አትሮኖስ
286K subscribers
123 photos
3 videos
41 files
587 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#መጉደልን_ወረስኩት

አንቺን እየፈለግከ፣ . . .
ስንት እዳሪ አለማሁ፣ ስንት ችግኝ ተከልኩ ፤
ስንት ጥቅምት አብቤ፣ ማፈራት እንዳማረኝ፤
የናፍቆትሽ ግንቦት፣ አክስሞ አረገፈኝ፡፡

በናፍቆት ሰማይ ላይ፣ በምናብ ጨረቃ ፤
አልሜሽ ሳልነቃ፣
አንግሼሽ ሳበቃ ፤
እውኔ ላደርግሽ፣ መኖርሽን ናፍቄ ፤
ከያበባው ዱቄት፣ ውብ ቀለም ጠምቄ፣
ስንት ግጥም ጻፍኩኝ፣ ስንት ዜማ ደረስኩ!
አንቺን እየጠበቅኩ፡፡

ደግሞ ተመልሼ፣ . .
ምኞቴ ሸራ ላይ፣ በተስፋ ብሩሼ ፣
እምቡጥ ሳፈነዳ፤
ቅጠል ሳለመልም ፧
ኩሬ እየቆፈርኩ፣ በረሀ ሳጠጣ ፤
አንኳን እጽዋቱ፡፤ አጽም ስጋ ለብሶ፣ አለት ስር አወጣ፡፡

ምን ያደርጋል ግና . . .
ያለ ፍሬ የቀረው፣ የተከልኩት ችግኝ፤
ውዳሴ ያደረግከት፣ የቋጠርኩት ስንኝ ፤
አብሮኝ አረጀና . . .
አብሮኝ አረጀና
የናፍቆትሽ ችግኝ ፤
የናፍቆትሽ ስንኝ ፤
የናፍቆትሽ ስእል፤
መጉደልን ለመድከት፣ ሆነኝ የራስ ምስል፡፡

🔘በደሉ ዋቅጅራ🔘

ጥቅምት፣ 2012፣ አዲስ አበባ