ስንክሳር
7.32K subscribers
825 photos
4 videos
37 files
237 links
በስንክሳር channal ስንክሳሩ ተገልጦ ቅዱሳን ይዘከራሉ፣ ወቅቱን የጠበቁ መረጃዎችን ያገኛሉ፡፡ ይከታተሉን!
Download Telegram
#ቅዱስ_ሚካኤል_ሊቀ✞መላእክት
ቅዱስ ሚካኤል በጥንተ ተፈጥሮ #በኢዮር : #ኃይላት
በተባሉት ነገደ መላእክት ተሹሞ ነበር:: ሳጥናኤል በካደ ጊዜ
እግዚአብሔር ባወቀ: አንድም በትሕትናውና ደግነቱ በ99ኙ
ነገደ መላእክት ላይ ሁሉ ተሹሟል::
✞ከፍጥረት ወገን #ከእመቤታችን ቀጥሎ የቅዱስ ሚካኤልን
ያሕል ክብርና ርሕሩሕ የለም:: በምልጃውም: በረዳትነቱም
የታወቀ መልአክ ነው:: መጽሐፍ "መልአከ ምክሩ
ለእግዚአብሔር" ይለዋል:: "ወስሙ መስተሣሕልም"
ይለዋል:: ቂም የሌለው: ለምሕረት የሚፋጠን: ደግ መልአክ
ነውና::
በብሉይ ኪዳን በመከራ ለነበሩ ቅዱሳን ሁሉ ሞገስ: ረዳትና
አዳኝ ቢሆናቸው "መጋቤ ብሉይ" ተሰኝቷል:: እሥራኤልን 40
ዘመን በበርሃ መርቷል: መግቧልም:: ቅዱስ መጽሐፍ ስለ
እርሱ ብዙ ይላል:: (ዘፍ. 48:16, ኢያ. 5:13, መሳ. 13:17,
ዳን. 10:21, 12:1, መዝ. 33:7, ራዕይ. 12:7)
ደስ የሚለው ደግሞ ርሕሩሑ መልአክ ከእመቤታችን ጋር
#ልዩ_ፍቅር አለው:: ከእናቷ ማሕጸን ጀምሮ እስከ ዛሬ እነሆ
አብሯት አለ:: ደስ ብሎት ይታዘዛታል:: ማማለድ ሲፈልግም
"#እመቤቴ_ሆይ!_ቅደሚ" ይላታል:: ወደ እሳት መጋረጃ አብረው
ገብተው ለዓለም ምሕረትን: በረከትን ያወርዳሉ::
ቅዱስ ሚካኤልን በዚሕች ዕለት ስለ እነዚህ ነገሮች
እናከብረዋለን:-
1.በመላእክት ሁሉ ላይ አለቃ ሆኖ መሾሙን
2.ቅዳሴ ቤቱን (ግብፅ ውስጥ)
3.ቅድስት አፎምያን መርዳቱን
4.ቅዱስ ባሕራንን መጎብኘቱን
5.ቅዱስ ላሊበላን ወደ ሰማያት ማሳረጉን
6.ለፍጥረታት ሁሉ ምሕረት የሚጠይቅበት ዕለት ነውና::
ሊቀ መላእክት በክንፈ ረድኤቱ ከክፉ ሁሉ ይጠብቀን::
🌼#ቅዱስ_ሚካኤል_ሊቀ_መላእክት🌼
#ቅዱሳት_መጻሕፍት እንደሚነግሩን የመላእክት ሁሉ
አለቃቸው በፈጣሪው ኃይል ብዙ ድንቆችን ሠርቷል::
ከመጀመሪያው ሰው #አዳም ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ: አምነው
ለሚጠሩት ረዳት ነው:: ዘወትርም ያድናቸው ዘንድ በሚፈሩት
ሰዎች ዙሪያ ይሠፍራል:: (መዝ. 33:7)
¤እግራችን እንዳይሰናከል ዘወትር ይጠብቀናል:: (መዝ.
90:11)
¤የቅዱስ ሚካኤል ስሙ ድንቅ ነው:: (መሳ. 13:18)
¤ከእርሱ በቀርስ የሚያጸና ማን አለና! (ዳን. 10:21)
¤ለሕዝቡም የሚቆም ታዳጊ መልአክ ነው:: (ዳን. 12:1)
¤በፊቱ ሲቆምም ስለ ክብሩ ጫማ አውልቆ: ባጭር ታጥቆ
ነው:: (ኢያ. 5:13)

ይህ ድንቅ መልአክ ከሺህ ዓመታት በፊት በሮም ከተማ
ይህንን ድንቅ ተአምር በዚህች ዕለት መሥራቱን ቤተ ክርስቲያን
ትመሰክራለች:: በድሮው የሮም ግዛት ' #ሩፍምያ ' የምትባል
ከተማ ነበረች:: ይህች ከተማ ክርስቲያኖችም: ኢአማንያንም
ተቀላቅለው የሚኖሩባት ናት::
+በከተማዋ የክርስቲያኖች ቁጥር ትንሽ ቢሆንም በእምነት
ግን ጠንካሮች ነበሩ:: በተለይ ደግሞ የቤተ ክርስቲያኗ መጋቢ ባለ ፍጹም እምነት ሰው ነበር:: በቦታው የቅዱስ ሚካኤል ቤተ
ክርስቲያን በመኖሩም ብዙ ተአምራት ይደረጉ ነበር:: ተበለጥን
የሚል ስሜት የተሰማቸው አሕዛብ (ዮናናውያን) ግን ይሕንን ቤተ ክርስቲያን ለማጥፋት ተማማሉ::
+በቀጥታ ሔደው ቢያፈርሱት ወይም ቢያቃጥሉት በሕግ
እንደሚጠየቁ ያውቃሉና በሥጋዊ ጭንቅላታቸው ዘዴ ያሉትን
መከሩና ወሰኑ:: በከተማዋ ዳር የሚያልፍ አንድ ትልቅ ወንዝ
አለ:: በሞላ ጊዜ ያገኘውን ሁሉ ጠርጐ የሚወስድም ነበር::
+ታዲያ ክፋተኞቹ ሌሊት ሌሊት እየተነሱ የሚሔድበትን
መንገድ ዘግተው: ወደ ቤተ ክርስቲያኑ አቅጣጫ መንገድ ከፈቱለት:: ከቀናት በሁዋላ ከባድ ዝናብ በዚህች ቀን ጣለ:: ወንዙ ትልቅ ነውና ያገኘውን ሁሉ እያገላበጠ ደረሰ::

በወቅቱ በቅዱሱ መልአክ መቅደስ ውስጥ ከመጋቢው በቀር
ሰው አልነበረምና አስፈሪ ድምጽ ሰምቶ ቢወጣ ወንዙ እየደነፋ
ወደ ቤተ ክርስቲያኑ እየመጣ ነው:: አሰበው: ከደቂቃዎች
በሁዋላ ቤተ ክርስቲያኑ እንዳልነበረ ሊሆን ነው::
+እርሱ አንድ ተስፋ ነበረውና ወደ ውስጥ ገብቶ ቅዱስ
ሚካኤልን ተማጸነ:: ከዚያ ላለመውጣትም ወሰነ:: ትንሽ ቆይቶ በታላቅ ኃይል ወንዙ ደረሰ:: በዚህ ጊዜ ግን ቅዱስ ሚካኤል
በግርማ ከሰማይ ወርዶ በወንዙ ፊት ቆመ::

መጋቢውንም "ጽና: አትፍራ" ብሎት በያዘው የብርሃን በትረ-
መስቀል መሬትን አንድ ጊዜ መታት:: በዚያች ቅጽበትም ትልቅ
ሸለቆ ተፈጠረ:: ወንዙም በሸለቆው ውስጥ አልፎ ሔደ::
የሚገርመው ሸለቆው የተፈጠረው በቤተ ክርስቲያኑ በታች
ነው:: ቅዱስ ሚካኤል ግን መጋቢውን ባርኮት በክብር ዐረገ::
በማግስቱ ክርስቲያኖቹ ይህንን አይተው ደስ አላቸው::
መልአኩንም አከበሩት:: አሕዛብ ግን አፈሩ::
Dn yordanos abebe
👉senkesar join us