን ጀምሮ መብላት ተሳናቸው ።

በስተመጨረሻም ሩጫቸውን ጨርሰው ሊያርፉ ሲሉ ልጆቻቸው ጠርተው ሲሰናበቱ መረቋቸው። በዚህ ጊዜ ያች ሴት ልትራቀቅ ወድዳ " አባቴ በጸሎቶ ያሰሩትም ይፍቱ " ብላ ጠየቀች። እርሳቸውም " የታሰረውም ይፈቱ " ሲሉ ዝንጀሮውም አብሮ ተፈታ ። በዚህም ከቀደመው የበዛውን አጠፉ።
ስናጠቃልለው በነገርም ያለ ነገርም # አትራቀቅ ...!

እንቀጥላለን ።
“ የሚያምኑትም ከፊት ይልቅ ለጌታ #ይጨመሩለት ነበር፤ #ወንዶችና_ሴቶችም ብዙ ነበሩ።”
|ሐዋ 5፥14
#እግዚአብሔር_ይመስገን ገና #እንበዛለን !