💚💛#አቡነ_ሰላማ_ከሣቴ_ብርሃን💛❤️
ቅዱሱ በትውልዳቸው ግሪካዊ ቢሆኑም ሶርያ
አካባቢ እንዳደጉ ይታመናል:: በቀደመ ስማቸው ፍሬምናጦስ
የሚባሉት አቡነ ሰላማ ወደ ኢትዮዽያ የመጡት በአደጋ
ምክንያት (በድንገት) ቢመስልም ውስጡ ግን ፈቃደ
እግዚአብሔር ነበረበት::
በድንበር ጠባቂዎች (በአደጋ ጣዮች) ከባልንጀራቸው
ኤዴስዮስ ጋር ተይዘው ወደ አክሱም የመጡት በንጉሥ ታዜር
(አይዛና) እና በሚስቱ ሶፍያ (አሕየዋ) ዘመን ነው:: ጊዜው
በውል ባይታወቅም በ4ኛው መቶ ክ/ዘመን ነው::
ፍሬምናጦስ ምንም የመጡበት ዓላማ ስብከተ ወንጌል
ባይሆንም በአክሱም ቤተ መንግስት አካባቢ ይሰበኩ ነበር::
ያን ጊዜ በጃንደረባው ቅዱስ ባኮስ የተቀጣጠለው የክርስትና
ችቦ ውስጥ ውስጡን በሃገሪቱ ነበረና ፍሬምናጦስ
አልተቸገሩም:: በተለይ ሕጻናቱን (ኢዛናና ሳይዛናን) ገና
ከልጅነት ስላስተማሯቸው ነገሮች የተሳኩ ሆኑ::
ልክ ንጉሥ ታዜር እንደ ሞተ ሁለቱ ሕጻናት በመንበሩ
ተቀመጡ:: ፍሬምናጦስንም ወደ ግብፅ ዻዻስና ጥምቀት
ከመጻሕፍት ጋር እንዲመጣላቸው ላኩ:: ሐዋርያዊ ቅዱስ
አትናቴዎስም ፍሬምናጦስን "ሰላማ" ብሎ ሰይሞ : በዽዽስና
: በንዋየ ቅድሳትና በመጻሕፍት ሸልሞ መለሳቸው::
አቡነ ሰላማ ወደ ኢትዮዽያ እንደተመለሱ ከነገሥታቱ ጀምረው
ለሕዝቡ ጥምቀትን አደሉ:: ኢዛናና ሳይዛናም አብርሃ (አበራ)
እና አጽብሃ (አነጋ) ተብለው ስማቸው ተደነገለ:: ከዚያ
በሁዋላ ድንቅ በሚሆን አገልግሎት ነገሥታቱ : ዻዻሱ
ሰላማና ሊቀ ካህናቱ እንበረም ለክርስትና መስፋፋት በጋራ
ሠርተዋል::
✝ የአቡነ ሰላማ ትሩፋቶች:-
1.ዽዽስናና ክህነትን ከእውነተኛ ምንጭ አምተዋል::
2.ክርስትናና ጥምቀትን በሃገራችን አስፋፍተዋል::
3.ቅዱሳት መጻሕፍትን ከውጭ ልሳኖች ተርጉመዋል::
4.ገዳማዊ ሕይወትን ጀምረዋል::
5.አብያተ ክርስቲያናትን አንጸዋል::
6.ግዕዝ ቋንቋን አሻሽለዋል::
ሀ.ከግራ ወደ ቀኝ እንዲፃፍ
ለ.እርባታ እንዲኖረው
ሐ.ከ"አበገደ" ወደ "ሀለሐመ" ቀይረዋል::
ባላቸው ንጹሕ የቅድስና ሕይወት ለሕዝቡ ምሳሌ ሆነዋ::
"ወበእንተዝ ተሰይመ ከሳቴ ብርሃን" እንዲል ገድላቸው
በነዚህ ምክንያቶች "ከሣቴ ብርሃን" (ብርሃንን የገለጠ) ሲባሉ
ይኖራሉ:: በመጨረሻም ከመልካሙ ገድል በሁዋላ በ352
ዓ/ም ዐርፈው ተቀብረዋል::
@dn yordanos
ቅዱሱ በትውልዳቸው ግሪካዊ ቢሆኑም ሶርያ
አካባቢ እንዳደጉ ይታመናል:: በቀደመ ስማቸው ፍሬምናጦስ
የሚባሉት አቡነ ሰላማ ወደ ኢትዮዽያ የመጡት በአደጋ
ምክንያት (በድንገት) ቢመስልም ውስጡ ግን ፈቃደ
እግዚአብሔር ነበረበት::
በድንበር ጠባቂዎች (በአደጋ ጣዮች) ከባልንጀራቸው
ኤዴስዮስ ጋር ተይዘው ወደ አክሱም የመጡት በንጉሥ ታዜር
(አይዛና) እና በሚስቱ ሶፍያ (አሕየዋ) ዘመን ነው:: ጊዜው
በውል ባይታወቅም በ4ኛው መቶ ክ/ዘመን ነው::
ፍሬምናጦስ ምንም የመጡበት ዓላማ ስብከተ ወንጌል
ባይሆንም በአክሱም ቤተ መንግስት አካባቢ ይሰበኩ ነበር::
ያን ጊዜ በጃንደረባው ቅዱስ ባኮስ የተቀጣጠለው የክርስትና
ችቦ ውስጥ ውስጡን በሃገሪቱ ነበረና ፍሬምናጦስ
አልተቸገሩም:: በተለይ ሕጻናቱን (ኢዛናና ሳይዛናን) ገና
ከልጅነት ስላስተማሯቸው ነገሮች የተሳኩ ሆኑ::
ልክ ንጉሥ ታዜር እንደ ሞተ ሁለቱ ሕጻናት በመንበሩ
ተቀመጡ:: ፍሬምናጦስንም ወደ ግብፅ ዻዻስና ጥምቀት
ከመጻሕፍት ጋር እንዲመጣላቸው ላኩ:: ሐዋርያዊ ቅዱስ
አትናቴዎስም ፍሬምናጦስን "ሰላማ" ብሎ ሰይሞ : በዽዽስና
: በንዋየ ቅድሳትና በመጻሕፍት ሸልሞ መለሳቸው::
አቡነ ሰላማ ወደ ኢትዮዽያ እንደተመለሱ ከነገሥታቱ ጀምረው
ለሕዝቡ ጥምቀትን አደሉ:: ኢዛናና ሳይዛናም አብርሃ (አበራ)
እና አጽብሃ (አነጋ) ተብለው ስማቸው ተደነገለ:: ከዚያ
በሁዋላ ድንቅ በሚሆን አገልግሎት ነገሥታቱ : ዻዻሱ
ሰላማና ሊቀ ካህናቱ እንበረም ለክርስትና መስፋፋት በጋራ
ሠርተዋል::
✝ የአቡነ ሰላማ ትሩፋቶች:-
1.ዽዽስናና ክህነትን ከእውነተኛ ምንጭ አምተዋል::
2.ክርስትናና ጥምቀትን በሃገራችን አስፋፍተዋል::
3.ቅዱሳት መጻሕፍትን ከውጭ ልሳኖች ተርጉመዋል::
4.ገዳማዊ ሕይወትን ጀምረዋል::
5.አብያተ ክርስቲያናትን አንጸዋል::
6.ግዕዝ ቋንቋን አሻሽለዋል::
ሀ.ከግራ ወደ ቀኝ እንዲፃፍ
ለ.እርባታ እንዲኖረው
ሐ.ከ"አበገደ" ወደ "ሀለሐመ" ቀይረዋል::
ባላቸው ንጹሕ የቅድስና ሕይወት ለሕዝቡ ምሳሌ ሆነዋ::
"ወበእንተዝ ተሰይመ ከሳቴ ብርሃን" እንዲል ገድላቸው
በነዚህ ምክንያቶች "ከሣቴ ብርሃን" (ብርሃንን የገለጠ) ሲባሉ
ይኖራሉ:: በመጨረሻም ከመልካሙ ገድል በሁዋላ በ352
ዓ/ም ዐርፈው ተቀብረዋል::
@dn yordanos