ስንክሳር
7.32K subscribers
825 photos
4 videos
37 files
237 links
በስንክሳር channal ስንክሳሩ ተገልጦ ቅዱሳን ይዘከራሉ፣ ወቅቱን የጠበቁ መረጃዎችን ያገኛሉ፡፡ ይከታተሉን!
Download Telegram
💚💛ቅዱስ አቦሊ ሰማዕት💛❤️
ቅዱስ አቦሊ የሰማዕታቱ #ቅዱስ_ዮስጦስና
#ቅድስት_ታውክልያ ልጅ ሲሆን በ3ኛው መቶ ክ/ዘመን
ያበራ የቤተ ክርስቲያን ዕንቁ ሰማዕት ነው:: የሚገርመኝ
ሦስቱ የግማሹ ዓለም አስተዳዳሪዎች ነበሩ:: ዮስጦስ
ንጉሥ: ታውክልያ ንግሥት: አቦሊ ደግሞ ልዑል ነው::
ነገር ግን ይህንን ክብራቸውን # በክርስቶስ ፍቅር ጐን: ሚዛን
ላይ ቢያኖሩት በጣም ቀሎ ታያቸው:: 3ቱም ከዙፋናቸው
ወርደው: ወገባቸውንም ታጥቀው: ባሮቻቸው በነበሩ ሰዎች
ስለ ክርስቶስ ብዙ ተንገላቱ:: መራራ ሞትንም ታገሱ::
በተለይ ቅዱስ አቦሊ ከአንጾኪያ ወደ ግብጽ (ብስጣ) ይዘው
አምጥተው ክርስትናውን እንዲተው ያላደረጉት የለም::
በቁሙ ቆዳውን ገፈው: በቆዳው አቅማዳ ሰፍተው: ያንንም
አሸክመው: የተገፈፈ አካሉን ጨውና ኮምጣጤ እየቀቡ
አዙረውታል::
እርሱ ግን ጌታ በላከለት ድንቅ መልአክ #ቅዱስ_ሚካኤል
ረዳትነት ሁሉን ችሎታል:: በዘመኑ ብዙ ተአምራትን የሠራ
ሲሆን አንድ ጊዜ ቤት ተንዶ 16 ሰዎች ቢያልቁ የተገፈፈ
ቆዳውን እየጣለባቸው ተነስተዋል:: በተአምራቱና
በተጋድሎውም ብዙ ሺህ አሕዛብን ለክርስትና: ብሎም
ለሰማዕትነት አብቅቷል::
እርሱም ከብዙ የመከራ ጊዜያት በሁዋላ በዚህች ቀን አንገቱን
ተከልሏል:: ጌታችን "ዜናሕን የጻፈውን: ያነበበውንና
የሰማውን ይቅር እለዋለሁ" ብሎ ቃል ኪዳንን ሰጥቶታል::
🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿
ፈጣሪ ከጻድቃንና ሰማዕታት በረከትን አይለይብን::
ወርሐ ነሐሴንም ለበረከት ይቀድስልን::
Dn yordanos abebe