✝መስከረም ፮ (6)
✞✞✞ ♥እንኩዋን ለታላቁ ጻድቅ " #አቡነ_ሳሙኤል_ዘዋልድባ" ዓመታዊ የፍልሠት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ♥✞✞✞
" #አባ_ሳሙኤል_ዘዋሊ "
ሃገራችን እልፍ አእላፍ ቅዱሳንን አፍርታለች:: እንኩዋን
በተባረከው በቀደመው ዘመን ይቅርና ዛሬም ከሃገር
ተርፈው ለዓለም የሚጸልዩ : በየበርሃውና በየፈርኩታው
የወደቁ ብዙ አባቶችና እናቶች አሉን::
በኢትዮዽያ ውስጥ ከተነሱ ቅዱሳን "ሳሙኤሎች" ልዩ
ቦታ አላቸው:: በ20 ዓመታት ልዩነት ብቻ 6ቱ ሳሙኤሎች
ተነስተው ከቅድስና ሕይወት እስከ ስብከተ ወንጌል :
ከገዳማዊ ሕይወት እስከ ምናኔ በጐውን ጐዳና አሳይተዋል::
☞እነዚህም:-
1.ሳሙኤል ዘዋልድባ
2.ሳሙኤል ዘጣሬጣ
3.ሳሙኤል ዘቆየጻ
4.ሳሙኤል ዘግሺ
5.ሳሙኤል ዘሃሌ ሉያ እና
6.ሳሙኤል ዘደብረ ወገግ ናቸው::
በተመሳሳይም በግብጽ የደብረ ቀልሞኑን ኮከብ
ጨምሮ (መልአኩን ቀውስጦስን ከጌታ ያማለዱት) ብዙ
ሳሙኤሎች ተነስተዋል:: የድሮ እናቶቻችን በእውነት ስም
መሰየሙን ይችሉበታል:: ✝"ሳሙኤል" ማለት "ሰምዓኒ
እግዚአብሔር ስዕለትየ - እግዚአብሔር ልመናየን ሰማኝ"
ማለት ነውና::✝
ወደ ቀደመ ነገራችን እንመለስና ታላቁ ኢትዮዽያዊ
ጻድቅ አቡነ ሳሙኤል ዘዋሊ የተወለዱት በ13ኛው መቶ
ክ/ዘመን (በ1295) በምድረ አክሱም ነው:: ወላጆቻቸውም እስጢፋኖስና ዓመተ ማርያም ይባላሉ::
✝የዘር ሐረጋቸው ከካህናት ወገን ነውና ጻድቁ ገና
በልጅነት ምሥጢራተ ሃይማኖትን ጠጥተዋል:: ለዚህም
ይመስላል ገና ሕጻን ሳሉ ምናኔን የተመኙት:: ከልጅነታቸው ጀምረው ወላጆቻቸውን ያገለገሉት
ሳሙኤል ትምሕርታቸውን ሲፈጽሙ የተጉዋዙት ወደ
ደብረ በንኮል ነበር::
በጊዜውም የጻድቁ ወላጆች ዐርፈው እንደ ነበር
ይነገራል:: ደብረ በንኮል ማለት የታላቁ ኮከብና አበ
መነኮሳት አቡነ መድኃኒነ እግዚእ ገዳም ነው:: መድኃኒነ እግዚእ ለሃገር ብርሃን የሆኑ ቅዱሳንን ያፈሩ ዘንድ ሲተጉ እግዚአብሔር 7ቱን ከዋክብት ሰጣቸው::
ክእነዚህ መካከልም ቀዳሚው አቡነ ሳሙኤል ናቸው::
ቀሪዎቹ ደግሞ እነ አቡነ ያሳይ ዘመንዳባ : ሳሙኤል
ዘጣሬጣ : ሳሙኤል ዘቆየጻና ያፍቅረነ እግዚእ ዘጉጉቤን
የመሰሉ ናቸው:: አቡነ ሳሙኤል ከ6ቱ ባልንጀሮቻቸው ጋር ሆነው በደብረ በንኮል ተጋድሎን አሐዱ አሉ:: እንጨት ይሰብራሉ:: ውሃ
ይቀዳሉ:: እህል ይፈጫሉ:: በፍጹም ልባቸውም
ይታዘዛሉ:: ጐን ለጐን ደግሞ ከቅዱሱ አበ ምኔት
መድኃኒነ እግዚእ ጽንዓትን : ትሕትናን : ትሕርምትን
ይማሩ : ሥርዓተ ገዳምንም ያጠኑ ነበር::
✝ከአገልግሎታቸው ማማር የተነሳ ሁሉን ደስ ማሰኘት
ቻሉ:: በዚህ ጊዜም ጻድቁ አበ ምኔት አቡነ ሳሙኤል
ዘዋሊንና 6ቱን አበው ጠርተው ለምንኩስና አቀረቧቸው::
"ይገባቹሃል!" ሲሉም ከአሞክሮ ወደ ምንኩስና አሸጋገሯቸው::
በዚያች ቀን 7ቱ ሲመነኩሱ ከሰማይ ብርሃን ወርዶ
በመታየቱ ቅዱሳኑ "ከዋክብት ብሩሃን" ተባሉ:: ለተወሰነ
ጊዜም በዚያው በገዳሙ አገለገሉ:: የአቡነ ሳሙኤል
ዘመዶች ግን እየመጡ ጻድቁን ስላስቸገሩ 7ቱም ቅዱሳን
ተመካክረው : ከአባታቸው መድኃኒነ እግዚእ ተባርከው
ከደብረ በንኮል ወጡ::
ሁሉም መንፈስ ቅዱስ ወደ መራቸው ሲሔዱ 3ቱ
(ማለትም ሳሙኤል ዘዋሊ : ያሳይ ዘመንዳባና ያፍቅረነ
እግዚእ ዘጉጉቤ) ወደ ጣና ሔዱ:: በዚያም ለጥቂት ጊዜ
አብረው ከቆዩ በሁዋላ ለአገልግሎት ተለያዩ:: አቡነ
ያሳይ "መንዳባን" : አቡነ ያፍቅረነ እግዚእ "ጉጉቤን"
ይዘው እዛው ጣና አካባቢ ሲቀሩ አባ ሳሙኤል ወደ ዋልድባ ሔዱ::
✞✞✞ ♥እንኩዋን ለታላቁ ጻድቅ " #አቡነ_ሳሙኤል_ዘዋልድባ" ዓመታዊ የፍልሠት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ♥✞✞✞
" #አባ_ሳሙኤል_ዘዋሊ "
ሃገራችን እልፍ አእላፍ ቅዱሳንን አፍርታለች:: እንኩዋን
በተባረከው በቀደመው ዘመን ይቅርና ዛሬም ከሃገር
ተርፈው ለዓለም የሚጸልዩ : በየበርሃውና በየፈርኩታው
የወደቁ ብዙ አባቶችና እናቶች አሉን::
በኢትዮዽያ ውስጥ ከተነሱ ቅዱሳን "ሳሙኤሎች" ልዩ
ቦታ አላቸው:: በ20 ዓመታት ልዩነት ብቻ 6ቱ ሳሙኤሎች
ተነስተው ከቅድስና ሕይወት እስከ ስብከተ ወንጌል :
ከገዳማዊ ሕይወት እስከ ምናኔ በጐውን ጐዳና አሳይተዋል::
☞እነዚህም:-
1.ሳሙኤል ዘዋልድባ
2.ሳሙኤል ዘጣሬጣ
3.ሳሙኤል ዘቆየጻ
4.ሳሙኤል ዘግሺ
5.ሳሙኤል ዘሃሌ ሉያ እና
6.ሳሙኤል ዘደብረ ወገግ ናቸው::
በተመሳሳይም በግብጽ የደብረ ቀልሞኑን ኮከብ
ጨምሮ (መልአኩን ቀውስጦስን ከጌታ ያማለዱት) ብዙ
ሳሙኤሎች ተነስተዋል:: የድሮ እናቶቻችን በእውነት ስም
መሰየሙን ይችሉበታል:: ✝"ሳሙኤል" ማለት "ሰምዓኒ
እግዚአብሔር ስዕለትየ - እግዚአብሔር ልመናየን ሰማኝ"
ማለት ነውና::✝
ወደ ቀደመ ነገራችን እንመለስና ታላቁ ኢትዮዽያዊ
ጻድቅ አቡነ ሳሙኤል ዘዋሊ የተወለዱት በ13ኛው መቶ
ክ/ዘመን (በ1295) በምድረ አክሱም ነው:: ወላጆቻቸውም እስጢፋኖስና ዓመተ ማርያም ይባላሉ::
✝የዘር ሐረጋቸው ከካህናት ወገን ነውና ጻድቁ ገና
በልጅነት ምሥጢራተ ሃይማኖትን ጠጥተዋል:: ለዚህም
ይመስላል ገና ሕጻን ሳሉ ምናኔን የተመኙት:: ከልጅነታቸው ጀምረው ወላጆቻቸውን ያገለገሉት
ሳሙኤል ትምሕርታቸውን ሲፈጽሙ የተጉዋዙት ወደ
ደብረ በንኮል ነበር::
በጊዜውም የጻድቁ ወላጆች ዐርፈው እንደ ነበር
ይነገራል:: ደብረ በንኮል ማለት የታላቁ ኮከብና አበ
መነኮሳት አቡነ መድኃኒነ እግዚእ ገዳም ነው:: መድኃኒነ እግዚእ ለሃገር ብርሃን የሆኑ ቅዱሳንን ያፈሩ ዘንድ ሲተጉ እግዚአብሔር 7ቱን ከዋክብት ሰጣቸው::
ክእነዚህ መካከልም ቀዳሚው አቡነ ሳሙኤል ናቸው::
ቀሪዎቹ ደግሞ እነ አቡነ ያሳይ ዘመንዳባ : ሳሙኤል
ዘጣሬጣ : ሳሙኤል ዘቆየጻና ያፍቅረነ እግዚእ ዘጉጉቤን
የመሰሉ ናቸው:: አቡነ ሳሙኤል ከ6ቱ ባልንጀሮቻቸው ጋር ሆነው በደብረ በንኮል ተጋድሎን አሐዱ አሉ:: እንጨት ይሰብራሉ:: ውሃ
ይቀዳሉ:: እህል ይፈጫሉ:: በፍጹም ልባቸውም
ይታዘዛሉ:: ጐን ለጐን ደግሞ ከቅዱሱ አበ ምኔት
መድኃኒነ እግዚእ ጽንዓትን : ትሕትናን : ትሕርምትን
ይማሩ : ሥርዓተ ገዳምንም ያጠኑ ነበር::
✝ከአገልግሎታቸው ማማር የተነሳ ሁሉን ደስ ማሰኘት
ቻሉ:: በዚህ ጊዜም ጻድቁ አበ ምኔት አቡነ ሳሙኤል
ዘዋሊንና 6ቱን አበው ጠርተው ለምንኩስና አቀረቧቸው::
"ይገባቹሃል!" ሲሉም ከአሞክሮ ወደ ምንኩስና አሸጋገሯቸው::
በዚያች ቀን 7ቱ ሲመነኩሱ ከሰማይ ብርሃን ወርዶ
በመታየቱ ቅዱሳኑ "ከዋክብት ብሩሃን" ተባሉ:: ለተወሰነ
ጊዜም በዚያው በገዳሙ አገለገሉ:: የአቡነ ሳሙኤል
ዘመዶች ግን እየመጡ ጻድቁን ስላስቸገሩ 7ቱም ቅዱሳን
ተመካክረው : ከአባታቸው መድኃኒነ እግዚእ ተባርከው
ከደብረ በንኮል ወጡ::
ሁሉም መንፈስ ቅዱስ ወደ መራቸው ሲሔዱ 3ቱ
(ማለትም ሳሙኤል ዘዋሊ : ያሳይ ዘመንዳባና ያፍቅረነ
እግዚእ ዘጉጉቤ) ወደ ጣና ሔዱ:: በዚያም ለጥቂት ጊዜ
አብረው ከቆዩ በሁዋላ ለአገልግሎት ተለያዩ:: አቡነ
ያሳይ "መንዳባን" : አቡነ ያፍቅረነ እግዚእ "ጉጉቤን"
ይዘው እዛው ጣና አካባቢ ሲቀሩ አባ ሳሙኤል ወደ ዋልድባ ሔዱ::