ስንክሳር
7.32K subscribers
825 photos
4 videos
37 files
237 links
በስንክሳር channal ስንክሳሩ ተገልጦ ቅዱሳን ይዘከራሉ፣ ወቅቱን የጠበቁ መረጃዎችን ያገኛሉ፡፡ ይከታተሉን!
Download Telegram
#ቅዱስ_ሚካኤል_ሊቀ✞መላእክት
ቅዱስ ሚካኤል በጥንተ ተፈጥሮ #በኢዮር : #ኃይላት
በተባሉት ነገደ መላእክት ተሹሞ ነበር:: ሳጥናኤል በካደ ጊዜ
እግዚአብሔር ባወቀ: አንድም በትሕትናውና ደግነቱ በ99ኙ
ነገደ መላእክት ላይ ሁሉ ተሹሟል::
✞ከፍጥረት ወገን #ከእመቤታችን ቀጥሎ የቅዱስ ሚካኤልን
ያሕል ክብርና ርሕሩሕ የለም:: በምልጃውም: በረዳትነቱም
የታወቀ መልአክ ነው:: መጽሐፍ "መልአከ ምክሩ
ለእግዚአብሔር" ይለዋል:: "ወስሙ መስተሣሕልም"
ይለዋል:: ቂም የሌለው: ለምሕረት የሚፋጠን: ደግ መልአክ
ነውና::
በብሉይ ኪዳን በመከራ ለነበሩ ቅዱሳን ሁሉ ሞገስ: ረዳትና
አዳኝ ቢሆናቸው "መጋቤ ብሉይ" ተሰኝቷል:: እሥራኤልን 40
ዘመን በበርሃ መርቷል: መግቧልም:: ቅዱስ መጽሐፍ ስለ
እርሱ ብዙ ይላል:: (ዘፍ. 48:16, ኢያ. 5:13, መሳ. 13:17,
ዳን. 10:21, 12:1, መዝ. 33:7, ራዕይ. 12:7)
ደስ የሚለው ደግሞ ርሕሩሑ መልአክ ከእመቤታችን ጋር
#ልዩ_ፍቅር አለው:: ከእናቷ ማሕጸን ጀምሮ እስከ ዛሬ እነሆ
አብሯት አለ:: ደስ ብሎት ይታዘዛታል:: ማማለድ ሲፈልግም
"#እመቤቴ_ሆይ!_ቅደሚ" ይላታል:: ወደ እሳት መጋረጃ አብረው
ገብተው ለዓለም ምሕረትን: በረከትን ያወርዳሉ::
ቅዱስ ሚካኤልን በዚሕች ዕለት ስለ እነዚህ ነገሮች
እናከብረዋለን:-
1.በመላእክት ሁሉ ላይ አለቃ ሆኖ መሾሙን
2.ቅዳሴ ቤቱን (ግብፅ ውስጥ)
3.ቅድስት አፎምያን መርዳቱን
4.ቅዱስ ባሕራንን መጎብኘቱን
5.ቅዱስ ላሊበላን ወደ ሰማያት ማሳረጉን
6.ለፍጥረታት ሁሉ ምሕረት የሚጠይቅበት ዕለት ነውና::
ሊቀ መላእክት በክንፈ ረድኤቱ ከክፉ ሁሉ ይጠብቀን::