ስንክሳር
7.32K subscribers
825 photos
4 videos
37 files
237 links
በስንክሳር channal ስንክሳሩ ተገልጦ ቅዱሳን ይዘከራሉ፣ ወቅቱን የጠበቁ መረጃዎችን ያገኛሉ፡፡ ይከታተሉን!
Download Telegram
+ #አባ_ማቴዎስ_ገዳማዊ+
እኒህ ቅዱስ ሰው በ4ኛው መቶ ክ/ዘ #ፋርስ አካባቢ
የነበሩ ጻድቅ ናቸው:: በወቅቱ ምንኩስና በአካባቢው
ባለመስፋፋቱ ወደ ዱር እየወጡ የሚኖሩ አበው ነበሩና
#አባ_ማቴዎስ አንዱ ናቸው:: እርሳቸው በበርሃ
ልብሳቸው አልቆ አካላቸው የሚሸፈነው በጸጉራቸው
ነበር::
የአቶር ንጉሥ የሰናክሬም ልጅ #መርምሕናምን (እጅግ
ታላቅ ሰማዕት ነው) ያሳመኑትና ያጠመቁት እርሳቸው
ናቸው:: እሕቱን #ሣራንም ከለምጿ አንጽተው ወደ
#ክርስትና መልሰዋል:: በዚህ ምክንያትም የፋርስ
አውራጃ የሆነችው #አቶር በሙሉ የክርስቲያኖች ቤት
ሆናለች:: አባ ማቴዎስ ከዘመናት ተጋድሎ በሁዋላ
በዚህች ቀን ዐርፈዋል::