አትሮኖስ
286K subscribers
123 photos
3 videos
41 files
587 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ቋጠሮ_ሲፈታ


#ክፍል_ሀያ_አንድ


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ

///

ገመዶ እኩለ ለሊት ላይ ስልኩ ጮኸ….

"ምንድን ነው ነገሩ" በማለት እየተነጫነጨ በተኛበት እጁን ዘረጋና ስልኩን ከኮመዲኖ ላይ አንስቶ ጆሮው ላይ ለጠፈና ‹‹ሄሎ››አለ፡፡

‹‹ኮማንደር መስማት አለብህ ብዬ ነው…ድንገተኛ ነገር ተከስቷል."ምክትሉ ነበር፡፡ ከመኝታው ተነሳና አልጋው ጠርዝ ላይ ተቀመጠ፡፡

"…ምንድነው የተፈጠረው?"

"ከእርባታ. ቦታው …ማለቴ የቤተሰቦችህ እርባታ ቦታ፣ከዛ ነው የተደወለልን"አለው…

ከአልጋው ወርዶ ጂንስ ሱሪውን መልበስ ጀምሮ ነበር፡፡ጭንቅላቱ የፍርሀት ቅዝቃዜ ሲፈስ ታወቀው፡፡

"ምን አይነት ድንገተኛ አደጋ ነው?"
‹‹ገና አልተረጋገጠም..ኃይል ወደእዛው ልከናል፡፡›› ያልተቆለፈ ሸሚዙን ከቆለፈ በኋላ ቆሞ ጫማውን አደረገ፡፡

‹‹በቃ ቶሎ አጣርተህ ደውልልኝ…ወደእዛው እሄዳለው፣ይሄው እየወጣሁ ነው… ››ስልኩን ዘጋና ኮቱንና ኮፍያውን አድርጎ ወደ ኮሪደሩ ሮጠ።
/////

አለም በከባድ እንቅልፍ ውስጥ ነበረች፣ ለዚህም ነው የበሯን መንኳኳት በህልሟ መስሎ የተሰማት…።ህልም ውስጥ ነበረች….በመጨረሻ ተከታታይ የሆነው የጥሪ ድምፅ ከእንቅልፏ ቀስቅሷት።

"ተነሺ እና በሩን ክፈቺ."በቁጣ እየጮኸባት ነው፣ ቁጭ አለችና አልጋው ዳር ያለውን መብራት አበራችው… መብራቱ ሲበራ …. ብርሃኑ ዓይኗን አጭበረበራት።

"ገመዶ ነኝ… ክፈቺ?" ጮኸ ። ዝም አለችው፡፡

"በአስር ሰከንድ ውስጥ ካልተነሳህሽ በሩን ሰብረዋለው››

የግድግዳውን ሰዓት ተመለከተች። ከምሽቱ ስምንት ሰዓት ገደማ ነበር።

‹‹ኩማንደሩ ወይ ሰክሯል ወይም አብዷል።››ስትል አሰበች፡፡ ያም ሆነ ይህ አሁን ባለበት ሁኔታ በሯን ልትከፍትለት አልፈለገችም።

"ምን ፈለክ?"

ከእሱ መልስ ስትጠብቅ በራፉ ላይ ፈንጅ የተጣለበት ይመስል ጎጎጎጎ አለና ተከፈተ….ተንደረደረና መኝታ ቤቷ ገባ፡፡በድንጋጤ እየተንቀጠቀጠች አልጋዋ ላይ ቆመች "ምን እየሰራህ ነው?"ብላ ጮኸችበት በቆመችበት አልጋ ልብሱን እየሰበሰበች እርቃኗን ለመሸፈን እየጣረች ነው››

"አንቺን ለማግኘት ነው የመጣሁ ‹‹
ከአልጋው ላይ ጎተተና ወለሉ ላይ አቆማት፣የተጠቀለለችበትን አልጋ ልብስ ከላዬ ላይ ገፎ ወረወረው፣እርቃኗን በፓንት ብቻ ፊት ለፊቱ ቆመች፣ምን ሊያደርጋት እንደሆነ መገመት ሁሉ አልቻለችም፡፡

"ኩማንደር በሬን ገንጥለህ መኝታ ቤቴ ለመግባትህ በቂ ምክንያት እንዳለህ ተስፋ አደርጋለሁ።"

"ማብራሪያ አለኝ።" አለና መሳቢያውን ከፈተ እና ውስጡ ያሉትን ልብሶች ማተረማመስ ጀመረ።

"ንገረኝ ምን እየፈለክ ነው?."አለችና እርቃኗን ወደእሱ ሄዳ ሚያተራምሰውን  የቁምሳጥን በራፍ በዳሌዋ ገፋችና ዘጋችበት ፡፡

"ምን ፈልገህ ነው?"ዳግመኛ ጠየቀችው፡፡
"ልብስ። እንደዚህ እርቃንሽን  መውጣት ካልመረጥሽ በስተቀር  ምትለብሺው ልብስ ያስፈልግሻል››

‹‹ወደየትም አልሄድም››

" ጂንስሽ የት ነው ያለው?›› በ ወፍራም ድምፁ ጠየቀ ። "የትም አልሄድም። ስንት ሰዓት እንደሆነ ታውቃለህ?››

ድንገት ቀና ሲል ከአልጋው አጠገብ ባለው ግድግዳ ልብሷ ተሰቅሎ አየው፡፡ ጂንሱን ከተሰቀለበት ላይ አወረደና ወረወረላት፣ መያዝ ስላልቻለች ወደ ወለሉ ወደቀ።
ከጫማዋቾ ውስጥ አንዱን መረጠና ወደእግሯቾ አቀረበላት፡፡ ዝም ብላ ፈዛ ታየው ጀመር፡፡ "እሺ.. እንዳለብስሽ ትፈልጊያለሽ?"

እሱን ለማስቆጣት ምን እንዳደረገች መገመት አልቻለችም። እርቃኗን እሱ ፊት ቆማ መከራከሩ ስለደከማት ጆንሱን አነሳችና አጠለቀች ፡፡ከላይ ሹራብ ለበሰች….ከኮመዲኖ መሳቢያ ውስጥ አንድ ካልሲ አወጣችና አራግፋ አጠለቀችና ጫማዋን አደረገች፡፡ በመጨረሻም ዞር ብላ አየችው።

"እሺ ይሄው ልብስ ለብሻለሁ …አሁን ምን እየተካሄደ እንደሆነ ንገረኝ ?"

"እየሄድን  እነግርሻለው  ››አለና  እጆቿን  በመያዝ  እየጎተተ  ይዞት  ወጣ  ፡፡በንዴት እየተንቀጠቀጠች ነበር።

‹‹እንዲህ እንድታደርገኝ ማን ነው የፈቀደልህ?››

"አንገትሽን መስበር አለብኝ…..አላደረገውም››በማለት ወደእሷ ተጠጋና ከንፈሯን ሳማት።ያለተቃውሞ ተሳመችለት፡፡ምላሱን ወደ አፏ ውስጥ አስገባ። በዚህ ጊዜ በቁጣ ስሜት መነጨቀችውና እራሷን አላቀቀች፡፡

ኮትዋን ከሳሎን በራፍ አካባቢ ካለው ማንጠልጠያ አነሳችና ያዘች፡፡ ከቤት ይዞት ወጣ " በሩስ?"ብላ ጠየቀችው ።
"የሚጠግን ሰው እልካለሁ።"

"በዚህ ለሊት?"

"በፈጣሪ … በሩን እርሺው..በአካባቢው ቤትሽን በንቃት የሚጠብቁ ፖሊሶች አሉ" ብሎ ጮኸ።

‹‹የሚጠብቁ ነው ሚሰልሉኝ?››

እጇን ጨምድዶ እንደያዛት ስትጠብቀው ወደነበረ ታክሲ ውስጥ ይዞት ገባ፡፡

"በፈጣሪ ገመዶ…ምን እየተፈጠረ ነው……?ነው ወይስ እያሰርከኝ ነው?››

‹‹እያሰርከኝ ..አንቺን……?ምነው ወንጀል ሰርተሸል እንዴ?›› ፡፡

‹‹እና ምንድነው ንገረኛ….?ወደየት እንደምሄድና ለምን እንደምሄድ የማወቅ መብት አለኝ›› ።

"የእርባታ ቦታው እየተቃጠለ ነው."

‹‹የእርባታ ቦታው.?.የነጁኒዬር?››

‹‹አዎ››

‹‹ወይ..ፈረሶችህ ተረፉ?››

ፈረሶቹን ምን ያህል ይወዳቸውና በምን ያህል መጠን ይንከባከባቸው እንደነበረ ስለምታውቅ ነው ቀድማ ስለፈረሶቹ የጠየቀችው፡፡

‹‹አላውቅም…የወደመውንና የተረፈውን ስንደርስ ነው የምናውቀው፡፡››
////
ሲደርሱ እሳቱ ከፈረሶቹ ጋጣ አካባቢ እየተንቀለቀለ ነው…በአንድ ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ሚገኘው የእንጨት ፋብሪካው ከአደጋ ውጭ ነው፡፡ቢሆንም በንፋስ ታግዞ ወይም በሆነ ምክንያት እሳቱ እዛ ቢደርስ ከፍተኛ ውድመት እንደሚያስከትል የታወቀ ነው፡፡

እንደደረሱ መኪናዋ ስትቆም ኩማንደሩ ከመኪናው ወረደና ወደእሳቱ አቅጣጫ ተንቀሳቀሰ…አለም ከኋላው ተከተለችው፡፡ከአንዱ የፈረስ ጋጣ ጭስ ሲትጎለጎል ይታያል…አለም ሆዷ ተገለባበጠባት። የእሳት አደጋ መከላከያ ሰራተኞች፣ የደንብ ልብሳቸውን ለብሰው እሳቱን ለመቆጣጠር እየሞከሩ ነበር።ብዛት ያላቸው የእርባታው ሰራተኞችና የአካባቢው ኑዋሪዎች ቅጠለም አፈርም እየተጠቀሙ እሳቱ እንዳይዛመት ለመቆጣጠር እየተረባረቡ ነው፡፡
አንድ ሰው ወደኩማንደሩ ቀርቦ"በጣም ብዙ ጉዳት ከማድረሱ በፊት ደርሰውበታል" ሲል ነገረው፡፡

‹‹ሰውስ አልተጎዳም?››

‹‹አንድ የተጎዳ ሰው አለ…››የሚል ድምፅ ሰማ፡፡

"ማንው የተጎድቷል?"

‹‹በጣም አሰቃቂ ትዕይንት ነበር።ከፈረስ ተንከባካቢዎች አንዱ ነው… በቂ አየር ወደ ሳምባዋ መሳብ አልቻለችም። ፈረሶችን ለማዳን ሲሯሯት አንድ እግሩም ተሰብሯል››

በዛ ቅፅበት አንድ ፈረስ እየጮኸ ነበር፣ በግልጽ ህመም ላይ እንዳለ ያስታውቃል። አለም እስካሁን ሰምታ የማያውቀው እጅግ አሳቃቂ ድምፅ ነበር የሰማችው። ገመዶ በፍጥነት ወደእዛው አመራ…ከኃላው ተከተለችው….የአቶ ፍሰሀ ቤተሰቦች በጠቅላላ በለሊት ቢጃማቸው በአካባቢው ነበሩ ፡፡መኖሪያ ቤታቸው ከእርባታው ድርጅት ብዙም ሰላማይርቅ እንደሰሙ በእግራቸው ነው ሮጠው ወዲያው ነው የደረሱት፡፡ ሳራ እያለቀሰች ነበር። ፍሰሀ

እራሱን ተቆጣጥሮ በፅናት ቆሞ ይታያል…ጁኒዬር እናቱን አቅፎ ያፅናናል፡፡ ገመዶ ወደ ጎን ገፋቸው እና እሳቱ ጠፍቶ ጭሱ ብቻ ከሚታይበት ጋጣ ውስጥ ገባ ፡፡
49👍4🔥1