#ቆንጆዎቹ
፡
፡
#ክፍል_አንድ
፡
፡
#ድርሰት_ሰርቅ_ዳንኤል
#ቅድመ_ታሪክ
እሪ! እሪ! ይላል አምቡላንሱ። ከፊቱ ያለውን እያተራመሰ፤እየደረማመሰ በጭለማው ውስጥ እንደ ቀስት ወደፊት
ይወነጨፋል፡፡ ቦግ..እልም ቦግ...እልም የሚሉትና የሚንቀለቀሉት ቀያይ የአደጋ መብራቶቹ የሚተፉት ቀይ ብርሃን በጨረቃ የለሹ ምሽት እየተወራጨ በዝናቡ ጎርፍ በተዘፈቀው አስፋልት ላይ ሲያርፍ ዙሪያው የደም ኩሬ ይመስላል። እሪ! እሪ! እሪ! ይላል አምቡላንሱ፤ በደሙ ኩሬ ውስጥ እየተንቦራጨቀ እሪ! እንደ መብረቅ ሲወረወር በሩቅ ያዳመጡት
አሽከርካሪዎች ጥግ ጥግ ይይዛሉ፡፡ እግረኞች ከመኪናው መንገድ ይሸሻሉ
በሩቅ ቆመው በምሽት ከር ሰበርግጎ እንደወጣ ጎሽ አፍጥጠው ይመለከቱታል። ከእራት ኪሎ አቅጣጫ የመጣው አምቡላንስ መሃል ለመሃል
ተርትሯት ሲገባ ካዛንቺስ ተሸበረች።
መንገድ ዳር የቆመችው የዲፕሎማቲክ መለያ ታርጋ የለጠፈችው መኪና ፈንጂ እንደተጠመደባት ሁሉ በቅ በሕዝብ ተከባለች፡፡ ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት በየመኪናዎቻቸው አናት ላይ የተገጠመላቸውን ሰማያዊ መብራት "ብልጭ ድርግም ብልጭ ድርግም እያደረጉ የደረሱት ፖሊሶች ሕዝቡን ለመብተን ይጥራሉ፡፡ ከዚህ ሲበትኑት ከወዲያ ይጠራቀማል፡፡የደንብ ልብስ የለበሱ ሁለት የፖሊስ መኮንኖች ከመኪናዋ ጎን እንደቆሙ የአምቡላንሱን ድምዕ ሲሰሙ ተቁነጠነጡ፡፡ ጠና ያለው ወደ መኪናዋ ተጠጋ፡፡ በመሪው በኩል ያለው በር ተከፍቷል፤ መስታወቱ ኣስፋልቱ ላይ ረግፏል፡፡ በሹፌሩ መቀመጫ ላይ የተቀመጠው የሞሮኮው ወታደራዊ አታሼ
ወደኋላ ተንጋሎ ዐይኖቹን ገርበብ አድርጓቸዋል፡፡ በስተግራ ከማጅራቱ ስር
ጥይቱ ከገባበት ጠባብ ቀዳዳ በቀጭኑ የሚንቆረቆረው ደም ግራ ትከሻውን
አበስብሶታል፡፡ ፖሊሱ ጠጋ ብሎ አጠናው፤ ግራ እጁን አንስቶ የልቡን ምት
አዳመጠ፡፡ አለ፡፡ አልሞተም፡፡ ደም የምትረጭ ልቡ የቀራትን እንጥፍጣፊ
እየጨመቀች ትር ትር ትላለች፡፡
የአምቡላንስ አዩዬ እያቀረበ መጣ፡፡ ፖሊሱ ትከሻው ሲነካ ተሰማው፡፡ ቀና ብሎ ተመለከተ፡፡ ከጀርባው ከቆመው ጓደኛው ጋር ተያዩ፡፡በመላ ተነጋገሩ፡፡ የአምቡላንሱ ድምዕ ቀረበ፡፡ ትርትር ትላለች ልቡ፡፡ ዋይ!
ዋይ! ይላል ኣምቡላንሱ። ፖሊሶቹ ተያዩ፡፡ የተሰጣቸው ትዕዛን ቁርጥ ያለ ነው:: ጠና ያለው ፖሊስ እጁን ሰደደና ከመሪው ጀርባ ጋላል ያለውን ቁስለኛ አፍና አፍንጫ ጥርቅም አድርጎ አፈነው፡፡ ትርትር አለች ልቡ:: ትንሽ ተፈራገጠ። ትር ትር ወዲያው ዝም አለ፡፡ ቀና አዕ ፖለሱ፦ ለመጀመሪያ
ጊዜ እርጋታ እየታየበት፡፡
#ቆንጆዎቹ_ገና_አልተወለዱም።
ኤኬ አርማህ
..አዲስ አበባ የአፍሪካ መዲና… እሁድ ሐምሌ 21.99… ማለዳ ያነባል. በርኖሱን ደርቦ፤ አንገቱን ቀልሶ እንባውን ያወርዳል ሰማዩ፡፡ ምድርን ከምድር ሲያይ፤ሲያዝን ሲተክዝ ሲባባ፤ ሲመረው... ሰማዩ ከሰማይ ስቅስቅ ብሎ ያለቅሳል። እረፍ አልኩ ስል በርኖሱ ይተክዛል፡፡ ዳግም ሆዱ ሲርድ... አንጀቱ ሲላወስ ሆድ ዕቃው
ሲታሰስ መንፈሱ ሲታመስ አሄሄ!… እህህ! ነፍሱ ስታቃስት ዳግም ይጀምራል ሊያለቅሰው፣ ሊያነባ…. ሰማዩ ማለዲ
ክረምቱ ጨክኗል ዓለም ምድር… ማማ..ከል ለብሳለች...ትንፋሿ ዳምኗል.. ጥላሸት? ….. እንፋሎት? ጭጋግ ነው! ባዘቶ!...
በአፓርትመንቱ ሶስተኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው በጉም በተሸፈነው የመኝታ ቤት መስኮት ቁልቁል የሚታየው ድብዝዝ ያለ ትርኢት አላጠግብህ ቢለው እጁቹን በመጋረጃ ውስጥ አሾልኮ ቀዝቃዛውን መስታወት በመዳፉ ወለወለው፡፡ ጨካኙ ቅዝቃዜ እንደመርፌ ጠቅ አደረገው እጁን ግን አልሰበሰበም፡፡
ከመንገዱ ባሻገር ያለው መናፈሻ ጭር እንዳለ ነው... ቢሆንም.…እየነጋ ነው. ሌላ ቀን አዲስ ቀን
ባዶ እግሩን ምንጣፉ ላይ እንደቆመ ራቁት ደረቱን አከክ አከክ አደረገና ሰዓቱን ተመለከተ፡፡
እንድ ሊሆን ነው አንድ አንድ ቀን፡፡
ፊቱን ወደ አልጋው መልሶ ቆመ ፡፡ እንደ ሁሌው እግሮቿን ዘና አድርጋ እጆቿን እዚያና እዚያ አመናቅራ በጀርባዋ ተንጋላ ተኝታለች፡፡ከላይዋ ላይ ተንሸራቶ አንድ ጠርዙ ከመሬት ሌላው ጠርዝ ከአልጋው መሃል የደረሰው የብርድ ልብስ ክፉኛ አጋልጧታል፡፡ የተመነቃቀረውንና የተበታተነውን አልጋ ሲመለከት ሰውነቱ ተፍታታበት፡፡
ቶሎ ብሎ ዓይኖቹን ክተጋለጠው ሰውነቷ ላይ ነቀላና ወደ መታጠቢያ ቤት አመራ፡፡
ሰውነቱን በሙቅ ውሃ ተጣጥቦ በሰፊ ፎጣ ኣካላቱን እያደራረቀ ወደ መኝታ ቤቱ ተመለሰ። ፈገግ አለ ሲመለከታት። ከእንቅልፏ ተነስታ ሰፊው አልጋ መሃል ተቀምጣለች፤ እንቅልፍ ያሳበጠው ትኩስ ፊቷ ወደ ቀድሞ ቅርጹ አልተመለሰም። ቦዛዝ ያሉ ጥቋቁር ዓይኖቿ ገና ማየት የጀመሩ አይመስሉም፡፡ ብትንትን ብሎ ትከሻና ደረቷ ላይ የተዘራው ፀጉሯ የደነበሩ መንታ ሚዳቆዎች የሚመሳስሉ ራቁት ጡቶቿን መሸፈን መሸሸግ አቅቶት
ግራ ተጋብቷል፡፡
“እንዴት አደርሽ እንዳትለኝ፡፡” አለች እንቅልፍ ባጎረነነው ድምጿ ተሽቀዳድማ፡፡
ለምን?” ፈገግ አለ፡፡
“ደህና አልልህማ! እብደት ነበር'ኮ… ናቲ ሙት እብደት ነው፡፡አንዳንደሰ ሰው መሆንህን ያጠራጥረኛል። አውሬ! " አለች ድንገት በሁለት እጆቿ ጭንቅላቷን ያዝ አድርጋ።
“አዳም ካደረገው የተለየ ምን ሳደርግ ተገኘሁ?” አለ ናትናኤል እየሳቀ፡፡ አልጋው ጫፍ ላይ ተቀምጦ ጎተት አደረጋት። ተጎተተችለት፡፡እጆቹን በብብቶቿ አሳልፎ አቅፎ ያዛት:: ሳመችው።
“አዳም እንዳንተ ከቀበጠ ሄዋን ብትጮህም የሚደርስላት የለም ብሎ
ነው፡፡ አንተ ግን ድገመኝና አስይዝሃለው…ጎረቤቶችህን ነው የምቀሰቅስልህ፡፡”
“ሀ! ሀ ! ሀ! ጎረቤቶቼ ከእኔ ተሽለው? ርብቃ፤ ሁሉም በየጓዳው አውሬ ነው፡፡ ፊት ከሰጡት ሁሉም አንድ ነው። ፊጥ ካለበት አይወርድም፡፡”እጆቹ በአንሶላው መሀል ዋኝተው አልፈው ጭኖቿ መሃል ገቡ፡፡
“እረፍ! እየው ደሞ ጀመረህ.. ቆይ! ናቲ!”
ሳይታወቀው ተመልሶ ገባበት፡፡ ስህተት:: ዛሬ ኣልጋ ላይ መዋል የለበትም፡፡በፍጹም! ምን ማድረጉ ነው ታዲያ? ድንገት ከአልጋው ላይ ተፈናጥሮ ተነሳ፡፡ ሳይታወቀው ፕሮግራሙን አበላሽቶ ነበር። ከርብቃ ጋር አንዴ ጨዋታ ከጀመረ! ልፊያ ከቀመሰ ቀኑ እንደማይበቃው ያቀዋል።አሽትቶ፣ ልሶ፧ ገምጦ፣ አኝኮ፤ ውጦ አያጠግባትም፡፡ ድጋሚ እንደ አዲስ
ሊያሸታት ይጀምራል፡፡ ሳይወድ በግድ ራሱን ተቆጣጥሮ ፊቱን መለስና ማበጠሪያውን አንስቶ , ፀጉሩን ያበጥር - ጀመር፡፡ : እናቷን! ይቺ ልጅ ሳይታወቀኝ መዳፏ ውስጥ ልትከተኝ ነው. አሰበ።
“ለምን ተነሳህ ግን በጠዋት?" በጀርባዋ “ክተንጋለለችበት ሳትነሳ ሽቅብ እያየች ጠየቀችው::
“ቀጠሮ” በመስታወቱ ውስጥ እየተመለከታት::
“በእሁድ!”
“አዎን ርብቃ፡፡” አለ በለሆሳስ፡፡
“ምንድንነበር ያልከኝ?…አበዛኸው! ናትናኤል ሙት አበዛኸው አሁንስ የቤትህ ቁሳቁስ መሰልኩህ መሰለኝ…” አለች እንደተከፋ ሕፃን እግሮቿን አመናጭራ ከአልጋ እየወረደች፡፡ “…በሳምንት ሁለት ቀን ብቻ መገናኘታችን በዛና በእሁድም ቀጠሮ ተይዝ ጀመር…አልታወቀህም እንጂ በጣም ነው የተዘባነንከው፡፡” ከእልጋው ግርጌ የተቀመጠውን ነጭ የጠዋት ልብስ ኣንስታ ሳትደርበው መሬት ለመሬት እየጎተተችው እራቁቷን የመታጠቢያ ቤቱን በር በርግዳ ገባችና ከውስጥ ጠረቀመችው፡፡ደቂቃም ሳትቆይ ጮሃ ስትሳደብ ተስማው-“አንተ ብሽቅ!... እርኩስ!…”፡፡ ብቻዋን ትጮሀለች፡፡ ፈገግ አለ የጥርስ ሳሙና የተቀባውን የሽንት ቤት መቀመጫ አስታውሶ ስትናደድ!
ስትቆጣ፤ ግስላ ስትሆን ይበልጥ ታምረዋለች፡፡ተራ ህይወታቸው ብቻ
አይደለም፥ ፍቅራቸውም ትግል ነው! ንክሻ ፤ ቡጭሪያ እሷም ብትሆን ጠዋት ጠዋት ትነጫነጭ

👍3