#ከከዳኸኝ_ክህደት_ይልቅ
እሳት ረግጠን ለብሰን እሳት፣
ከላይ ሃሩር ከፊት ጥይት፣
ከውስጥ ረሃብ የአካል ዝለት፣
ከተፈጥሮ ጋር ግብ ግብ
ከጠላት ጋር መተናነቅ፣
ለአንድ ኢትዮጵያችን ክብር
በጥቁር አፈሯ ላይ አብረን መውደቅ፡፡
ወዲህ ደግሞ ሲኖር ፋታ፣
ከዛፍ ጥላ ስር ተቀምጠን፣
ክላሻችንን ተመርኩዘን፣
የልብ ምስጢር የምንጋራ
አላማ ያስተሳሰረን፡፡
አደዬ ወላጅ እናትህ
የእናቴን ናፍቆት የሚያስረሱኝ፣
‹ ‹ ወደይ› › እያሉ ፍቅር የሰጡኝ፣
‹ ‹ አጁሃ›› ብለው ያበረቱኝ፣
ቋንቋህን መልመድ ተስኖኝ
እያበሸቅክ ያግባባኸኝ፣
አንተ ማለት የልቤ ሰው
የመወለድን ቋንቋነት
ወንድም ሆነህ የነገርከኝ፡፡
‹ ‹ ምድራዊ ፈተና በዝቶ
ዙሪያው ቢነድ በገሞራ፣
ጥሰነው እናልፈዋለን
የማይሞት ታሪክ ልንሰራ› ›
እያልን የዘመርን በጋራ፣
‹ ‹ የማንጨበጥ ነበልባል
እሳት ነን ለጠላታችን፣
ፍሙ ከርቀት ይፋጃል
ብረት ያቀልጣል ክንዳችን )
ብለን በወኔ ያዜምን፣
እኔና አንተ አንድ ነበርን፡፡
ጓዴ.......!
ካንተ ቀድሜ ፈንጂ ልረግጥ
ነብሴን ልሰጥህ የማልኩብህ፣
ምን ያህል አምኜህ ነበር
ጭምብልህን ገልጩ ያላየሁህ?
የቀበሮው ጉድጓድ ወንድሜ
አንተ የክፉ ቀን ጓዴ፣
ሃገሬን በጎጥ ሸጠሃት
ቃታ መሳብክን ልመን እንዴ?
በግፍ ጥለኸኝ እያየሁ
ለአሞራ ሲሳይ ስትሰጠኝ፣
በሬሳዬ ላይ ስትጨፍር
እፍኝ አፈር እንኳ ነፍገኸኝ
ቀርጥፈህ ከበላኸው ቃል በላይ
ከከዳኸኝ ክህደት ይልቅ፣
እመነኝ እጅግ ያመኛል
አንድ ጥያቂ ባልጠይቅ፡፡
ጥያቄዬ...!
ይሄ ሁሉ የግፍ መዓት
ባኖርኳችሁ ላብ ገብሬ፣
ምን አጎደልኩኝ ንገረኝ
ምን በደለችህ ሃገሬ?
🔘በሻለቃ/ጋዜጠኛ ወይን ሐረግ በቀለ🔘
//መታሰቢያነቱ በጁንታው በግፍ ለተገደሉት የሰሜን እዝ አባላት//
እሳት ረግጠን ለብሰን እሳት፣
ከላይ ሃሩር ከፊት ጥይት፣
ከውስጥ ረሃብ የአካል ዝለት፣
ከተፈጥሮ ጋር ግብ ግብ
ከጠላት ጋር መተናነቅ፣
ለአንድ ኢትዮጵያችን ክብር
በጥቁር አፈሯ ላይ አብረን መውደቅ፡፡
ወዲህ ደግሞ ሲኖር ፋታ፣
ከዛፍ ጥላ ስር ተቀምጠን፣
ክላሻችንን ተመርኩዘን፣
የልብ ምስጢር የምንጋራ
አላማ ያስተሳሰረን፡፡
አደዬ ወላጅ እናትህ
የእናቴን ናፍቆት የሚያስረሱኝ፣
‹ ‹ ወደይ› › እያሉ ፍቅር የሰጡኝ፣
‹ ‹ አጁሃ›› ብለው ያበረቱኝ፣
ቋንቋህን መልመድ ተስኖኝ
እያበሸቅክ ያግባባኸኝ፣
አንተ ማለት የልቤ ሰው
የመወለድን ቋንቋነት
ወንድም ሆነህ የነገርከኝ፡፡
‹ ‹ ምድራዊ ፈተና በዝቶ
ዙሪያው ቢነድ በገሞራ፣
ጥሰነው እናልፈዋለን
የማይሞት ታሪክ ልንሰራ› ›
እያልን የዘመርን በጋራ፣
‹ ‹ የማንጨበጥ ነበልባል
እሳት ነን ለጠላታችን፣
ፍሙ ከርቀት ይፋጃል
ብረት ያቀልጣል ክንዳችን )
ብለን በወኔ ያዜምን፣
እኔና አንተ አንድ ነበርን፡፡
ጓዴ.......!
ካንተ ቀድሜ ፈንጂ ልረግጥ
ነብሴን ልሰጥህ የማልኩብህ፣
ምን ያህል አምኜህ ነበር
ጭምብልህን ገልጩ ያላየሁህ?
የቀበሮው ጉድጓድ ወንድሜ
አንተ የክፉ ቀን ጓዴ፣
ሃገሬን በጎጥ ሸጠሃት
ቃታ መሳብክን ልመን እንዴ?
በግፍ ጥለኸኝ እያየሁ
ለአሞራ ሲሳይ ስትሰጠኝ፣
በሬሳዬ ላይ ስትጨፍር
እፍኝ አፈር እንኳ ነፍገኸኝ
ቀርጥፈህ ከበላኸው ቃል በላይ
ከከዳኸኝ ክህደት ይልቅ፣
እመነኝ እጅግ ያመኛል
አንድ ጥያቂ ባልጠይቅ፡፡
ጥያቄዬ...!
ይሄ ሁሉ የግፍ መዓት
ባኖርኳችሁ ላብ ገብሬ፣
ምን አጎደልኩኝ ንገረኝ
ምን በደለችህ ሃገሬ?
🔘በሻለቃ/ጋዜጠኛ ወይን ሐረግ በቀለ🔘
//መታሰቢያነቱ በጁንታው በግፍ ለተገደሉት የሰሜን እዝ አባላት//
👍1