ስንክሳር
7.32K subscribers
825 photos
4 videos
37 files
237 links
በስንክሳር channal ስንክሳሩ ተገልጦ ቅዱሳን ይዘከራሉ፣ ወቅቱን የጠበቁ መረጃዎችን ያገኛሉ፡፡ ይከታተሉን!
Download Telegram
#ቅዱስ_አውዶኪስ_ቀሲስ
ይህ ቅዱስ ሰው ለቅዱስ መስቀሉ ከነበረው ፍቅር
የተነሳ በብዙ ድካም ወደ #ኢየሩሳሌም በእግሩ ተጉዞ
ነበር:: ከብዙ መንገደኞች ጋር በጐዳና ላይ ሳሉ ታዲያ
አንድ አይሁዳዊ (ሰማርያዊ) ተቀላቀላቸው:: በወሬ
በወሬ የት እንደሚሔዱ ሲጠይቃቸው "መካነ መስቀሉን
ለመሳለም ወደ #ጐልጐታ ነን" አሉት::
እሱ ግን ከት ብሎ ስቆ "እንዴት እንጨት
ትሳለማላችሁ" በሚል አፌዘባቸው:: የፀሐዩ ሐሩር እጅግ
ጠንቶ ነበርና ቅዱስ አውዶኪስ ኃይለ መስቀሉን ሊያሳይ
ወደደ:: በመንገድም መርዝነት ያለው ውሃ ነበርና ቅዱሱ
ቀርቦ ጸልዮ በመስቀሉ ባረከውና ፈጥኖ ወደ ጣፋጭነት
ተቀየረ::
ምዕመናኑ ደስ ብሏቸው ሲጠጡ ያ አይሁዳዊ
'እጠጣለሁ' ብሎ ቢቀርብ ወደ ነበረው ተመለሰበት::
'በኮዳ የያዝኩትን እማልጠጣ' ብሎ ቢከፍተው ደግሞ
ተልቶ አገኘው:: እጅግ ደንግጦ አለቀሰ:: በጣም
ጠማው: ግን ምኑን ይጠጣ!
አማራጭ ሲያጣ ወደ ቅዱስ አውዶኪስ ሒዶ እግሩ
ላይ ወድቆ አለቀሰ:: በመስቀሉ ቢማጸን መራራው
ጣፈጠለት:: በዚህ ምክንያትም ወደ ክርስትና
ተመልሷል:: ቅዱሱ በመልካም ሽምግልና ሲያርፍ ውሃው
የተቀየረበት ቦታ ላይ ቤተ መቅደስ ታንጾ በዚህ ቀን
ተቀድሷል::