አትሮኖስ
280K subscribers
111 photos
3 videos
41 files
478 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#የተወጋ_ልብ


#ክፍል_ስድስት


#ድርሰት_በትክክል_ገና


.....“ግራ ገባኝ አኮ ሸዋዬ? እስቲ የተፈጠረውን ነገር በጥሞና አስረጅኝ?” እየተሽቆጠቆጠ ጠየቃት። ሸዋዬ ቱግ! ብላ ተነሳች።

“ግራ ይግባህ!! የእናት የአባቴ አምላክ ግራ ያግባህ!! ድሮውንም ግራ
ነበርክ! አሁንም ግራ ነህ!” ብልጭ! አለበት፡፡ በቆመችበት በቃሪያ ጥፊ
ሲደረግምባት እንደ ብራቅ ጮኽችና አልጋዋ ላይ በጀርባዋ ፍንችር ብላ
ወደቀች። ከዚያም የመኝታ ክፍሉ በር እንደ ቦምብ ጮሆ የኮርኒሱን ቆሻሻ እስከሚያራግፈው ድረስ አላትሞ ዘጋባትና በቀጥታ ጌትነት ወደተኛበት ክፍል መጣ፡፡

“ኢልመ ሞክራ !” ጮኽበት፡፡ “የመኩሪያ ልጅ!!” በለበጣ አጠራር፡ ጌትነት
በስማው ጩኽት ተደናግጦ ብንን.. አለ፡፡ ጭንቅላቱ ላይ ከባድ ሸክም ያረፈበት መሰለው፡፡ የት እንዳለ የት እንደወደቀ የሚያውቀው ነገር አልነበረም።ጉርሽጥ የመሰሉ ዐይኖቹ እንደተቆጣ አንበሳ ቀልተው ካፈጠጡበት የቶሎሳ ዐይኖች ላይ ተተክለው ቀሩ።

“ቶሌ ኢቦ! ሌንጮ ኬኛ ሜ ዋን ተኤ ኦዴሲ?! ጂአ ለመ ኬሳ አመለኬ
ጶከቴ ባሉ ጀልቀብዴ? 'እሺ እባክህ የኛ አንበሳ? የተፈጠረውን ነገር አውራልን እስቲ! ገና በሁለት ወርህ ሽጋ አመልህን ታወጣው ጀመር?! የተደበቀ ቆንጆ አመልህን?” ባልገባው ቋንቋ አሽሟጠጠው፡፡ ጌትነት በድንጋጤ ተርበተበተ።

“እንዴ..ምን.አደርክ ጋሼ.ቶሎ ሳ?!ከተጋደመበት በፍጥነት ተነስቶ በአክብሮት ሊጨብጠው ተንደፋደፈ። አልቻለም፡፡ ያደረደበት ቶሎ እንዳይ
ነሳ ወደ ታች ጎትቶ ያዘው።
“ሲለኔ ሀዳር ማን ጠየቆ?! አሁን ሲለፈጠረው ታሪክ ቢቻ ቶሎ በሊና
ነጊር!” እየተንጎራደደ ትዕዛዝ ሰጠው፡፡ ጌትነት ስካሩ ሙሉ ለሙሉ አልለቀቀውም ነበር። የቶሎሳን ስሜት በሚገባ ማጤን አልቻለም። እንደዚያም ሆኖ ግን ሃይለ ቃሉ ያልተለመደ ሆነበት፡፡ ደነገጠ፡፡ መጠጥ ጠጥቶ ከነልብሱ ተኝቶ በመገኘቱ፣ ባሳየው አዲስ ያልተገባ ፀባይ ተናዶ የተቆጣው መስሎት በእፍረት ተሸማቀቀና ይቅርታ ሊጠይቀው ብድግ አለ፡፡ ሸዋዬ በቶሎሳ ጭንቅላት ውስጥ ያስቀመጠችው መርዝ መኖሩን የት አውቆት? ማታ ምን እንደሰራ ምን እንዳደረገ የሚያውቀው ነገር የለም።ጠዋት ውጤቱ በግልፅ የሚታየው ስካሩን እንጂ ከስካሩ ጋር ተያይዘው ከተፈ
ጠሩት አስደናቂ ትርኢቶች መካከል አንዷን እንኳ ማስታወስ አልቻለም፡፡
ሰክሮ መገኘቱ በራሱ ትልቅ ድፍረትና ሀጢአት ነውና ጋሼ ቶሎሳ ይቅር
እንዲለው ሊለምነው ፈልጎ እንደምንም ብሎ ከአልጋው ላይ ተነሳ።

“እባክህ ጋሼ ቶሎሳ አትቀየመኝ፡፡ የቤት ጠላ ነው ብዬ ነው ከአቅሜ በላይ
የጠጣሁት። ይቅርታ አድርግልኝ?” አንገቱን አቀረቀረ፡፡
“ኢሱ የራሱ ቺጊር ኖ! ሀቂሙን ገሚቶ ጠጣው የራሱ ጉዳይ ኖ! ቶሎሳ
ጉዳይ አዶለም! ሰካራም ! ቢራ አልጠጣውም ሀላልሺም?! አሁን ሚን
ገኘሺና ጠጣሺው?!” እነዚያ ትናንሽ ዐይኖቹን እንደ ነብር አጉረጠረጠበት። ጌትነት ትናንት እና ዛሬ ተቀላቅለውበት ምንም ነገር እንዳልተፈጠረ ሁሉ ትናንት አዲስ ክስተት አዲስ ትርዒት የተፈፀመበት ቀን እንዳልነበረ ሁሉ ተረጋግቶ ነበር የተኛው፡፡ ሆዱ የቀራጭ አቅማዳ እስከሚመስል ድረስ ጠላ ሲጋት ማምሸቱን እንጂ ስለሌላው ጣጣ አሁን ቶሎሳ ስለሚያወራው ታሪክ ምንም የሚያውቀው ነገር አልነበረም፡፡ ራቱን ምን
እንደበላ እንኳ አያስታውስም፡፡ ቶሎሳ እንደዚያ ግስላ ሆኖ ሲያንባርቅ
ግራ ተጋባ፡፡ ተደነጋገረው።
“እባክህ ጋሼ ቶሎሳ ሁለተኛ አላደርገውም፡፡ አይለመደኝም። የዛሬን ብቻ ተለመነኝ፡፡ ቤቴ ነው ብዬ ተዝናንቼ ነው የጠጣሁት” በድጋሚ ተለማመነው። ቶሎሳ ብው አለ፡፡
“ኢሄ ሶዬ ጤና ኤለም ሂንዴ?!ሲለጠላ ወሬ አልፈሊጊም!! አይገባሂም
ሂንዴ?! ሲለሆነ ነገር ቢቻ ነጊር! ሲለፈጠረው ታሪክ ሀንዲም ሳታስቀሮ
ፊሪጥ ፊሪጥ አዲርጊና ነጊር!!”
ጌትነት ስለምን እንደሚያወራ ውሉን መጨበጥ ተሳነው።ድንብርብሩ
ወጣ! ዐይኖቹን ጭፍን ክድን... ጭፍን... ክድን... ጭፍን... ክድኝ...
አደረጋቸው። የቶሎሳን ያልተለመደ ቁጣና ጩኽት፣ በንዴት የተለዋወጠ ፊት ሲመለከት ክፉኛ ተደናገጠ፡፡ ዐይኖቹንም ጆሮዎቹንም ተጠራጠረ፡፡ ጆሮውን ኮረኮረ፡ እትዬ ሸዋዬ የቶሎሳን ጩኽት ስምታ ሮጣ
የምትመጣ መሰለው፡፡ እዚያ ደርሳ...“ምነው ቶሎሳ? ምን ሆናችሁ?
ምን ነካችሁ? ጉረቤት ሁሉ እስኲሚረበሽ ድረስ የምን ጩኽት ነው? ቢጠጣ ምን አለበት ታዲያ? የቤት ጠላ ነው የጠጣው። መሸታ ቤት ሄዶ
አልጠጣ? በል አሁን ይብቃህ!”ብላ ቶሎሳን ስትገስፀው በሀሳቡ ታየው።
እትዬ ሸዋዬ መጥታ እንድትገላግለው ተመኘ፡፡

“ምን እንደምትለኝ ማወቅ አልቻልኩም እኮ ጋሼ ቶሎሳ? እትዬ ሽዋዬ
ጩኽትህን ስትሰማ ትደነግጣለች። ሁለተኛ አይለመደኝም፡፡ እባክህ
የዛሬን ብቻ ይቅርታ አድርግልኝ?” እንዳይገረፍ የሚሽቆጠቆጥ ህፃን ልጅ
መሰለ፡፡ ቶሎሳ አውቆ ሊያታልለውና ሊቀልድበት የሚያደርገው የብልጣ
ብልጥነት ሙከራ መስሎት የበለጠ ተናደደ። ጨስ...“ሀቲቀባጢር!” አለና
ዘሎ አንገቱን አነቀው፡፡ መቼም የአደነጋገጡ ነገር አይነሳ። ከመውደቅ
ተረፈ እንጂ ሰማይ በላዩ ላይ የተደፋበት ነበር የመሰለው። ተርበደበደ::
“ምንድነው ነው የምትለኝ ጋሼ ቶሎሳ?!” እሱም ሰውነቱ በንዴት ማተኮስ ጀመረ። ቀስ አለና አንገቱን ጨምድዶ የያዘውን የቶሎሳን እጅ ከአንገቲ ላይ አላቀቀ። በጉልበት ቢያያዙ ቶሎሳን ጃርት የበላው ዱባ አስመስሎ እንደሚሄድ የታወቀ ነው። በፍፁም የሚመጣጠኑ አይደሉም፡፡ ጌትነት ጠፍሮ የያዘው የአክብሮትና የፍርሃት ልጓም ብቻ ነው። በሱ እምነት
ምንም የፈፀመው ወንጀል፣ ምንም የሰራው ሀጢአት የለም፡፡ የፈፀመው
ወንጀልና የስራው ሀጢአት ቢኖር ጠላ ጠጥቶ ሰክሮ መገኘቱ ነው::
ለዚህ ጥፋቱ ደግሞ እየተርበተበተ ቶሎሳን ይቅርታ እየጠየቀው ነው::
ነገሮች ቀስ በቀስ ግልፅ እየሆኑ የመጡት ቶሎሳ እንደታረደ በሬ በሚጓጉር ድምፅ ማጓራት ሲጀምር ነበር።
“ሸዋዬን ሚንዲኖ ያደረገች?!በሚን ሚኪናቲኖ ቀየመች?!ለሚንዲኖ ማቲናገሮ?!” ጮኽና በድጋሚ አንገቱን ሊያንቀው መጣበት፡፡ ጌትነት ክው አለ።
“ም..ምን….ምን?...” ከድንጋጤው የተነሳ በፍፁም የሱ የራሱ መሆኑን በሚያጠራጥር አንደበት ተንተባተበ፡፡

“ሚንዲኖ ደረካት?! ሚናባቲኖ ሆነች?!” በድጋሚ ጮኽበት።
“እ...እኔ....እኔን ...ነኝ...እኔን ምምንን ...አደረገኝ ..አለች ” አፉ
ተሳሰረ።
“አሃሃሃ!.…ሌባ ሀይና ደረቂ መሊሶ ሊብ ዲቂቂ ሀሉ! ኢንደ ታናሽ ሆንዲሙ መልኪቼው ኢንደ ታላቅ ሆንዲሙ አከቢራል መሲሎት ነበረው።አባቱ ሁለታ ከቢዶት ኢናቱና ኢቱን ኢንዲረዳው ፈለኩት።ተሪፎት አዳላም ከባሌ ጠራሁት። ካፊሎ ኢንዲበላው ሆንዲሙን አኪል ኢምነት ጣልኩት።አንታ አላ ቢሎ ሁጭ አደረው ሆንጀል ደረገና ሚስቱን
በሳጫት ሀደረው፡፡ ኢዝጋቤር ቢዲሩን ኪፈል! ስኪሮ ቲዳሩን ቢጥቢ ኡጡን ሲላወጣው መስጊናሎ!ሆ! ኢዝጋቤር!!” እሱ የሰማዩ ጌታ ብድሩን ብ
እንዲከፍለው ወደ ሰማይ ቀና ብሎ ተመለከተ። ከዚያም ተስፋ በቆረጠ
ሁኔታ ጌትነትን ትክ ብሎ አየው፡፡ ያውም ቶሎሳ ጨርቅ ከመጋፈፍ ድንበር ወዲህ ባለ ምክንያት አስቀይሟት ይሆናል በሚል ግምት እንጂ ጉዳዩ ከዚያ የዘለለ አደገኛ ሙከራ እንደነበረ ቢያውቀው ኖሮ ትርዒቱ
ከዚህ የተለየ ገጽታ በኖረው ነበር፡፡ ቶሎሳ በጌትነት ላይ የተመሰረተበት ክስ ሌላ መሆኑን የተፈጠረው ተአምር ሊገምተው የማይችለው መሆኑን ቢያውቅ ኖሮ ጉድ ይፈላ ነበር፡፡ ደግነቱ ጌትነትን እንደዚያ ሊያስጠረጥረው በሚያስችለው ሁኔታ ውስጥ አላገኘውም፡፡ ልብሱን እንኳ ሳያወልቅና ሰክሮ እንደተጋደመ ነው ያገኘው። ቶሎሳ በፍፁም
👍4
#ያልታበሱ_እንባዎች


#ክፍል_ስድስት


#ድርሰት_በአሰፋ_በቀለ_ገየሱስ

...ወይዘሮ እልፍነሽ አጭር ወፍራም ናቸው፣ ከወገባቸው ጎንበስ ያሉ ፀጉራቸወም በአጭርና ሸበቶ፤ በባህሪያቸው ወራኛ የሚባሉ ናቸው፤ አንዷን ከአስር
በላይ የሚያባዙ፤ ለውሸት ልክ የሌላቸው:: ከዚሁ ባህሪያቸው በመነጨ የጎረቤት ሰው ሁሉ እልፍነሽ ወሬ እፈሽ ይላቸዋል፡፡

ሽዋዬ ቤት ወስጥ ገብታ ራሷ ወንበር ሳብ አድርጋ ስትቀመጥ ወይዘሮ እልፍነሽ እጆቻቸውን በወገባቸው ላይ አጣምረው ከፊቷ ቆሙ፡፡ ለወሬው በጣም
የቸኮሉ ይመስላለ::
«እንደው ምን አግኝቶሽ ይሆን ልጄ?» ሲሉ ጠየቋት::
«ቁጭ በሏ!» አለቻቸው ሸዋዬ ከንፈሯን በምላሷ እያራስች፡፡ የእጆቿን መዳፎች አጋጥማ በጉልበቶቿ መሀል አጥብቃ ይዛቸዋለች፡፡
ወይዘሮ እልፍነሽ ለወሬው ሰፍ ብለዋል። ጠበብ ካለች አፋቸው ውስጥ ከአራት በላይ የማይታዩ ጥርሶቻቸውን ገለጥ አድርገው ፈገግ እያሉ ተቀመጡና፡-
«እስቲ ንገሪኝ ልጄ!» አሏት፡፡
«ጉድ የምትሰሩኝ እኮ እናንተ ጎረቤቶቼ ናችሁ!» አለቻቸው ሽዋዬ ምላሷን በከንፈሮቿ ዳር እና ዳር ግራና ቀኝ ወጣ ገባ እያረገች ወይዘሮ እልፍነሽ ደረታቸውን በእጃቸው ደሰቅ አረጉና «ውይ በሞትኩት! ምነው? ምን አደረግን?»
«የእህቴ ህይወት ሲበላሽ እያያችሁ ዝም ትሉኛላችሁ?»
«ምነው? ምን አገኛት?»
«አርግዛ ትምህርቷን ብታቋርጥስ?»
«እንዴ!» አሉ ወይዘሮ አልፍነሽ ነገሩን እንደማቃለል ዓይነት በሚያስመስል አነጋገር፡፡ «እጮኛዋ ባለሙያ አይደል እንዴ! ችግር ቢፈጥር ኣሽቀንጥሮ ይጥልላት የለ!» ካሉ በኋላ አፋቸውን የበለጠ ወደ ሸዋዬ ጠጋ በማድረግ «አአሁን ቀደምስ
ችግሩ ተፈጥሮ ገላገላት ተብሎ ብለው ሳይጨርሰ ሽዋዬ ቀደመቻቸው::
«ምን አሉ?» አለች ዓይኗን ፍጥጥ አድርጋ እያየቻቸው። እጮኛዋ ያሏት ነገር ከተቀመጠችበት አንጥሮ ሊያነሳት ሲል ደሞ የወርጃ ነገር ጨመሩባትና
በአለችበት ኩርምትምት አለች።
«ኧረ ተይኝ እቴ!» ብለው ወይዘሮ እልፍነሽ እንደ መግደርደር ዓይነት ወደ ውጭጉዳይ አየት ካደረጉ በኋላ እንደገና ወደ ሽዋዬ መለስ በማለት «በአንቺ እህት ስንት
ልጃገረዶች እየቀኑባት ደሞ እንዲህ ያለ ሥጋት ይደረብሽ እንዴ? ሆሆይ...»
ሸዋዬ በባሰ ድንጋጤ ሰውነቷ ሽምቅቅ ብሎ መንፈሷ ድክም፣ ልቧም ስንፍ አለና በተራዘመ የቃል አወጣጥ «አ ሶ ር ዳ ለ ች ነው የሚሉኝ ስትል ጠየቀቻቸው::
«ገላግሏት!»
ሸዋዬ አሁንም ድክም ባለ መንፈስ «አ መ ስ ግ ና ለ ሀ:!» አለቻቸውና
ከተቀመጠችበት በቀስታ ብድግ አለች። ወይዘሮ እልፍነሽ እወነትም አፍሰው አቃሟት፡፡
«ጠሐይ ይብረድልሽ እንጂ!» አሏት ወይዘሮ እልፍነሽ እኚያኑ
ጥርሶቻቸውን ገለጥ እያደረጉ፡፡
«ቤቴ ሄጄ ማረፍ እፈልጋለሁ። ደህና ዋሉ!» ብላቸው ወጣች፡፡

ወይዘሮ እልፍነሽ አሁንም እጃቸውን በወገባቸው ላይ አጣምረው እስር እስሯ እየሄዱ በሹክሹክታ ዓይነት «እይው ልጄ፧ እኔ እኮ ቀድሜ ጠርጥሪያለሁ፣
ብታይ አንቺ እግርሽ ወጣ ያለ ጊዜ እሱ ዘሎ ጥልቅ! ትናት ዘሎ ጥልቅ! ዛሬም ዘሎ ጥልቅ ሲል እያየሁ ሆዴ በጣም ይፈራ ነበር፡፡» አሏት፡፡
ከቤት ይዟት ወጥቶ ያውቃል?»
«ኧረ በገዛ ቤትሽ ውስጥ እቴ! ደሞ የምን ወደ ውጪ ሆይ…?» አሉና
«ማናት ይቺ እቴ ስሟን አምጪልኝ፡ ይቺ የወይዘሮ ዘነቡ ሠራተኛ?»
«ፋንታዬ?»
“እ! እሷ ቲራቲር ስታይ አይደል እንዴ የምትውለው፤ እሷን ብትጠይቂያት እኮ ጉድ ትነግርሻለች፡፡»
ሽዋዬ ነገሩ ሁሉ ገባት። ወሬው ሁሉ ከፋንትዬ እንደሚመነጭ ተረዳች፡፡
ይሁንና ብትጠይቃት ደፍራ እውነቱን ላትነግራት እንደምትችል ገመተች። ለነገሩ ወሬ በቅቷታል፡፡ ከእንግዲህ ታፈሡ ብቻ ቀረቻት፣ በእሷ ግምት አስቻለውና
ሔዋንን የምታገናኝ ታፈሡ እንደምትሆን በማመን፡፡

ሸዋዬ በዕለቱ እህል ውሃ አላሰኛትም ሔዋን ምሳ አዘጋጅታ እየጠበቀቻት ቢሆንም ቤቷ እንደ ደረሰች የሔዋንን ዓይኖች ቀና ብላ እንኳ ሳታይ በቀጥታ አልጋዋ ላይ ወጥታ ጥቅልል ብላ ተኛች፡፡ በዚያው መሽ፡፡ ቀኑም በለሊት ተተካ፡፡ ያ ሁሉ ሆና ሽዋዬ በዓይኗ ላይ እንቅልፍ አልዞረም፡፡ ይልቁንም እንኳን ራሷ ለአልጋዋም አልመቻት ብላ በየደቂቃው በመገላበጥ ስታንቋቋት አደረች፡፡

በማግስቱ ጠዋት ሔዋን ወደ ትምህርት ቤት ስትሄድ ልክ እግሯ ከቤት እንደ ወጣ ሸዋዬ ልታደርግ ስታስብ ከአደረችው እቅድ ውስጥ የመጀመሪያውን መፈፀም ጀመረች:: ሔዋንና አስቻለው የተፃፃፉት የፍቅር ደብዳቤ ካለ ብላ ደብተሮቿን መፈተሽ ያዘች ፤ ገፅ በገፅ እያገላበጠች፣ የደብተሮቹን መሸፈኛ እየገለጠችና ዘቅዝቃ እያራገፈች በረበረቻቸው። የሔዋን ቅያሪ ልብሶች
አልቀሯትም፡፡ ኪሶቿን ሁሉ ዳበሰቻቸው፡፡ ግን ምንም ነገር ሳታገኝ ቀረች፡፡
ሲደክማት አልጋዋ ላይ ቁጭ አለች:: ግን ደግሞ አንድ ነገር ትዝ አላት። የድካሟ ምክንያት ርሀብ ጭምር ነው:: ከትናንት ምሣ ጀምሮ እስከ ዛሬ ቁርስ ሰዓት ድረስ ምንም አልቀመሰችምና ወደ ምግብ አዘነበለች፡፡ በእርግጥም ከነውዝፉ አጠቃለለችው:: በንዴት ውስጥ ስለነበረች አጎራረሷ እንኳ ጤናማ አልነበረም ቶሎ
ቶሎ ጎሰጎሰችው።

ከታፈሡ ጋር የምትገናኝበት ስዓት በመከራ ደረሰ። ጠዋት ወደ ታፈሡ ቤት መሄድ አልቃጣችም፤ በአንድ በኩል ለጠብ ነው የምትፈልጋት! በሌላ በኩል ደግሞ አስቻለውም ቢሆን ከታፈሡ ቤት አይጠፋምና፡፡ በሁለተኛው ፈረቃ
የዕረፍት ሰዓት ነው ከታፈሡ ጋር የተገናኘችው፡፡ በዲላ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ መሀል ላይ በምትገኘው ባንዲራ ሥር ሆና
ጠራቻትና አብረው እንደተቀመጡ ሸዋዬ ዓይኗን እፍጣ፣ ጥርሷን አግጣ፡-

«ስሚ አንቺ!» አለቻት፡፡
«ወይ» ታፈሡ ድንግጥ በማለት፡፡
«እህቴን ከአበ-ልጅሽ ጋር አቃጥረሽ አበላሽሻት አይደል?? »
«ኦ» ታፈሡ ሁለመናዋን ነዘር እያደረጋት።
« አላደረኩም በያ?»
«ጓደኛዬ ምን እያልሽ ነው?»
«ኧረ ጓደኛሽን ወዲያ ፈልጊ!»
«ከአንቺ የበለጠ ምን ጓደኛ እለኝ?» አለቻት ታፈሡ ነገሩ እየገባት ሂዶ ፈገግ እያለች።

«ጥሩ አቃጣሪ ኖረሻል፤ ጉድሽ ሁሉ ወጣ?»
«አቀዛሽው ሽዋዬ»
« አቃጣሪ ማለቱ? እንዲያውም ሲያንስሽ ነው»
«ጨምሪልኛ ኪም ኪም ኪም ኪም!
« አሁን ሳቂ! የምታለቅሽበት ጊዜ ይመጣል::»
«እጠብቃለኋ ኪም ኪም ኪም ኪም» ታፈው እሁንም፡፡
«እንዲህ ስትንከተከች ትንሽም አታፍሪ?» ሽዋዬ ውስጧ ብግን እያለ፡፡
«ምንም አላፍር ሽዋዬ! ምንም በማላውቀው ነገር ይህን ያህል ካልሽኝ ምናልባት ሁለቱ ተዋድደው ከአገኘኋቸው እንዲያውም እንዲያውም አጋባቸዋለሁ::»
«ኣ» ሸዋዬ ቆሽቷ እያረረ፡፡
«በእርግጥ ሁለቱ ተዋደው ከሆነ ወደ ኋላ አልልም! ታይኝ የለ!» ብላት ታፈሡ ከሸዋዬ ፊት ዘወር አለች።

ሸዋዬ ግራ ግብት እንዳላት ነበር ከዚያ በኋላ ያለውን ጊዜ ያሳለፈችው፡፡
የታፈሠ ሁኔታ ስለ ሔዋንና አስቻለው ፍቅር ብዙም ፍንጭ አልሰጣትም።
በእርግጥ ስለዚሁ ጉዳይ ባለፈው ለሊት በምታስላስልበት ጊዜ በተለይ ከወይዘሮ እልፍነሽ የሰማችው ወሬ ለጊዘው ቢያናድዳትም በእውነትነቱ ግን ተጠራጥረዋለች፡፡
👍3