💚💛 ቅዱሳን 7ቱ ደቂቅ 💛❤️
እነዚህ 7 ቅዱሳን ከዘመነ ሰማዕታት እስከ ዘመነ
ጻድቃን የተዘረጋ ታሪክ አላቸው:: 7ቱም ባልንጀሮች ሲሆኑ
በ2ኛው መቶ ክ/ዘመን በኤፌሶን ተወልደው አድገዋል::
ክርስትናን ተምረውም በወጣትነታቸው የንጉሥ ጭፍሮች
ሁነዋል:: የተቀጠሩትም የቤተ መንግስቱን ግምጃ ቤት
ለመጠበቅ ነው:: በሥራቸውም ሆነ በጠባያቸው ደጐች ነበሩና ንጉሡ ዳኬዎስም: ሕዝቡም ይወዷቸው ነበር:: እነርሱ ግን
በጉብዝና ወራት ፈጣሪን ማሰብን መርጠው በፍቅር: በጸሎትና በምጽዋት ይተጉ ነበር:: ከጥቂት ዓመታት በሁዋላ ግን ጭንቅ መከራ መጣ:: ንጉሡ ዳኬዎስ ክርስትናውን ትቶ ጣዖት አምላኪ ሆነ:: አዋጅም አስነገረ:: አዋጁም "ክርስቶስን ያልካደ: ለጣዖትም
ያልሰገደ: ሃብት ንብረቱ ለዘረፋ: እጅ እግሩ ለእስር: ደረቱ
ለጦር: አንገቱ ለሰይፍ: ቤቱም ለእሳት ይሰጣል" የሚል
ነበር:: በዚህ ምክንያት ብዙ ክርስቲያኖች ተሰደዱ::
የበርካቶቹም ደማቸው ፈሰሰ:: # ኤፌሶን የግፍና የአመጻ
ከተማ ሆነች:: የመከራ ጽዋው ጊዜውን ጠብቆ ወደ 7ቱ
ወጣቶች ዘንድ ደረሰ:: ንጉሡ እነሱንም አስጠርቶ "ለጣዖት
ስገዱ" አላቸው:: እነርሱ ግን የአምላካቸውን ፍቅር በዋዛ
የሚቀይሩ አልነበሩምና "እንቢ" አሉት:: ንጉሡ ምንም ክፉና አውሬ ቢሆንም ይወዳቸዋል::
ሊገድላቸው አልፈለገምና አሳሰራቸው:: ከቀናት በሁዋላ
አስጠርቶ ሊያታልላቸው ሞከረ:: ግን አልተሳካለትም:: በዚያ
ወራት ጦርነት ይበዛ ነበርና ግዛት ለማስፋትም ቢሉ ለማስገበር ወጣ:: ከመውጣቱ በፊት ግን 7ቱን አስጠርቶ "አሁን ከእስር
ፈትቻቹሃለሁ:: ከጦርነት እስክመለስ ከልባችሁ ጋር ምከሩ:: ካልሆነ ሞት ይጠብቃቹሃል" ብሏቸው ነበር የወጣው:: ቅዱሳኑ ንጉሡ እንደ ወጣ ተቀምጠው መከሩ:: ውሳኔንም አስተላለፉ::
ዓለምን ንቀው: ሃብት ንብረታቸውን መጽውተው: ትንሽ ሳንቲም ብቻም ይዘው በድብቅ ወጡ:: አንድ ወታደር (በጐች አሉት) ይከተላቸው ነበርና የት እንደ ገቡ ተመለከተ:: ቅዱሳኑ ዘወትር በመዓልትና በሌሊት በበዓታቸው ውስጥ ይተጉ ነበር:: ከእነሱም አንዱ በተራ እየወጣ ቂጣ ይገዛ ነበር::
አንድ ቀን ግን ከእነሱ አንዱ ራት ሊገዛ ሲወጣ ንጉሡ መመለሱን ሰማ:: ወደ በዓቱ ተመልሶ ለወንድሞቹ ነገራቸው:: ከዚያች ቀን በሁዋላ 7ቱም አልወጡም::
በዓታቸውን ዘግተው ሲጸልዩ ደክሟቸው ተኙ:: ከዚያች ቀን
በሁዋላ ግን አልነቁም::
ያ የበጐች ባለቤት (ወታደር) ለብዙ ቀናት አለመውጣታቸውን
ሲመለከት "ሙተዋል" ብሎ አዘነ:: በድብቅ ክርስቶስን
ያመልከው ነበርና:: እርሱ የቅዱሳኑን ተጋድሎ በድንጋይ
ሰሌዳ ላይ ጽፎ ወደ በዓታቸው ውስጥ ጣለው:: ትልቅ ድንጋይም አምጥቶ ገጠመው:: እነዚህ ቅዱሳን ተኝተዋልና አልነቁም:: ቀናት: ወራት: ዓመታት ተዋልደው
ለ372 ዓመት ተኙ:: አንድ ቀን አንድ እረኛ ለሥራ ፈልጐት
ድንጋዩን ፈነቀለው:: በዚህ ጊዜ ቅዱሳኑ ነቁ:: በወቅቱ መልካቸው የወጣት ነው:: እድሜአቸው ግን 400 ሊሞላ ትንሽ ቀርቶት ነበር:: ልክ እንደ # አቤሜሌክ ብዙ
መተኛታቸው አልታወቃቸውምና ከመካከላቸው አንዱ የራት
ዳቦ ሊገዛ ቢወጣ ግራ ተጋባ:: ኤፌሶን የማያውቃት ሌላ
ሃገር ሆነችበት:: ከተማዋ ዘምናለች:: በየቦታው አብያተ ክርስቲያናት: ቅዱስ መስቀልም በየአደባባዩ ተተክለዋል:: ነገሩ ግር ቢለው አንዱን ከመንገድ ጠርቶ "ወንድሜ! ይህቺ ከተማ ኤፌሶን አይደለችምን?" አለው::
እርሱም "አዎ ናት" ብሎት አለፈ::
ችግሩ ግን "ራት ልግዛ" ብሎ ወደ ገበያ ሲሔድ: እርሱ የያዘው ገንዘብ የዳኬዎስ ስም የተጻፈበት መሆኑ የፈጠረው ነበር:: በነጋዴዎቹ "የተደበቀ የጥንት ገንዘብ አግኝተሃል"
በሚል ተከሶም ወደ ንጉሡ # ቴዎዶስዮስ ዘንድ ቀረበ::
(ትንሹ ቴዎዶስዮስ ነው:: የነገሠውም በ5ኛው መቶ ክ/
ዘመን ነው) በክርክሩ መካከል ቅዱሱ የእሱንና የወንድሞቹን ነገር ሲናገር ንጉሡም: ሊቀ ዻዻሱም ( #አባ_ቴዎድሮስ ይባላል)
ተገረሙ:: አብረው ከከተማ ወጥተው ሔደው: 7ቱንም
ሲጸልዩ አገኟቸው:: ፊታቸውም እንደ እግረ ፀሐይ ያበራ
ነበር:: 7ቱም ለ7 ቀናት በኤፌሶን ድውያንን እየፈወሱ: ሰውን
ሁሉ እየባረኩ ቆዩ::
ይህ ሁሉ የተደረገው በወቅቱ "ትንሳኤ ሙታን የለም" የሚሉ
መናፍቃን ተነስተው ብዙ ሰው ክዶ ነበርና ለእነሱ ምሥክር
ሊሆንባቸው ነው:: በርካቶችም በዚህ ድንቅ ተስበው ወደ
ሃየማኖት ተመልሰዋል:: 7ቱ ቅዱሳን ግን በ7ኛው ቀን
በክብር ዐርፈዋል:: ንጉሡ በ7 የወርቅ ሣጥኖች ቀብሯቸዋል::
@dn yordanos abebe