ስንክሳር
7.32K subscribers
825 photos
4 videos
37 files
237 links
በስንክሳር channal ስንክሳሩ ተገልጦ ቅዱሳን ይዘከራሉ፣ ወቅቱን የጠበቁ መረጃዎችን ያገኛሉ፡፡ ይከታተሉን!
Download Telegram
🌼ቅዱስ ኢያሱ ነቢይ ወመስፍን🌼
ቅዱሱ የተወለደው በምድረ ግብፅ በባርነት ከነበሩ እሥራኤላውያን ሲሆን የቀደመ ስሙ #አውሴ ይባላል:: ዘመኑ #እግዚአብሔር ሕዝቡን ከ215 ዓመታት ባርነት
ሊያወጣ የተቃረበበት ነውና #ሊቀ_ነቢያት_ሙሴ ከምድያም
ሲመለስ ከመረጣቸው ተከታዮቹ ዋነኛው ኢያሱ ነበር:: እሥራኤል ከባርነት ሲወጡ ሙሴ 80 ዓመቱ: ኢያሱ ደግሞ 40 ዓመቱ ነበር::
ሕዝቡ አንገተ ደንዳና ነበርና ለ40 ቀን የታሠበላቸውን መንገድ 40 ዓመት እንዲሆን አደረጉት:: በዚህ ጊዜ ኢያሱ ከመምሕሩ ከሙሴና ከሕዝቡ አልተለየም:: አውሴን ኢያሱ ብሎ ስም የቀየረለት ሙሴ ሲሆን ይሔውም በፈቃደ
እግዚአብሔር ነው:: ኢያሱ ማለት " #መድኃኒት " ማለት ነው:: ለዚሕም ምክንያቶች አሉት:-
1.ለጊዜው አማሌቃውያንን ድል ነስቶ ሕዝቡን አድኗል: ምድረ
ርስትን አውርሷል::
2.ለፍጻሜው ግን ለጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ምሳሌ (ጥላ)
እንዲሆን ነው:: ቅዱስ ኢያሱ በበርሃው ለዘመናት እግዚአብሔርን አምልኮታል::
ሊቀ ነቢያትን ታዞታል (አገልግሎታል): እሥራኤልንም የጦር አለቃ ሆኖ ከአሕዛብ እጅ አድኗቸዋል:: በዚህም በእግዚአብሔርና በሕዝቡ ዘንድ ሞገስን አግኝቷል:: ቅዱስ
ሙሴ #ደብረ_ናባው ላይ ባረፈ ጊዜ ሕዝቡን: ካሕናቱንና
ታቦተ ጽዮንን ተረከበ:: ይህን ጊዜ ዕድሜው 80 እየሆነ ነበር::

እግዚአብሔርም ኢያሱን "ከአንተ ጋር ነኝ" ብሎ በሕዝቡ ላይ ነቢይና መስፍን (አስተዳዳሪ) እንዲሆን ሾመው:: ቅዱሱም ሰላዮችን ልኮ አስገምግሞ:
¤ባሕረ ዮርዳኖስን ከፍሎ:
¤ሕዝቡን አሻግሮ:
¤የኢያሪኮን ቅጥር 7 ጊዜ ዙሮ:
¤በኃይለ እግዚአብሔር አፍርሶ:
¤የኢያሪኮን ነገሥታት አጥፍቶ:
¤ለሕዝቡ ምድረ ርስትን አወረሰ::
የገባዖን ሰዎች "አድነን" ብለው በላኩበት ጊዜ ነገሥተ አሞሬዎንን ይወጋ ዘንድ ኢያሱ ወጣ:: እነዛን ግሩማን ነገሥታት በፈጣሪው ኃይል: በጦርና በተአምራት ድል ነስቶ የእግዚአብሔር ስሙ ከፍ ከፍ አለ:: በዚሕች ዕለትም ለ12ቱ
ነገደ እሥራኤል ርስትን ሲያካፍል ፀሐይን በገባዖን: ጨረቃን ደግሞ በቆላተ ኤሎም (በኤሎም ሸለቆ) አቆመ:: ሰባት #አሕጉራተ_ምስካይ (የመማጸኛ ከተሞችን) ለየ:: ነቢይና መስፍን ሆኖ ሕዝቡን ለ40 ዓመታት አገለገለ:: በመጨረሻም ለሕዝቡ:- "እኔና ቤቴ እግዚአብሔርን እናመልካለን:: (ኢያ. 24) እናንተስ?" አላቸው:: እነርሱም "እኛም እንዳንተ ነን" አሉት:: ለዚህም ምልክት ይሆን ዘንድ 3 ገጽ ያላት ሐውልትን በመካከላቸው አቆመ::
ይህችውም የቅድስት #ድንግል_ማርያም ምሳሌ ናት::
ሐውልቷ 3 ገጽ እንዳላት እመቤታችንም በ3 ወገን (በነፍስ:
በሥጋ: በልቡና) ድንግል ናት:: አንድም በ3 ወገን (ከኃልዮ: ከነቢብ: ከገቢር ኃጢአት) ንጽሕት ናት:: ለዚህም ነው
#አባ_ሕርያቆስ
"ሐውልተ ስምዕ ዘኢያሱ" (የኢያሱ የምስክር ሐውልት አንቺ
ነሽ) ሲል ያመሰገናት::
ታላቁ ነቢይ ኢያሱ ግን ከግብጽ በወጡ በ80 ዓመት: በተወለደ በ120 ዓመቱ (ጥሬው መጽሐፍ ቅዱስ በ110 ዓመቱ ይላል) በወገኖቹ መካከል ዐርፎ በያዕቆብ መቃብር ተቀበረ:: እሥራኤልም ለ30 ቀናት አለቀሱለት::
@dn yordanos abebe