አትሮኖስ
280K subscribers
112 photos
3 videos
41 files
476 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#የተቃጠለ_ልብ
:
#ክፍል_አስራ_ሁለት
:
ደራሲ:-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ
:
:
...አቤል እና ሮዝ እድሳትበሚደረግለት አዲስ በምትከፍተው ሆቴል ውስጥ ቁጭ ብለው ስለቤተሰቦቿ እውነቱን ከውሸቱ እየደባለቀች እየነገረችው እንደነበርና እሱም ቤተሰቦቾን ለመፈለግ ወደ ዲላ እንደሚሄድ ቃል ገብቶላት እንደነበር #በክፍል_9 ታሪካችን አቅርበን ነበር ቀጣዩ👇

...አቤል ከአዲስ አበባ ከለሊቱ 12 ሰዓት ተነስቶ ስምንት ሰዓት ተኩል ሲሆን ዲላ ከተማ ደረሰ ፡፡ዲላን ከተማ ሲረግጥ ይሄ የመጀመሪያው ነው፡፡ግን ሙሉ አድራሻ እና መረጃ ይዞ ስለመጣ ብዙም አልተቸገረም፡፡ቤርጎ ይዞ ዕቃውን ካስቀመጠ ቡኃላ ቀጥታ ወደ ሮዝ እናት ቤት ነው የሄደው፡፡ ከመጠነኛ ፍለጋ ቡኃላ ቤቱን አገኘው፡፡ሰፋ ያለ ግቢ ያለው ደከምከም ያለ ይዞታ ላይ የሚገኝ የድሮ ቢላ ቤት ነው፡፡አንኳኳ …የውጪን በርፍ ሄለን ነች የከፈተችለት፡፡እንዳያት ነው ያወቃት፡፡
‹ቀጥተኛ የሮዝ ግልባጭ ነች› ሲል አሰበ፡፡ከዕድሜ መጠን ልዩነት በስተቀር አንድም ይሄ ነው የሚባል የጐላ ልዩነት የላቸውም፡፡
እጁን ለሰላምታ ዘረጋላት.. ፈራ ተባ እያለች ጨበጠችው፡፡‹‹ባልሳሳት ሄለን መሰልሺኝ››
‹‹በትክል ተመልሷል››አለችው አንተንስ ማን ልበል በሚል አስተያየት እየገመገመችው፡፡ከዚህ በፊት አይታው እንደማታውቀው እርግጠኛ ነች..ቢሆንም ስሜን ጠርቶ ሰላምታ ካቀረበልኝ የቅርብ ሰው መሆን አለበት በሚል እሳቤ‹‹ግባ ›› አለችው …አልተግደረደረም ….ተከትሎት ገባ ::የእቤቱ ውስጥ እንደውጩ ያረጀ አይደለም በጣም በጽዳት የተያዘ የዕቃዎቹ አደራደር እንከን ማይወጣለት በስርአት የተደራጀ ቤት ነው፡፡ወንበር ይዞ ተቀመጠ፡፡ከፊት ለፊቱ ተቀመጠች፡፡
‹‹እሺ አያትሽ የሉም ››ጠየቃት
‹‹እማዬን ያውቃታል ማለት ነው..?› ስትል በውስጧ አሰበች‹‹የለችም ወደ ለቅሶ መሰለኝ የሄደችው››በትህትና እንደታጠረች መለሰችለት፡፡
በማንነቱ ግራ እንደተጋባች ገባውና እራሱን ማስተዋወቅ ቀጠለ.. ሙሉ ስሙን ነገራት..ስሙ አዲሰ አልሆነባም… የሆነ ጊዜ የሆነ ቦታ ሰምታዋለች‹‹….ይቅርታ ከዚህ በፊት እንተዋወቃለን..?››በድፍረት ጠየቀችው
‹‹አይመስለኝም››
‹‹አይ ስምህን ስሰማው አዲስ አልሆነብኝም..ከሌላ ከሆነ ከማውቀው ሰው ጋር ተምታቶብኝ ይሆናል››
‹‹አይ እንደእዛ አይመስለኝም ስሜን ሰምተሸው ሊሆን ይችላል…ልብ ወለድ ታነቢያለሽ…?››
ብርግግ ብላ ደነገጠች፡፡ ‹‹አዎ አስታውስኩ ከደራሲው ጋር ስመ ሞክሼ ነህ ማለት ነው?››
‹‹አይ ሞክሼነት አይደለም… እራሱ ደራሲውን ነኝ››
‹‹ደራሲው?››
‹‹አዎ ምነው?››
‹‹እኔ እንጃ ….ታዲያ እንዴት ሆኖ …? በምን ምክንያት እኛ ቤት ለመምጣት ተገደድክ..መቼስ ዘመዳችሁ ነኝ ብለህ አታስጮኸኝም››
‹‹ያው ዘመዳችሁ ነኝ በይው …የእናትሽ ጓደኛ ነኝ፡፡››
‹‹ትቀልዳለህ እንዴት ሆኖ በምን መስፈርት ነው ከእማዬ ጋር ጓደኛ የምትሆነው?››
‹‹እዚህ ካሉት ከአያትሽ ጋር አይደለም ያልኩሽ..የሮዝ ጓደኛ ነኝ››
‹‹እ…..››ብላ በቅሬታ ከንፈሯን ወደኃላ ለጠጠችው
‹‹ምነው በአንዴ ፊትሽ ጨለመ…? ››
‹‹አይ እዚህ ቤት መጠራት የሌለበት ሰው ስም ነው የጠራኸው… ከአንተ የመተዋወቅ እድል በማግኘቴ በጣም ደስተኛ ነኝ..ግን አንድ የማልደብቅህ ነገር ቢኖር የመጣህበት መንገድ አልተመቸኝም››
‹‹የእሷ ጓደኛ ነኝ አልኩሽ እንጂ የመጣውት እኮ ከእሷ ጋር በተያያዘ ጉዳይ አይደለም›› ዋሻት
‹‹እና ለምን እንደሆነ ልታስረዳኝ ትችላለህ?››ከመኮሳተሯ ውስጥ ሳትወጣ ጠየቀችው፡፡
‹‹ሶስተኛ መጽሀፌን እየጻፍኩ ነው፡፡የመጻፌ ታሪክ ጭብጡ ደግሞ በዚሁ በዲላ ከተማ ዙሪያ የሚያጠነጥን ነው..ለዛም መረጃዎችን እንዳሰባስብ እንድታግዢኝ እርዳታሽን ለመጠየቅ ነው አመጣጤ››አላት ይሄ በፊትም ያሰበበት ዘዴ ነው፡፡
በዚህ ዘዴ ከቀረባት እና በእሷ ዘነድ አመኔታን ካተረፈ ቡኃላ.. ቀስ በቀስ ውስጧን ለማጥናት ይቀለዋል… ስለእናቷ ያላትን አመለካከት.. በመካከላቸው ያለውን ግጭት እንዴት ሊፈታ እንደሚችል ፍንጭ ያገኝ ይሆናል ..ከሁሉም በፊት ከእሷ ጋ መቀራረብና ልቧን ማግኘት ቀዳሚ ተግባሩ ነው፡፡አሁንም እያደረገ ያለው ወደ እዚያ የሚያደርሰውን መዳረሻ መንገድ ጥርጊያ እያሳመረ ነው፡፡
‹‹እንዴ ምን አይነት ነገር ነው ?እንዴትስ ልረዳው እችላለው?›› ስትል አሰበች ሄለን በውስጧ፡፡
‹‹ይሄንን እኔ የምችል አይመስለኝም፡፡ ባይሆን በዚህ ጉዳይ ላይ ብስለቱም ዕውቀቱም ያላቸው ሰዎች በከተማችን አሉ ..እነሱ እንዲረዱህ ማድረግ ትችላለህ፡፡እንደውም አንድ የማውቀው ሰው አለ ላስተዋውቅህ እችላለው..››
‹‹አይ አልፈልግም… ፍቅደኛ ካልሆንሽ በስተቀር እኔ የምፈልገው ያንቺን እገዛ ነው..ደግሞ የማትችይውን ነገር አልጠይቅሽም››
‹‹ካልክ እሺ..አንተን ማገዝ ከቻልኩ ለእኔ ክብር ነው…እንዲሁ በደረቁ አደረቅኩህ አይደል ሻይ ወይስ ቡና ላፍላ?››
‹‹አይ ምንም አልፈልግም.. አሁን ሄጄ አረፍ ልበል.. ነገ ከትምህርት ቤት ስትወጪ ደውልልሽ እና እንገናኛለን››
‹‹ኸረ ተው… እማዬን ሳታገኛት ነው የምትሄደው››
‹‹ግድ የለም ሰሞኑን እዚሁ አይደለው.. አገኛቸዋለው፡፡››ብሎ ተነሳ …በገረሜታ እንደታፈነች በራፍ ድረስ ሸኘችውና ወደቤቷ ተመለሰች፡፡
፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦
፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦
በሁለተኛው ቀን 11ሰዓት ላይ አንድ ካፌ ተቀጣጥረው ተገናኙ…
‹‹ይቅርታ ሄለን በቀጣይነት ልጽፈው ነው ያልኩሽ ታሪክ ዋና ገጻ ባህሪ አንቺ ነሽ››ቀጥታ ወደቁም ነገሩ ገባ
‹‹ይቅርታ አልገባኝም››መለሰችለት
‹‹ግልፅ ነው ፡፡በአንቺ እውነተኛ ታሪክ ላይ የራሴን ፈጣራ አክዬበት ና አዳብሬው ነው መጽሀፍን መጽፍ የምፈልገው››
‹‹እኔ ምን ታሪክ አለኝና ..››ብላ በመገረም ሳቀች
‹‹እሱን እኔ ነኝ የምወስነው…››
‹‹እንደፈለግክ››
‹‹እሺ ፍቃድሽን ከሰጠሸኝ አሁን እኔ እንደጋዜጠኛ ጥያቄ ጠይቅሻለው አንቺ ትመልሺልኛለሽ››
‹‹እሺ›› አለችው ከመገረም ውስጥ ሳትወጣ፡፡ጐኑ ካለው ወንበር ላይ አስቀምጦት የነበረውን ጥቁር የቆዳ ቦርሳ አንስቶ ከፈተና ከውስጡ ማስታወሻ ደብተሩን አወጣ፡፡ ቦርሳውን ወደ ቦታው መለሰው፡፡እስኪሪብቶ ከደረት ኪሱ አወጣና ተመቻቸ..የመጀመሪያ ጥያቄውን ጠየቀ
‹‹እሺ ሄለን ሙዚቃ ትወጂያለሽ?››ስለእሷ ከእናቷ በቂ መረጃ ስለሰበሰበ እንድታወራ የሚያደርጋትን መሪ ጥያቄ ለመጠየቅ ያን ያህል ከባድ አልሆነበትም…..
‹‹በጣም››በተነቃቃ ስሜት መለሰችለት…
‹‹እንዴት ሙዚቃ ልትጀምሪ ቻልሽ?››
‹‹ክረምት ክረምት አጐቴ ጋር አዲስ አባበ ስሄድ እሱ ቤት ፒያኖ ነበር ..እና እሱ ሲጫወት እያዳመጥኩ በጣም እመሰጥ ነበር..እንዲያለማምደኝ ስጠይቀው በደስታ አለማመደኝ ….ፒያኖውን መጫወት እየተለማድኩ እግረ መንገዴን መዝፈን ጀመርኩ… ከዛ በቃ ሳለውቀው ተፀናወተኝ ፡፡በትምህርት ቤትም ዝግጅት ሲኖር መድረክ ላይ ወጥቼ በመጫወት ተመልካቾቼ ስያደንቁኝና ስያጨበጨቡልኝ መበረታት ጀመርኩ እናም የወደፊት ህልሜ አደረግኩት፡፡..ግን እንዲህ አይነት ህልም እንዳልም ነፍሱን ይማረውና አጐቴ ነው ትልቁን ድርሻ የሚወስደው››
‹‹አጐትሽን ትወጂው ነበር ማለት ነው?››
‹‹ከመውደድም በላይ… አጐቴ ማለት በእናቴ ስህተት እና ክፋት ምክንያት ለማላውቀው አባቴ ምትክ ሆኖ ፍቅሩን የለገሰኝ …ሲንከባከበኝ የኖረ ለዕድገቴ ከአያቴ ቀጥሎ ትልቁን ድርሻ የያዘ …ያሳደገኝ ሰው ነው፡፡››
‹‹እዚህ እናንተ ጋር ነው አይደል የሞተው?››የሚያውቀውን እውነት በጥያቄ መልክ አቀረበላት፡፡
‹‹አዎ..አንዳንዴ እግዚያብሄር
👍1