አትሮኖስ
280K subscribers
112 photos
4 videos
41 files
476 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#አላገባህም


#ክፍል_አስራ_አራት


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
/////

ሚካኤልና ፀአዳ አንድ ሬስቷራንት ቁጭ ብለው ተፋጠዋል፡፡ከሁለቱም ፊት ለፊት ተከፍቶ የተቀመጠ ቢራ አለ..አንዳቸውም ግን አንስተው አልተጎነጩለትም፡፡

‹‹ለምን ጊዜችንን ትጨርሳለህ…የሆንከውን ካልነገርከኝ እንደማለቅህ ታውቃለህ››

‹‹ፀዲ..ለምን ችክ ትያለሽ..?ምንም አልሆንኩ የስራ ጉዳይ ነው አልኩሽ እኮ››

‹‹እኮ ግድግዳ በመዶሻ የሚያስነድል ምን አይነት የስራ ጉዳይ ነው?፡፡ሚኪ እኔ እኮ ለአመታት ነው የማውቀው..አንተን የስራ ጉዳይ በዚህ ልክ ሊያበሳጭህ…ኦረዲ አብደሀል እኮ››

‹‹ተይ ፀዲ አታጋኚ››

‹‹አጋነንኩ እንዴ…?የማትነግረኝ ከሆነ …››አለችና እጇን ወደ ሱሪ ኪሷ ሰዳ ስልኳን አወጣች፡፡
‹‹ምን ልታደርጊ ነው?››ግራ በመጋባት ጠየቃት፡

‹‹ብቻዬን አልቻልኩህም..ለአዲስ ደውልላትና ትምጣ..ከዛ ለሁለት እንሞክርሀለን››

‹‹በፈጠረሽ……የእሷን ጭቅጭቅና ለቅሶ የምሸከምበት ትእግስቱ የለኝም››

‹‹እና ንገረኛ››

‹‹እሺ ነግርሻለው››
ስልኩን ጠረጴዛ ላይ ከቢራ ጠርሙሱ ጎን አስቀመጠችና ሙሉ ትኩረቷን ወደእሱ አደረገች፡፡
ለተወሰኑ ደቂቃዎች ቁዘማ በኋላ እንደምንም አፉን ከፈተ‹‹የአባቴ ጉዳይ ነው››

‹‹እሱንማ አውቄለው…ከዛ ውጭ አንተን በዚህ ልክ ሊረብሽ የሚችል ሌላ ጉዳይ የለም…በዝርዝር ንገረኝ፡፡

‹‹አባቴ እናቴንም ሆነ እህቴን እንዳልገደላቸው ነገረኝ…እኔም አምኜዋለው››

ፀአዳ ክፉኛ ደነገጠች‹‹እና ማን ነው የገደላቸው..?ማለቴ እንዴት ሞቱ?››ተንተባተበች፡፡

‹‹እሱን አላውቅም…አባቴ ግን ከመሞቴ በፊት እናትህንና እህትህን እኔ እንዳልገደልኳቸው በትክክለኛ ማስረጃ አረጋግጥልኝ፡፡ከመሞቴ በፊት ልጆቼ እኔ ንፅህ ሰው መሆኔን ማወቃቸውን ማረጋገጥ እፈልጋለው››አለኝ በማለት ሙሉውን ታሪክ በዝርዝር ነገራት፡፡

‹‹እና አሁን ምን ልታደርግ ነው…?እንዴት አድርህ ማረጋገጥ ትችላለህ?››

‹‹ግድግዳውን የናድኩት ለዛ ነበር..አባቴ እዛ ግድግዳ ውስጥ የደበቃቸው የተወሰኑ ማስረጃዎች ነበሩ..አለና ስልኩን ከፍቶ  በሚሞሪ ያሰቀመጣቸውን ቪዲዬዎች አስደመጣት፡፡ሽምቅቅ አለች፡፡

‹‹በጣም ያሳፍራል አይደል?››አላት፡፡

‹‹በእውነት ምን እንደምልህ አላውቅም››ስትል መለሰችለት፡፡

‹‹አየሽ ክህደት ምን እንደሆነ ምን አይነት ህመም እንደሚያስከትል ከእኔ በተሻለ አንቺ ታውቂያሽ..አባቴ እነዚህን ሁሉ መረጃዎች ካወቀ በኋላ ሚስቱ እሱን ሳይሆን ሌላ ሰው እንደምታፈቅር ከተረዳ በኋላ…በጣም የሚወዳት ቀምጥል ልጁ የእሱ ሳትሆን የሌላ ሰው ልጅ እንደሆነች ካወቀ በኃላ  ….የሁለት መንታ ወንድ ልጆቹ እናት እሱን ጥላ ወደልጅነት ፍቅረኛዋ ልትሄድ ዝግጅት ላይ እንዳለች በግልፅ ካወቀ በኋላ  ምንድነው ማድረግ ያለበት?ይሄንን ሁሉ በደል እንዴት መቋቋም ይችላል…?እና  እሱ ቢቀውስና የእብድ ስራ ቢሰራ ይፈረድበታል?››

‹‹በጣም የተወሳሰበ ነገር ነው…ግን እኮ አላደረኩትም ብለውሀል….›››

‹‹እሱማ  አዎ እወነቱን እንደሆነ ደግሞ እርግጠኛ ነኝ….ግን እንዳውቀው ካስቀመጠልኝ መረጃ አንድም እሱ እንዳለደረገው የሚገልጽ ፍንጭ ማግኘት አልቻልኩም..እና መተንፈስ እስኪያቅተኝ ድረስ በጣም ግራ ተጋብቻለው፡፡

‹‹ምን እንደገረመኝ ታውቃለህ?››አለች፡፡

ትኩረቱን በሙሉ ወደእሷ ሰበሰበና‹‹ምን? ››ሲል ጠየቃት፡፡
አባትህ በግድያው ተጠርጥረው ፍርድ ቤት በሚመላሰሱበት ጊዜ ይሄንን አሁን ለአንተ የሰጡህን መረጃዎች ለምን ለፍርድ ቤቱ አላቀረቧቸውም….ቢያንስ እኮ የተፈረደባቸው የሞት ቅጣት ወደእድሜ ልክ ይቀየርላቸው ነበር፡፡››

‹‹አዎ..ትክክል ነሽ…መረጃዎቹን እንዳገኘው እኔም ወደ አእምሮዬ የመጣው የመጀመሪያ ጥያቄ እሱ ነበር..እና ትናንትና ወደወህኒ ቤት ሄጄ አግኝቼው ነበር….ለምን ለፍርድ ቤት እንደመረጃ አድርገህ አላቀረብከውም ስለው…ለእናንተ ስል?››ሲል መለሰልኝ፡፡

‹‹አልገባኝም… እንዴት ለእኛ ስትል ?››ብየየ መልሼ ጠየቅኩት፡፡
‹‹እንዳልከው ይሄንን ለፍርድ ቤት እንደወንጀል ማቅለያ አድርጌ ባቀርብ ኖሮ ይሄኔ እናትም አባትም ነበር የምታጡት፡፡በወቅቱ የእኛ ቤተሰብ ጉዳይ በየጋዜጣውና መፅኄቱ እንዴት እንደሚፃፍ ታውቃለህ..ይሄ ነገር ወጥቶ ቢሆን ኖሮ ስለእናትህ ምን እንደሚፃፍ አስበው…የተፃፈ ነገር ደግሞ ታሪክ ሆኖ ይቀመጣል…የልጅ ልጇቼ ጭምር ስለወንድ እና ሴት አያታቸው ታሪክ ሲያነብ ምን አይነት የልብ መሰበር ያጋጥማቸዋል…የእኛን ማህበረሰብ ለነገሮች ያለውን ብያኔ የምታውቀው ነው..በእኔ ጉዳይ ምን ያህል ፈተና እና መገለል እንደሚገጥማችሁ አውቃለው…ይሄ የእሷ ታሪክ ቢጨመርበት ኖሮ መግቢያ መውጫ ነው የሚያሳጦችሁ››በማለት መለሰልኝ፡፡

‹‹አይገርምም !!ወላጅ መሆን እኮ እዳ ነው..አንዳንዴ የነፍስ ክፍያ ለመክፈል እንኳን የማታመነታበት ምስጢራዊ ፀጋ ነው፡፡››

‹‹አዎ ትክክል ነሽ››

‹‹አሁን አንድ ምርጫ ብቻ ነው ያለን››

በንቃት‹‹ምን ?››ሲል ጠየቃት፡፡

‹‹ሰውዬውን ፈልገን ማነጋገር››

‹‹የትኛውን ሰውዬ?››

ፈራ ተባ እያለች ‹‹የእናትህን ጓደኛ…..››ስትል መለሰችት፡፡

የሚካኤል ደም ስር በንዴት ውጥርጥር አለ‹‹እሱ እኮ ጠላታችን ነው..እዚህ ሁሉ ውጥንቅጥ ውስጥ የከተተን እሱ ነው…ፊት ለፊት አግኝቼ እንድገድለው ነው የምትፈልጊው፡፡››

‹‹የሆነ ፍንጭ ለማግኘት የግድ እሱን ማግኘት አለብን…የግድ አንተ ልታናግረው አይገባም…ቆይ እስኪ››  አለችና ጠረጴዛ ላይ ያስቀመጠችውን ስልክ አንስታ ከፈተች ..ምን ልታደርግ ነው ብሎ ሲጠብቅ‹‹ስሙ ማን ነበር››ስትል ጠየቀችው፡፡

‹‹የማ?››

‹‹የሰውዬው ነዋ››

‹‹ለሚ በቀለ ››

ስሙን ሰርች ላይ ከታ መፈለግ ጀመረች፡፡

የግብርና ሚኒስቴር ዳይሬክተር ዳይሬክቶሪት ደ/ር ለሚ  በቀለ የሚል ዜና አየች፡፡

‹‹እንዴ ሰውዬው ባለስልጣን ነው እንዴ?››

ምንም አልመለሰላትም..ዜናውን ከፍታ ለማንበብ ሞከራች…ከአምስት አመት በፊት የተፃፈ ዜና ነው፡እሱን ተወችና ….ሌላ ፈለገች ..ሶስት አራቱን ከከፈተች በኃላ በአራተኛው ትኩረት ሚስብ ዜና አገኘች‹‹የግብርና ሚንስቴሬ ዳይሬክተር ዳይሬክቶሬት የሆኑት ዶ/ር ለሚ  በቀለ በጤና እክል ምክንያት መልቀቂያ በማስገባት ስልጣናቸውን ለቀዋል ››ይላል፡፡ከአራት አመት በፊት የተለቀቀ ዜና ነው፡፡

ወደፌስብክ ገባችና በስሙ ፈለገች.. ዲአክቲቬት ከሆነ አመታት አልፈዋል፡፡

‹‹ሰውዬው ጥሩ ሁኔታ ላይ አይመስለኝም….ቆይ ለእኔ ተውልኝ››

‹‹ምን ልታደርጊ አሰብሽ….?››

‹‹ያለን ምርጫ አንድ ብቻ ነው፣ቢያንስ አሁን አንድ ነገር አውቀናል..ከአራት አመት በፊት ግብርና ሚኒስቴር ይሰራ ነበር…ስለዚህ አዛ ሄድና አሁን ሚገኝበትን አድራሻ ጠይቃቸዋለው…ቢያንስ ስልኩን ይሰጡኛል፡፡››

‹‹እስቲ እናያለን››ብሎ በረጅሙ ተነፈሰ፡፡

‹‹አይዞህ ምንም አትጨነቅ..ይሄንን ነገር እንፈታዋለን….የፈለገ መስዋእትነት ያስከፍል የአባትህን ምኞት እናሳካለን….ይሄ ጉዳይ ዘሚካኤልንም ወደቤተሰቦቹ እንዲመለስ ለማድረግ ያግዘን ይሆናል፡፡››

‹‹እኔ እንጇ..ዘሚካኤል እናቱን እንደፈጣሪው ነው የሚወዳት..ለእሱ እሷ እንከን አልባ መልአክ የሆነች ሴት ነች…ይሄንን ሲሰማ ዳግመኛ ይበልጥ  እንዳይሰበር ነው የምፈራው፡፡

‹‹አይዞህ ….ከመሰበር በኃላ ያለ መጠገን ነው እኛን ሞርዶ ሙሉ ሰው የሚያደርገን፡፡ደግሞ እናትህ ጥፋት ያጠፋችው  በሚስትነቷ ነው እንጂ በእናትነቷ  እስከወዲያኛው ምሉ እንደሆነች ነው፡፡››
👍6610🥰1
#አላገባህም


#ክፍል_አስራ_ስድስት


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
////

አዲስ አለም በራሷ መኪና ግን ሹፌር እየነዳላት  ከአዳማ ወደአዲስ አበባ እየተጓዘች ነው፡፡

የተቀመጠችው ከኋላ ወንበር ላይ ሲሆን ከግራዋ የራሷ ልጅ ቅዱስ ሲኖር ከግራዋ ደግሞ የፀአዳ ልጅ ምሰር ትገኛለች፡፡

አዲስአለም ወደአዲስ አበባ የምትሄደው እናቷን ለመጠየቅ ነው፡፡ይሄ ቤተሰቦቾ አዳማ ለቀው ወደ አዲስ አበባ ከገቡ በኋላ  በወር ወይም በሁለት ወር አንዴ የምታርገው ነገር ስለሆነ ማንም ለምን እንዴት ብሎ የሚጠይቃት የለም፡፡ምስርን በምን ሰበብ አስፈቅዳ ከእሷ ጋር ይዛት እንደምትመጣ ግን ግራ ገብቷት ነበር፡፡ማታ ነበር ፀአዳ ጋር የደወለች፡፡

‹‹እሺ ጓደኛዬ እንዴት ነሽ?››

‹‹ሰላም ነኝ ምነው ቀን ተገናኝተን ነበር እኮ..በዚህ መሀከል ምን ትሆናለች ብለሽ አሰብሽ?››.

‹‹አንቺ ደግሞ ከአፍሽ ቀና ነገር ቢወጣ ምን አለበት?››

‹‹በይ አሁን ምን ፈልገሽ ነው ወደገደለው ግቢ….››

‹‹በእናትሽ ነገ እነማዬ ጋር አብረን እንሂድ››

‹‹ነገ ››

‹‹አዎ ነገ››

‹‹ያምሻል እንዴ…?ስንት ስራ እንዳለብኝ  ስነግርሽ ውዬ እንዴት የማልችለውን ነገር ትጠይቂኛለሽ?››

‹‹ውይ ለካ ስራ አለብሽ..ብቻዬን መሄድ እኮ ደብሮኝ ነው››

ብቻሽን መሄድ ከደበረሽ  ታዛዥ እና ጣፋጭ የሆነ ምርጥ ባል አለሽ እሱን አስከትለሽ ሂጂ››

‹‹አንቺ እየሰማሽ እኮ ነው››

‹‹ላውድ ላይ አድርሽ ነው እንዴት የምታወሪኝ… አንቺ እኮ ቅሌታም ነሽ….ለነገሩ ሚኪን በተመለከተ መጥፎ ነገር እንደማልናገር እርግጠኛ ስለሆንኩ እንደፈልገሽ››

‹‹መጥፎ ነገር እንደማትናገሪ እኔም ምስክር ነኝ … ውሸት ግን ትናገሪያለሽ..ምን አልባት እንዳልሺው ጣፋጭ ሊሆን ይችላል ታዛዣ ግን አይደለም..ልክ እንደአንቺው ስራ አለኝ አልችልም የሚል መልስ ነው የሰጠኝ››

‹‹በቃ ከልጅሽ ጋር ሒጂ››

‹‹ወይ እንደውም ተውት ከልጆቼ ጋ ሄዳለው…ምስርን ቆንጆ አድርገሽ አሳምሪያትና ወደስራ ስትሄጂ ይዘሻት ውጭ.. በዛው መጥቼ ወስዳታለው››

‹‹ምን እያልሽ ነው?››ፀአዳ እንደመበሳጨት አለች፡፡

‹‹የራስሽው ምክር እኮ ነው፡፡ልጆቹን ይዤ ሄድና ዘና እንላለን…እናንተም ካለልጆቻችሁ ይድላችሁ…እሁድ ማታ ተመልሰን እንመጣለን፡፡››

‹‹አንቺ እኮ የሆነ መዠገር ነገር ነሽ…እኔ ለራሴ ስንት ስራ አለብኝ..?ገና አሁን እሷን ሰውነቷን ሳጥብ..ፀጉሯን ሰሰራ….››

አላስጨረሰቻትም፡፡‹‹በቃ…ጥዋት ሁለት ተኩል አካባቢ ስራ ቦታሽ እመጣና ወስዳታለው..ደህና እደሪ..እወድሻለው፡፡››ብላት ስልኳን ዘጋችው፡፡እንዳለችውም ጥዋት ስትሄድ ፀአዳ ከነንጭንጯ ልጇን ምስርን አስባና አሳምራ ነበር የጠበቀቻት፡፡

‹‹ውይ ጎደኛዬ ንዴት እንደሸወድኩሽ ስታውቂ እንዴት ትናደጂ ይሆን?›› ብላ አሰበችና ብቻዋን ፈገግ አለች፡፡

ሹፌሩ ጎሮ አካባቢ የሚገኘው የቤተሰቦቾ ቤት ካደረሳት በኃላ  ሚካኤል እንዲገዛለት ያዘዘው ዕቃዎች ስለሉ ወደመርካቶ ለመሄድ ተዘጋጀ….

‹‹በቃ ነገ አስር ሰዓት አካባቢ እዚህ ድረስ ››አለችው አዲስ፡፡

‹‹እዚህ የምትንቀሳቀሺበት አይቸግርሽም?››

‹‹ችግር የለውም..የትም የመውጣት እቅድ የለኝም…ምን አልባት የምወጣም ከሆነ ራይድ እጠቀማለው››አለችና ሸኘችው፡፡

ከዛ ልጆቹን ወደቤት አስገብታ እናቷን በቅጡ እንኳን ሰላም ሳትል ነው ወደጓሮ ሄዳ ስልክ የደወለችው፡፡ከሶስት ጥሪ በኃላ ተነሳ‹‹እንዴት ነህ ዘሚካኤል?››

‹‹ሰላም ነኝ..ግን አልተሳካልኝም ብለሽ እንዳታበሳጪኝ››

‹‹አረ ተሳክቶልኛል…መጥተናል እማዬ ቤት ነው ያለነው፡፡››

‹‹በጣም ጎበዝ…..በቃ ጎሮ አካባቢ ነው ያልሺኝ፡፡››

‹‹አዎ… ትክክለኛ አድራሻውን በሚሴጅ ልክልሀለው››

‹‹በቃ..በአንድ ሰዓት ውስጥ እመጣለው››

‹‹ጥሩ ነው..እኛም ገና አሁን መድረሳችን ስለሆነ እስከዛ ከእማዬ ጋ እንጫወታለን…በል ቻው››

‹‹አዲስ በጣም አመሰግናለው…ቻው››

ስልኩ ተዘጋ ፣፣እሷ ግን ፈዛ ቀረች…ከዘሚካኤል ጋር በዚህ መጠን መቀራረብ መቻሏ የተአምር ያህል ነው….ለዘመናት ስታልመውና ስትመኘው የነበረ ነገር ነው፡፡ግን በዚህ መንገድ ይሆናል ብላ ፈፅሞ ሀሳብ አልነበራትም..እሱ የእሷን የልብ ጓደኛ አፍቅሮ እሷ ደግሞ እሱን ከሚያፈቅራት ልጅ ጋር ለማቀራረብ ስትጥር….በራሷ ድርጊት ፈገግ አለች፡፡

‹‹ምን አለበት…. ለሚያፈቅሩት ሰው የሚያፈቅረውን ነገር እዲያገኝ መርዳት ትንሽ ህመም ቢኖረውም ግን ደግሞ ደስ የሚል ስሜት አለው፡፡››አለችና ለስሜቷ ድጋፍ ለመስጠት ሞከረች…የባሏ ሚካኤል ምስል በድንገት መጥቶ አየሩን ሞላው‹‹ፍቅሬ ምን እያሰብሽ ነው…?የገዛ ወንድሜን!!!››ብሎ በሀዘን በተሰበረ ስሜት ሲወቅሳት አየች፡፡

‹‹አንተ ደግሞ ይሄ እኮ ያለፈ ታሪክ ነው….ታውቃለህ እሱን ለማግኘት ስትጥር ነበር ከአንተ ጋር የተቀራረብኩት…ከዛ እሱም ሀገር ጥሎ ጠፋ አንተም ለእኔ ምርጥና ተወዳጅ ሆንክልኝ..እናም  በሙሉ ልቤም ወድጄ አገባሁህ››

‹‹ግን ስታገቢኝ…ወደሽ ነው..ወይስ አፍቅረሺኝ?››

‹‹አይ አንተ ደግሞ ምን ቃላት ትመነዝራለህ….ለማንኛውም..የእሱ ያለፈ የአፍላ የወጣትነት ስሜት ነው..አሁን እየቀረብኩትና እየረዳሁት ያለሁት ያንተ ወንድም ስለሆነ ብቻ ነው››

‹‹እንዴ…!!ምንድነው  ጓሮ ተደብቀሽ ብቻሽን ምታወሪው?››የእናትዬው የመገረም ንግግር ነበር ከገባችበት ቅዠት መሰል ሀሳብ አባኖ ያወጣት፡፡

‹‹አይ እማዬ ..ምንም አይደል ..የሆነ ነገር እያሰብኩ ነበር››

‹‹የሆነ ነገር..ምነው ከሚካኤል ጋር ተጣላችሁ እንዴ?››

‹‹ወይ እማዬ ምንድነው የምታወሪው..?ከሚካኤል ጋር ለምንድነው የምጣለው?››

‹‹ባልና ሚስት ለምንድነው የሚጣሉት?››

‹‹እኔ እንጃ..እኔና ሚኪ ስንጣለ አይተሸን ታውቂያለሽ?››

‹‹እሱ መልካምና ታጋሽ ባል ስለሆነ ነዋ…እንጂማ እንደአንቺ መመነጫጨቅ ቢሆን… ››እናትዬው ነግግሯን ሳታገባድድ አንጠልጥላ ተወችው፡፡

‹‹እማዬ ደግሞ… የእኔ እናት ነሽ  የእሱ?››

‹‹የሁለታችሁም…ባሌ ነው ብለሽ አምጥተሸ ካስተዋወቅሺኝ ቀን ጀምሮ እኮ ልክ እንደአንቺ እሱም ልጄ ሆኗል…በዛ ላይ አሁን ወርቅ የሆነ የልጅ ልጅ ሰጥቶኛል…በይ አሁን ነይ ግቢ ቁርስ ቀርቧል…››አሏትና ተያይዘው ወደውስጥ ገቡ፡፡ 

ዘሚካኤል እንዳለውም ከአንድ ሰዓት በኃላ በራፍ ላይ ደርሶ ደወለላቸው፡፡ተዘጋጅታ ስትጠብቀው ስለነበረ ወዲያውኑ ነው ልጆቹን ይዛ የወጣችው፡፡ከግዙፉ ሀመር መኪናው ወርዶ በራፍን ከፍቶ ቆሞ እየጠበቃቸው ነበር…የስድስት አመቷ ምስር እንዳየችው ደነገጠች…..መጀመሪያ የት እንደምታውቀው ነበር ግራ የገባት..ከዛ የምትወደው ዘፋኝና ተዋናይ መሆኑን ስታውቅ ስሜቷን መቆጣጠር አቅቷት እየተንደረደረች ወደ እሱ መሮጥ ስትጀምር እሱም ከቆመበት እጆቹን ዘርግቶ ወደእሷ ተንቀሳቀሰ…እቅፉ ውስጥ ወደቀች.. ጭምቅ አድርጎ አቀፋትና በአየር ላይ አንጠለጠላት..የምስርን ድርጊት ያየው ቅዱስ እጆቹን ከእናቱ እጅ አስለቅቆ ኩስ ኩስ እያለ ምስር እንዳደረገችው ወደዘሚካኤል ሮጠ….አዲስአለም በልጆቹ ያልተጠበቀ ድርጊት  በድንጋጤ አፏን ከፈተች ….ሚካኤል ቅዱስ ስሩ ሲደርስ ምስርን ወደአንዱ እጁ አዘዋወራትና ጎንበስ ብሎ ቅዱስን አቅፎ ወደላይ አነሳውና ጉንጮቹን እያገላበጠ ሳመው…..በዚህ ጊዜ አዲስ አለም ከመደነቅ ሳትወጣ ስራቸው ደርሳ ነበር፡፡

‹‹ቆይ ከእነዚህ ልጆች ጋር ከዚህ በፊት ትተዋወቁ ነበር እንዴ?››

ጉንጮቾን እያገላበጠ ሰማት..ትንፋሹ ልክ ሰው ፊት ላይ እደሚበትን አደንዛዥ ዕፅ ኃይል አለው…
👍6612
#አላገባህም


#ክፍል_አስራ_ሰባት


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ

///
ጭልጥ ያለ እንቅልፍ ውስጥ ነው፤ የሆነ የሚንጠጣረር ነገር እያደነቆረው ነው፡፡በመከራ ነው ከእንቅልፉ የነቃው…የበራፉ መጥሪያ ድምፅ መሆኑ አወቀ..ስልኩን ከኮመዲኖ ላይ አነሳና ሰዓቱን ተመለከተ፡፡ለአንድ ሰዓት ሩብ ጉዳይ ይላል፡፡ያልተለመደ ነገር ነው፡፡በዚህ ሰዓት ማን ነው በራፍን መጥሪያ የሚያንጣርረው?፡፡የፅዳት ሰራተኛዋ እንደማትሆን እርግጠኛ ነው፡፡እሷ አንደኛ በዚህ ሰዓት አትመጣም…ብትመጣም የራሷ የሆነ ቁልፍ ስላላት እሱን የምትቀሰቅስበት ምንም  አይነት ምክንያት የላትም….መኝታውን ለቆ ተነሳና ጋዎኑን ደርቦ መኝታ ቤቱን ለቆ ወጣ፡፡፡ሳሎን ደርሶ በራፉን ሲከፍት..እየተመለከተ ያለው  ፈፅሞ በአእምሮው ያልጠበቀውን ነው፡፡ፊቱን በጥፊ ደረቱን በጡጫ እየቀጠቀጠች ገፍትራ ወደውስጥ አስገብታ ትቦጫጭረው ጀመር….‹‹ምን አድርጌሀለው..?እንዴት በልጄ ስሜት እንደዛ ትጫወታለህ..?ምን አይነት አረመኔ ሰው ብትሆን ነው?፡፡››
እንደዚህ አውሬ የሆነች ሴት በእድሜ ዘመኑ አጋጥሞት  አያውቅም፡፡ፊቱን ከብጭሪያ ለመከላከል ሁለቱን  እጆቹን በፊቱ ዙሪያ አድርጎ ለመከላከል ሞከረ፡፡
‹‹አረ ፀዲ ተረጋጊ….››
‹‹አልረጋጋም..እንዲህ አሳብደሀኝ እንዴት ነው የምረጋጋው…..?ልጄን እንዴት እንዳሳደኩዋት ታውቃለህ…?››መደባደቧን እና ጮኸቷን አላቆረጠችም….እንባዋ ከቁጥጥሯ ውጭ ሆኖ እየረገፈ ነው፡፡ትናንት የሆነውን ከሰማችበት ደቂቃ ጀመሮ ማልቀሷን አላቆረጠችም… ለሊቱን እንቅልፍ ባይኗ ሳይዞር ስትቃጠልና ስትነፈርቅ ስላደረች የእናቱን ሞት አዲስ እንደተረዳ ሀዘንተኛ አይኖቾ ከማበጣቸውም በላይ ክፍኛ ደፍርሰዋል፡፡
ዘሚካኤል መከላከሉ ብቻ እንደማያዋጣ ገባው፡፡እንደምንም አለና ሁለት እጆቾን ያዘና ስቦ ከሰውነቱ ጋር አጣበቃት፡፡
‹‹ልቀቀኝ..ከዚህ ቀፋፊ ሰውነትህ ጋር መነካካት …..››አላስጨረሳትም የተከፈተ አፏን በአፉ ከደነው….በተቻላት መጠን ተወራጨች…ከእሱ ፈርጣማና የዳበረ ጡንቻ ማምለጥ አልቻችም…ከንፈሩን ነከሰችው….ለቀቃትና..ተስፈንጥራ ወደኃላ ልታመልጥ ስትል መልሶ በመያዝ ሙሉ በሙሉ ከስር ገብቷ ተሸከማት……እንደእፃን ልጅ በእግሯም በእጇም ተወራጨች… ወደሶፋው ይዟት ሄደ…ሶፋው ላይ ሊወረውረኝ ነው ብላ ስትጠብቅ እሷን አጥብቆ እንደያዘ እግሩን ዘረጋና ከሳፋው ላይ አንዱን ትራስ ወደወለሉ አወረደ….በፍጥነት ገለበጣትና እንደህፃን አቅፎ ወደታች በጉልበቱ ተንበረከከ እና ወለሉ ላይ አስተኛት…ሾልካ ከስሩ ለማምለጥ ታገለች… በጥንካሬ ጨምቆ ከወለሉ ላይ አጣበቃትና ጭንቅላቱን ቀና አድርጎ ትራሱ ላይ አስደገፋት …እንዳይጨፈልቃት በመጠንቀቅ እላዩዋ ላይ  ተቀመጠ…የለበሰውን ጋወን አውልቆ ወረወረው….
‹‹ምን ልታደርግ ነው?››አይኗቾ በድንጋጤ ፈጠጡ፡፡
ወደታች ጎንበስ አለና የለበሰችውን ቲሸርት ከግራና ከቀኝ ይዞ ወደታች ተረተረው….የመጨረሻውን ንዴት በመናደዷ ምክንያት ደምስሯ ተግተረተረ‹‹ምን እያደረክ ነው? ልትደፍረኝ ነው እንዴ..?እከስሀለው…ስምህን ነው ያማጠፋው….››የቀራት ብቸኛ መከላከያ ምላሷ ብቻ ነበር….ልታስፈራራው ሞከረች ፡፡ተንጠራራና ሌላ ትራስ አምጥቶ ከጎኗ በማድረግ ከላዬ ላይ ወርዶ ከጓና ተኝቶ ወደራሱ ገለበጣትና አቀፋት፡፡
ከታች እሱ በቁምጣ ሲሆን እሷ ደግሞ ልክ እንደወትሮዋ ጅንስ ሱሪ እንደለበሰች ነው፡፡
‹‹በፈጠሪ ስትበሳጪ እንዴት ነው የምታምሪው?፡፡››
‹‹እያሾፍክብኝ ነው?››
‹‹በፍፅም ..አይገባሽም እንዴ ..?ካንቺ ፍቅር ይዞኛል…ላገባሽ እፈልጋለው››
ምትሰማውን ቃል ማመን አቃታት‹‹ይሄ ደግሞ ሌላ ቀልድ መሆኑ ነው?ሕይወት እንደምትተውነው ተውኔት መሰለህ?››
‹‹እሱ እንዳያያዝሽ ነው …እኔ ግን የተናገርኩት ከልቤ ነው…ከፈለግሽ ዛሬውኑ ሄደን መጋባት እንችላለን…እንደማገባሽ እግጠኛ ስለሆንኩ ነው ምስርን ልጄ ነች ያልኩት፡፡››
‹‹እንዴት እሺ ትለኛልች ብለህ አሳብክ?››
‹‹እንደምትወጂኝ አይኖችሽ ውስጥ ስላነበብኩ››
የተፋቀረ ሁሉ ይጋባል ያለህ ማን ነው….ደግሞ እወቅ እኔ ፍቅር አልፈልግም…አሁን ልቀቀኝ ..ከአንተ እስከወዲያኛው መሸሽና መራቅ ነው የምፈልገው፡፡››
‹‹አይ ከአኔ ሸሽተሸ ማምለጥ  አትችይም፡፡››
‹‹ልቀቀኝ አልኩ..›› ለመመናጨቅ ሞከረች አጥብቆ ያዛትና ከንፈሯ ላይ በድጋሚ ተጣበቀ… ሳላሳ ሰከንድ ያህል ብቻ ነው መታገል የቻለችው..ከዛ ቀስ በቀስ እየለዘበች…  የእጆቾ ጡንቻዎች እየለሰለሱ ..ከንፈሯቾ ለከንፈሮቹ መልስ እየሰጡ መጡ…እሱን ሲቧጭሩ እና ሲደበድብት የነበሩት ጣቶቹ ጀርባውናና መላ ሰውነቱን ማሻሸት ጀመሩ…ከዛ እሱ ቁምጣውን ሲያወልቅ እሷም በገዛ እጇቾ ጅንስ ሱሪዋን እያወለቀች ነበር….እዛ ግዙፍ የሳሎን ወለል ላይ 30 ለሚሆኑ ደቂቃዎች በፍቅር እየተንከባለሉ እና ከኮርነር  ኮርነር እየተሸከረከሩ በጣር የታጅበው ወሲብ ሲሰሩ በራፉ ክፍት መሆኑን እንኳን አላስተዋሉም ነበር፡፡
ከወሲብ በኃላ አርቃኗን ሆና ‹‹አንተ ምን አይነት አዚም ነው ያለህ ግን?››ስትል ባለማመን ጠየቀችው፡፡
‹‹ያው የፍቅር አዚም ነዋ››
‹‹አይ አይመስለኝም…..የሆነ  የሚያደነዝዝ አይነት መስተፋቅርማ አለህ…አሁን ሻወር ቤቱን አሳየኝ..››አለችው፡፡
ከተዘረረበት ወለል እየተነሳ ወደእሷ ሄዶ ከስር ተሸክሞ ወደምኝታ ክፍሉ ተሸክሟት ገባ….‹‹ያው ግቢና ታጠቢ››
‹‹እሺ…ቲሸርቴን ቀዳደሀዋል….አሁን ምን ልለብስ ነው?››እያለች ገባች፡፡
‹‹አታስቢ አዘጋጅልሻለው….ግን አብሬሽ ሻወር መውሰድ እፈልጋለው፡፡››
‹‹ስርአት ይዘህ የምትታጠብ ከሆነ ትችላለህ›› አለችው፡፡በደስታ እርቃኑን ገባና ተቀላቀላት…መታጠብ ጀመሩ፡፡ ቃል እንደገባው ግን ስርዓት ይዞ አልታጠበም..እሷም በቃላት አውጥታ አትናገር እንጂ ስርዓት የለሽ መሆኑን ፈልጋው ነበር..ከዛ ሻወር ቤት ለመውጣት አንድ ሰዓት በላይ ነበር የወሰደባቸው፡፡ ከዛ ተያይዘው ሲወጡ ሁለቱም ሰውነታቸውን ማዘዝ እስኪያቅታቸው ዝለው ነበር.. ርቃናቸውን ተያይዘው አልጋ ውስጥ ነው የገቡት…ሁለት ሰው መሆናቸውን መለየት እስኪከብድ ድረስ ሙሉ በሙሉ ተቃቅፈው ለሞት የተቃረበ እንቅልፍ ውስጥ ገቡ፡፡
///
ተመሳሳይ የበራፍ ተደጋግሞ መንጫረር ነበር ከእንቅልፉ ያባነነው..‹‹ዛሬ ደግሞ ምን ጉድ ነው ?››በማለት እየተነጫነጨ…እንደምንም ነቅቶ ስልኩን ሲመለከት..ከ30 በላይ ሚስኮል ነበረው…ሰዓቱን ሲመለከት 7ሰዓት ተኩል ሆኗል…ማመን አልቻለም፡፡ይሄ ሁሉ ሚስኮል ከማን ነው ብሎ ሲያየው አብዛኛው ከአዲስአለም ነው…ስለፀደይ ተጨንቃ እንደሆነ ገመተ ..አልጋውን ለቆ ሲወርድ ፀደይ እራሷን አታውቅም፡፡
ጋወኑን ቅድም ሳሎን ወለል ላይ ትቶት ስለነበረ….ቁምጣ እና ቲሸርት ለበሰና በድኑን እየጎተተ ወደ ሳሎን ሄዶ በራፉን ሲከፍት ክፍኛ የደነገጠችውና አይኗ  የፈጠጠው አዲስአለም በራፉ ላይ ተገትራለች
‹‹እዚህ አልመጣችም…?ወይኔ ጓደኛዬ….›
‹‹አረ ተረጋጊ..ግቢ ››
ወደውስጥ አስገባትና በራፉን መልሶ ዘግቶ ተመለሰ‹‹እሺ የት ሄደች ይባላል ?አንተ ደግሞ ለምንድነው ስልክህን የማታነሳው?››
‹‹አሁን ተረጋጊና ከተቻለሽ ቆንጆ ምሳ ስሪልን››
‹‹ምን እያወራህ ነው?ፀደይ ጠፍታለች እኮ ነው የምልህ››
👍6014
#አላገባህም


#ክፍል_ሀያ


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
///

ዘሚካኤል እንግዳው ላይ አፍጥጦ

‹‹አይ ምንም እየገባኝ አይደለም….?››አለ

ሰውዬውም ዘሚካኤል‹‹ቁጭ በል አስረዳሀለው..››አለና ወደውስጥ ገብቶ ቀድሞ ተቀመጠ…

ፀደይ  ዘሚካኤልን እየጎተተች ይዛው መጣችና አስቀመጠችው…እሷም ተቀመጠችን ስልኳን አውጥታ ሪከርድ ላይ አደረገችና ሰውዬው የሚናገረውን ለመስማት ዝግጁ ሆነች፡፡

‹‹ምን ድረስ ታውቃላችሁ?››

‹‹እኔ ምንም የማውቀው ነገር የለም››ዘሚካኤል በትግስተ የለሽነት መለሰ፡፡

ፀደይ ዝም አለች‹‹ጥሩ ከመጀመሪያው ብጀምርላችሁ ችግር የለውም..እኔ እና እናትህ የልጅነት ጓደኛሞች ማለት ፍቅረኛሞች ነበርን…በጣም ነበር የምንዋደደው…..ምንጊዜም ስለመጋባትና ዕድሜ ዘመናችንን ሙሉ አብሮ ስለመኖር ነበር የምናስበው…ከዛ ድንገት አባቴ ወደአሜሪካ መሄድ አለብህ አለኝ…ብዙ ወንድሞቹ እዛ ስላሉ ሀሳቡን ላስቀይረው አልቻልኩም….አባቴን በጣም ነበር የምፈራው..ከዛ ጥያቄውን ተቀብዬ ወደአሜሪካ ሄድኩ…ለካ እሷ በወቅቱ እህትህን ፀንሳ ነበር..፡፡››

‹‹ፀንሳ ማለት …ከማን?››

‹‹ከማን ይሆናል ከእኔ ነዋ››

‹‹እና እህቴ የአንተ ልጅ ነች…?.ምንድነው የምትቀባጥረው?››

‹‹አልቀባጠርኩም..ከፈለክ አባትህን ጠይቀው …ያውቃል…እናትህ እኔ ጥያት ስለሄድኩ በጣም ተበሳጭታብኝ ስለነበር እና በዛ ላይ አርግዛ ስለነበር…ወዲያው አባትህን አገባችው…ስታገባው..ለልጇ አባት ለማግኘት አንጂ አፍቅራው አልነበረም…እሱም ይወዳት ስለነበረ ተንከባከባት….እህትህም በሰባት ወር እንደተወለደች ነበር ያሰበው…የገዛ ልጁ ነበር የምትመስለው….ስለዚህ ትርሲትን  እንደልጁ አሳደጋት..ከዛ አንተ እና ወንድምህ ተወለዳችሁ፡፡እኔም ከሀያ አመት ቆይታ በኃላ ከአሜሪካ ተመለስኩ፡፡ለእሷ የነበረኝ ፍቅር ከውስጤ ስላልበረደ ፈልጌ አገኘኋት…በጣም ተበሳጭታብኝ የነበረ ቢሆንም ታፈቅረኝ ስለነበረ በሂደት ይቅር አለቺኝ…አባትህን  ፈታ እኔን እንድተገባኝ እጨቀጭቃት ጀመር…እሷም ምንም እንኳን ከእኔ ጋር ለመጋባት በጣም ፍላጎት ቢኖራትም እናንተን መበተን ስላልፈለገች በሀሳቤ ልትስማማ አልቻለችም፡፡

እኔም እሷን ትቼ ሌላ ሴት ማግባት ብሞክርም አልቻልኩም..አቃተኝ…ከዛ በቃ አንቺ እሺ ብለሽ ባልሽን ፈተሸ ማታገቢኝ ከሆነ ቢያንስ ልጄን የማግኘት መብት አለኝ..ለልጄ አባቷ እኔ እንደሆንኩ ንገሪያት እያልኩ በዚህ መጨቃጨቅ ጀመርን፡፡እሷም ያንን ማድረግ አልችልም እያለች መከላከል ጀመረች፡፡በዚህ ሁሉ ጊዜ ግን በድብቅ እየተገናኘን ፍቅራችንን እንወጣ ነበር…

‹‹ለምን ያህል ጊዜ ከአባቴ እየተደበቃችሁ ..እንደዛ አደረጋችሁ?››ግሽግሽ ባለና ጥላቻ በተጫነው ስሜት ጠየቀው፡፡

‹‹አራት ወይም አምስት አመት››መለሰለት

‹‹እና አባቴ ይሄን ሁሉ ታሪክ ሲያውቅ ነዋ ..ቀልቡን ነስቶት ያንን  ወንጀል የፈፀመው?››

‹‹አይ አይደለም…ስለዚህ ጉዳይ ሳስብ እስከዛሬ ድረስ ራሴን መቆጣጠር እስኪያቅተኝ  አዝናለው..እመነኝ በጉዳዩ በጣም መፀፀት ብቻ ሳይሆን ብዙ ነገሬን አጥቼበታለው….፡፡ ስራዬን፤ ጤናዬን …ብዙ ብዙ ነገር…ብዙ ጊዜም ራሴን አጥፍቼ ከልጄ ትርሲት እና ከእናትህ ጎን ለመተኛት ሞክሬ ነበር..ግን በሆነ መንገድ እተርፋለው…መጨረሻ ይሄው እንደምታየኝ የአያቴ መንደር መጥቼ በዚህ አይነት ሁኔታ መኖር ጀመርኩ..ትንሽም ወደእዚህ ከመጣሁ ነው ጤነኛ የሆንኩት››

‹‹ሰውዬ እኔ ያንተን ፀፀት ለመስማተ  ምንም አይነት ፍላጎት የለኝም..ስለዋናው ጉዳይ ንገረኝ››

‹‹ትዝ ይለኛል ቀኑ እሁድ ነበር….በእለቱ አባትህ ሞጆ የጓደኛው ለቅሶ ስለነበረ መሄዱን እናትህ ስትነግረኝ..መኪናዬን ከአዲስአበባ አስነስቼ አዳማ ሄድኩ ፡፡እናትህን ተቀጣጥረን ስለነበር ቡቲክ አገኘኋት …እሁድ በዛ ላይ ጥዋት  ስለሆነ የገበያ ግር ግር አልነበረም.. ከዛ የተወሰነ ከቆየን በኃላ የተለመደ ጭቅጭቃችንን ጀመርን‹‹ …ለልጄ አባቷ መሆኔን ወይ ቀድመሽ ንገሪያት ወይ እነግራታለው››አልኳት፡፡

‹‹እሷ ቅጣውን በልዩ ሁኔታ ነው የምትወደው …አባትሽ ቅጣው አይደለም ብላት ልጄ በጣም ነው ምትጎዳው››አለቺኝ፡፡

‹‹ብትጎዳም ለጊዜው ነው…ከውሸት ጋር ለዘላለም ከምትኖር እውነቱን አውቃ ለትንሽ ጊዜ ብትጎዳ ይሻልል››አልኳት
በዚህ ጉዳይ ላይ ለ30 ደቂቃ ለበለጠ ጊዜ በከረረ ሁኔታ ስንከራከር ቆየን….ከዛ የስልክ ንግግር ድምፅ ነው  ሁለታችንንም ያነቃን….

እህትህ ትርሲት ከባንኮኒው ማዶ … ፊቷ በእንባ ታጥቦ…አይኖቾ ፈጠውና  አውሬ መስላ ቆማለች..ሱቁ ውስጥ ገብታ እዛ የቆመችበት ቦታ መች እንደቆመች አናውቅም..ምን ያህሉን እንደሳማችንም አናውቅም….ከሁኔታዋ እንደሚታው ግን የሚበቃትን ያህል እንደሰማችን ያስታውቃል…ሁለታችንም በርግገን ጎን ለጎን ተጣብቀን ከተቀመጥንበት ተነሳን….

‹‹ለማን እየደወለች ነው?››ሁለታችንም ግራ ተጋባን፡፡ወዲያው ስልኩ ተነሳላትና ማውራት ጀመረች፡፡

‹‹አባዬ  ….ያንተ ልጅ አይደለሁም እንዴ…?እማዬና ውሽማዋ ሲያወሩ ሰማው…አባዬ እኔ ያንተ ልጅ ካልሆንኩ መኖር አልፈልግም…የሌላ ሰው ልጅ መሆን በጣም ነው የሚቀፈኝ…አይ አልጠብቅህም ..በጣም ነው የምወድህ….››አለችና ስልኩን ግድግዳው ላይ ወርውራ ከሱቁ ወጥታ ተፈተለከች፡፡ልንደረስባት ሞከርን ግን ወዲያው ተሰወረችብን፡፡

‹‹ወይኔ ልጄ….ወይኔ ልጄ…››እናትዬው ተርበተበተች....እኔም የምይዝው የምጨብጠው ግራ ገባኝ….ሱቁን ዘጋንና….

‹‹ወደየት ነው የሄደችው?››ስል እናትህን ጠየቅኳት፡፡‹‹እኔ ምናውቃለው..ወደቤት ከሄደች…ሄጄ ልያት››አለችኝ

‹‹በቃ ነይ መኪና ውስጥ ግቢ››ስላት

‹‹እንዴ ..አንድ ላይ ስንሄድ..?››

‹‹አሁን እኮ ነገሮች ተደበላልቀዋል…ምንፈራው ሳይሆን የምንጋፈጠው ነው››አልኳትና እየጎተትኩ መኪናዬ ውስጥ ይዣት ገባው፡፡በየመንገዱ እየፈለግናት…ልትሄድ ትችልበታለች ብላ እናቷ የጠረጠረችበት  አንድ ሁለት ቦታ አቁመን አይተን መጨረሻ ወደቤት ሄድን…መኪናውን ራቅ አድርጌ እንዳቆም አደረገችኝና…‹‹እኔ ገብቼ ልያትና ካለች እነግርሀለው..ከሌለችም ሌላ ቦታ ሄደን እንፈልጋታለን›› ብላኝ ገባች፡፡እኔም በጭንቀት እየተንቆራጠጥኩ መጠበቅ ጀመርኩ…5 ደቂቃ ..10 ደቂቃ አለፈ..ስልኬን አውጥቼ ስደውል እናትህ ሞባይል አይነሳም…ራሴን መቆጣጠር አቃተኝና የሆነው ይሁን ብዬ ወደግቢው ገባው፡፡ሳሎኑ በራፍ እንደተከፈተ ነበር…ስገባ  ልጄ ኮርኒሱ ላይ ተንጠልጥላለች..እናትህ ደግሞ የገዛ ሆዷን ላይ ቢላዋ ሽጣ ተዘርራለች፡፡ይመስለኛል እናትህ ወደቤት ስትገባ እህትህ ተሰቅላ እራሷ አጥፍታ ስታያት ወዲያው አካባቢው ላይ ያገኘችውን ቢላዋ ሆዷ ውሰጥ የሻጠችው ይመስለኛል፡፡

ከዛ ደንዝዤ የምሆነው ጠፋኝ…ምን ላድርግ ..?ልጄን ከተሰቀለችበት ለማውረድ ገመድ መቁረጫ ለመፈለግ ወደውስጥ ገብቼ መቁረጫ ይዤ ስመለስ አባትህ ከውጭ ከሳሎኑ ሲገባ አየሁት፡፡በደመነፍስ ወደ ጎሮ በራፍ ሄድኩ…ዞሬ ከግቢው ወጣሁና መኪናዬ ውስጥ ገብቼ ደም እንባ እያለቀስኩ ሁኔታዎችን መከታተል ጀምርኩ፡፡ ከዛ አንተና ወንድምህ አንድ አይነት ሰማያዊ የስፖርት ልብስ ለብሳችሁ ወደቤት ስትገቡ ተመለከትኩ፡፡ ከደቂቃዎች በኃላ ፖሊሶች ሰፈሩን ወረሩት…እናንተንም አባታችሁንም ፖሊሶች ይዘዋችሁ ሲሄድ የእናትህንና የእህትህን አስከሬን በአንብላንስ ሲወሰድ ከመንገድ ማዶ መኪናዬ ውስጥ ተቀምጬ እየተመለከትኩ ነበር፡፡ ሁለቱም እራሷቸውን  እንዳጠፉ እርግጠኛ ነኝ፡፡
👍6415
#አላገባህም


#ክፍል_ሀያ_አንድ


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ

/////
ዘሚካኤል ስቲዲዬ ቆይቶ ገና ወደቤት እንደገባ ነበር ስልኩ የጠራው፡፡

የደወለችለት አዲስ አለም ነበረች፡፡የጠበቀው ሚካኤል ይደውልልኛል ብሎ ነበር ፡፡ከአባቱ ጋር የሚገናኙበትን ቀን ከወህኒ ቤቱ አስተዳዳሪ ጋር ተነጋግሮ እንደሚደውልለት ነገሮት ነበር፡፡እና ይሄን ቀን በፍርሀትና በጉጉት ነበር እየጠበቀ ያለው፡፡ስለአባቱ ዜና ለመስማት፡፡ስልኩን አነሳው፡፡

‹‹ሄሎ አዲስ እንዴት ነሽ?››

‹‹ሰላም ነኝ አንተስ?››

‹‹እኔ በጣም ደህና ነኝ…ሚካኤል ይደውልልኛል ብዬ እየጠበቅኩ ነበር፡፡››

‹‹ይደውልልሀል..አሁን ኩማንደሩ ቀጥሮት ሊያገኘው ሄዶል …ከእሱ እንደጨረሰ እርግጠኛ ነኝ ይደውልልሀል፡፡…አታስብ ኩማንደሩ ደግሞ ያንተ አድናቂ ስለሆነ ከአባታችሁ እንድትገናኙ ሁኔታውን ያመቻቻል….በዛ እርግጠኛ ነኝ፡፡››አለችው

‹‹ጥሩ ታዲያ አንቺ ሰላም ነሽ?››

‹‹በጣም ሰላም ነኝ…ግን አንድ ጥያቄ ልጠይቅህ  ነበር››

‹‹ምን?››

‹‹ከፀዲ ጋር እንዴት ናችሁ?››

ያልጠበቀውን ጥያቄ ነው የጠየቀችው‹‹በጣም አሪፍ ነን…ከቦንጋ ከተመለስን በኋላ በአካል ባንገናኝም በስልክ ግን በቀን ሁለት ሶስት ጊዜ እንደዋወላለን…እንደውም የፊታችን ቅዳሜና እሁድ ከከተማ ወጣ ብለን ለማሳለፍ ተነጋግረናል፡፡

ግን ምነው ጠየቅሺኝ?››

‹‹ግልፅ ሆነህ ንገረኝ…ስለእሷ ምን ታስባለህ..ማለቴ አሁንም በፊት እንደነገርከኝ ታፈቅራታለህ?››

‹‹እንዴ!እንዴት በአንድ ወር ፍቅሩ ይተናል ብለሽ አሰብሽ? እንደውም ጥሩ ነገር አነሳሽልኝ…የሆነ ቀን አመቻችቼ ካንቺ ጋር መነጋገር እፈልግ ነበር..እኔ ላገባት እፍልጋለው..በቅርብ ቀን..እና እንዴት ጠይቄ ላሳምናት የሚለውን ከእኔ ይልቅ አንቺ ስለምታውቂ እንድታማክሪኝ እፈልጋለው፡፡››

‹‹እንግዲያው እንደዛ ከሆነ ሳይረፍድብህ ፍጠን››

‹‹አልገባኝም?››

‹‹ያንተን ልጅ አርግዛለች..››

የሰማውን ነገር ማመን አልቻለም…በደስታ ጮኸ…

‹‹ማለት…በፈጣሪ እየዋሸሺኝ አይደለም አይደል? ››

‹‹አርግዛለች..ለእኔም አልነገረችኝም ፡፡

በአጋጣሚ አንድ የግል ሆስፒታል  ካርድ ክፍል የምትሰራ ወዳጅ ነበረችኝ …አሁን ከደቂቃዎች በፊት ደውላ  ጓደኛሽ ፀንሳ እኛ ሆስፒታል  ለማስወረድ መጥታ ነበር…ብላ ነገረችኝ፡፡መጀመሪያ አላመንኩም ነበር..በኋላ ግን ሆስፒታሉ ድረስ ሄጄ በሌላ መንገድ እራሷ መሆኗን አረጋግጬያለው…ልታስወርደው ለተነገወዲያ ቀጠሮ አሲይዛለች….ቀጥታ ላናግራት ፍልጌ ነበር….ጭራሽ እልክ ትጋባለች ብዬ ስለፈራሁ ምንም ልላት አልቻልኩም…አንተ ምታደርገው ነገር ካለ ሞክር››

‹‹ወይኔ በፈጣሪ..ለእኔ አረገዘችልኝ…..››በበቃ ቻው አዲስ አንቺ አትጨነቂ እኔ አስተካክለዋለው፡፡

የአዲስን ስልክ ከዘጋ በኃላ ቀጥታ ልብሶቹ በሻንጣ  መክተት ነው የጀመረው፡፡ሁለት ሻንጣ ልብስና በወሳኝ የሚፈልጋቸውን ነገሮች ሰበሰበና አፓርታማውን ለቆ ወጣ …ቀጥታ ወደአዳማ ነው የነዳው፡፡

ፀአዳ ቤት ሲደርስ በራፏ ዝግ ነበር..ሊደውልላት አልፈለገም ፡፡ሻንጣውን አወረደና በራፏ በረንዳ ላይ አድርጎ እሱ መኪናው ውስጥ ሆኖ መጠበቅ ጀመረ…ከምሽቱ አንድ ሰአት ስትመጣ እሱ መኪና ውስጥ ሻንጣው በረንዳ ላይ ሆኖ ስታየው ፍፁም ነው ግራ የተጋባችው…ምስር  እሱ መሆኑን ስታውቅ ከእናቷ ተነጥላ ወደእሱ መሮጥ ስትጀምር እሱም ፈጥኖ ከመኪናው ወረደና እጇቹን እንደክንፍ ዘርግቶ ጠበቃት…ተጠምጥማበት በደስታ ጉንጩን ትስመው ጀመር…
ወደቤት እንደገቡ ፀደይ‹‹ምንድነው ጉዱ?››ስትል ጠየቀችው፡፡

‹‹ምንም ..ለጥቂት ሳምንታት እረፍት ስለሆንኩ እዚህ ከእናንተ ጋር ለመቆየት ወስኜ ነው፡፡››

‹‹እዚህ ከእኛ ጋር?››

‹‹አዎ ከእናንተ ጋር››
ህፃኖ ምስር ‹‹ታድለን…ታድለን›› እያለች መጨፈር ጀመረች፡፡

ፀአዳ ልጇ ምስር ፊት ምንም ማለት አልቻለችም.‹‹እንግዲያው እደቤትህ ዘና በል…እኔ ልብስ ልቀይር ››አለችና መኝታ ቤት ገባች፡፡ከዛ እራት ሰርታ በሉና ከሶስት ሰዓት በኃላ ምስርን አስተኝተው ነበር እንደአዲስ ጭቅጭቁን የጀመሩት፡፡

‹‹ምን እየሰራህ ነው?››

‹‹እንደምታገቢኝ ቃል ገብተሸ ቀለበት እስክታስሪልኝ ድረስ ከዚህ ቤት ወጥቼ ወደቤቴ አልመለስም››ሲል ቁርጡን ፍርጥም ብሎ ነገራት፡

‹‹ጭራሽ ማግባት? እየቀለድክ ነው፡፡››

‹‹በፍፅም …ብቀልድ ነው እንደዚህ አይነት እርምጃ የወሰድኩት፡፡››

‹‹ስማ..እኔ ካንተ ጋብቻ ፍቅር ምናምን አልፈልግም››

‹‹ታዲያ ምንድንው ምትፈልጊው?››

ትኩር ብላ አየችው….
‹‹ንገሪኝ ከእኔ ምንድነው የምትፈልጊው….. ?››

‹‹ካንተ ወሲብ ብቻ ይበቃኛል….ማለቴ እስከአሁን የደረግነውን ለማለት ነው …ደግሞ  አሁንም እናድረግ እያልኩህ አይደለም፡፡››

በንግግሯ ሆድን እስኪያመው ሳቀ…በመሀል ስልክ ተደወለለት ..ከወንድሙ ነበር…በጉጉት አነሳው‹‹እሺ ሚካኤል ደህና አመሸህ?››

‹‹ሰላም ነኝ…ነገ ጥዋት ሶስት ሰዓት ላይ አዳማ መገኘት ትችላለህ?››

‹‹ምነው ?አባዬን እንድናገኝ ፈቀዱልን እንዴ?››

‹‹አዎ በጣም ደስ የሚለው ደግሞ አንድ ላይ እንድናገኘው ነው ያመቻቹልን ቅር ካላለህ አዲስንና ቅዱስንም ይዘናቸው እንሄዳለን››

‹‹አረ ቅር አይለኝም ጥሩ ሀሳብ …ግን አባዬ እኔን ለማናገር ፍቃደኛ የሚሆን ይመስልሀል?››ሰሞኑን ሲብሰለሰልበት የነበረውን ስጋቱን አንስቶ ጠየቀው፡፡

‹‹ትቀልዳለህ እንዴ…ከመሞቱ በፊት ማግኘት የሚፈልገው ብቸኛ ነገር እኮ አንተን ማናገር ነው…በደስታ  ነው የሚያነባው….እንኳን በአካል አግኝተሀው አባዬ ብለህ ስጠራው ሰምቶ ይቅርና ባለፈው ፎቶህን ሳሳየው እንዴት እያገላበጠ ሲስምና ሲያለቅስ እንደነበረ እኔ ነኝ የማውቀው…በል በዛ እርግጠኛ ሁን..ምንም አትጨናነቅ፡፡››

‹‹ምን ያስፈልገዋል…?ማለት ምን ይዤለት ልሂድ?››

‹‹የሚያስፈልገወን ነገር ሁሉ አዘጋጅተናል…አንተ ደግሞ ሚፈልገውን ነገር እንጠይቀውና በሚቀጥለው ዙር ትወስድለታለህ…ደግሞ ደስ የሚለው ከቦንጋ ያመጣችሁትን ከዶ/ሩ ጋር ያደረጋችሁትን ውይይት ለኩማንደሩ አሰምቼው በጣም ነው ያዘነው..እናም አባዬን ከሌሎች እስረኞች ጋር ተቀላቅሎ እንዲኖር ወስነዋል…››

‹‹በጣም የሚያስደስት ነገር ነው እየነገርከኝ ያለሀው..ወንድሜ በጣም ጥሩ ሰው እንደሆንክ ታውቃለህ አይደል… በጣም ነው የምኮራብህ፡፡››

ሚካኤልም እንባ እየተናነቀው‹‹እኔም በጣም ነው የምኮራብህ››አለው

‹‹በቃ እሺ …...ሶስት ሰዓት ነው ያልከኝ አይደል?፡፡››

‹‹አዎ…መድረስ ትችላለህ አይደል…?››

‹‹በደንብ እንጂ ሁለት ተኩል ደርሼ ደውልልሀለው››

‹‹ጥሩ በቃ ደህና እደር››ስልኩን ዘጋ፡፡

ንግግራቸውን ሁሉ በገረሜታ ስትሰማ የነበረችው ፀደይ‹‹እርግጠኛ ነህ ግን ሁለት ተኩል ትደርሳለህ?››ስትል በፈገግታ አሾፈችበት፡፡

‹‹ትቆጪኛለሽ ብዬ ነው እንጂ እዚህ ነኝ ልለው ነበረ››

‹‹ልፋ ቢልህ ነው ….ግን ለእናንተ ደስ ብሎኛል››

‹‹ማለት?››

‹‹አንተና ወንድምህ እንዲህ እየተደዋወላችሁ በሰላም ማውራት መቻላችሁ ትልቅ ነገር ነው…አረ እንደውም ከመነጋጋርም አልፋችሁ መሞጋገስ ጀምራችኃል››

‹‹እድሜ ለአንቺ ….ባንቺ ቀናነትና ጥረት ነው ለዚህ የበቃነው….››

‹‹እኔን ማሞገሱን እንኳን ለሌላ ጊዜ አቆየው..በነገራችን ላይ የአባትህ ጉዳይ ላይ  ይግባኝ ለመጠየቅ ሚቻል ከአሆነ አንድ ጎበዝ ጠበቃ አግኝኝቼ ሁኔታውን አስረድቼው ነበር….››

‹‹በእውነት ..ታዲያ ምን አለሽ?››
👍6721👎1👏1