#የዋልድባ ጉዞ ማስታወሻ- ክፍል አራት
(ወንድወሰን ውቤ)
.....ጌታችን ሆይ እስራኤልን እኮ በኪደተ እግርህ ረግጠኻታል፡፡ ዓለምን ያዳንክበትን ፍቅር በመስቀል ገልጸህባታል፡፡ ታዲያ ይህች ምድር እንዴት ዳግማዊት ኢየሩሳሌም ትሆን ዘንድ ይቻላታል? ጌታም የአንዳቸውን ከወይራ የተሠራ መቁጠሪያ ወስዶ መሬት ላይ ጣለ፡፡ ዕለቱን በቅላ ዛፍ ሆነች፡፡ መከራውን የተቀበለባት መስቀልም ከእርሷ ወጣ፡፡ ተመስጦ ሰጣቸውና በራእይ ዳግም በአይሁድ ካህናት እጅ ሲንገላታ፣ ሕማማተ መስቀልን ሲቀበል፣ ነፍሱን በፈቃዱ ሲሰጥና በሦስተኛው ቀን ሞትን ድል አድርጎ ሲነሣ ዐሳያቸው፡፡
መከራውን እንደ እናቱ እመቤታች ድንግል ማርያምና እንደ ፍቁረ-እግዚእ ዮሐንስ ከልብ በሚፈልቅ እንባ ተካፈሉ፤ ድሉንም ከልብ በተቀዳ ሀሴት አጣጣሙ፡፡ አሁን ዐይነ-ሥጋቸው ደክሞ የነፍሳቸው ዐይን በደንብ በራ፡፡ አሁን እምቢታቸው ጠፍቶ ታዛዥነት ነገሠባቸው፡፡ ሰው ክርስቶስ እንዲሁ የከፈለለትን የፍቅር ዋጋ ሲረዳ የደምና የሥጋ ስሌትን አቀዝቅዞ እንደ ቅዱስ ጴጥሮስ አንተ ታውቃለህ ማለት ይጀምራል፡፡ እነሱም “ጌታ ሆይ እንዳልክ ይሁን የባረክልንን ዳጋማዊት ኢየሩሳሌምን ተቀብለናል፡፡ የተጠመክበት ዮርዳኖስ፣ የተንገላታህበት ጎልጎታ፣ የተሰቀልክበት ቀራንዮ አለንና በዚህ መሆን ለኛ መልካም ነው፡፡” አሉ፡፡
እንግዲህ ዋልድባ ገዳም ጌታ ራሱ ባርኮ የገደመው ቅዱስ ቦታ መሆኑ ነው ታላቅነቱ፡፡ አስቀድሞም በሕጻንነቱ እመቤታችን ይዛው በተሰደደች ጊዜ በዚህ ቦታ ዐርፈው ነበርና ያኔ እንደባረካት ይነገራል፡፡ ባርኮ አጸናቸው፣ ለምንኩስና የተዘጋጁትንም የድንጋይ ቆብ ጠርቦ አመነኮሳቸውና ተሰወረ፡፡ ከእነሱም የጸኑት “እኛም አብረን ተአንተ፤” (ከአንተ አንለይም) አሉና “ሃሌ ሉያ ለአብ፤ ሃሌ ሉያ ለወልድ፤ ሃሌ ሉያ ለመንፈስ ቅዱስ!!!” ብለው እሱ ገብቶበታል ባሉት ዋሻ ገብተው ተሰውረው ቀሩ፡፡ ገዳሙም አብረንታንት መድኃኔዓለም ተባለ፡፡ አንተን ስንከተልህ፣ ስናመልክህ እንኖራለን፣ ካንተ ወዴት እንሔዳን ማለታቸው ነው፡፡ በእርግጥም ይኼው ለብዙ ክፍለ ዘመናት ሁሌም ኢየሱስ ክርስቶስ በፊታቸው እንደተሰቀለ ሁኖ የሚታያቸው፣ መከራ መስቀሉን የሚያስቡ እውነተኛ መናንያን በተጋድሎ፣ በፍቅርና በትህትና ተረዳድተው ይኖሩበታል፡፡
ዋልድባ በዚህ ታላቅ ገዳም ሥር ለሚጠቃለሉና በሰፊው የገዳሙ ክልል ውስጥ ለሚገኙ የዋልድባ አብረንታንት መድኃኔዓለም፣ የዋልድባ ሰቋር ኪዳነ ምሕረት፣ የዋልድባ ዳልሽሐ ኪዳነ ምሕረት እና ለሌሎችም በርከት ላሉ የገዳሙ ቦታዎች የሚያገለገግል የጋራ ስም ሲሆን አብረንታት መድኃኔዓለም ደግሞ ዋናው ገዳም ነው። ጌታ የተሰወረበት ዋሻ ከገዳሙ የሁለት ሰዓት ያህል መንገድ የሚወስድ ሲሆን ዛሬም ድረስ በምእመናን ይጎበኛል፡፡ አፈሩ ድውያንን ይፈውሳል፡፡ የዋሻው መጨረሻ ስለማይታወቅ አባቶች በድንጋይ ካብ የዘጉትን በጨለማው ዋሻ ውስጥ ዳስሼ ተመልክቻለሁ፡፡
ማዬ-ዮርዳኖስ ዘዋልድባ”
የዋልድባ ገዳም ጸበል ማየ-ዮርዳኖስ ትባላለች፡፡ ባለቤቱ መድኃኔዓለም “እንደ ተጠመቅሁባት እንደ ዮርዳኖስ ትሁንላችሁ” ብሎ ባረኳታል። ጸበሏ ለክብረ በዓሉ የሚመጣው ያ! ሁሉ ሕዝብ ሲጠመቅባት ቢሰነብትም ትንሽ እንኳ አትጎድልም። ኋላም ለእርሱና ቤት ለቀሩ ወገኖቹ ፈውስ ትሆነው ዘንድ ገጠሬው በቅልና ቅምጫና ከተሜው በጀሪካን እየሞላ ይወስዳል። ማየ ዮርዳኖስ ግን አሁንም ድረስ አንድ ኩባያ የተቀዳባት አትመስልም። መጉደል ዐታውቅም፤ ሁሌም ሙሉ። የሚቀዳት ቢጠፋም ሞልታ አትፈስም፡፡ የኔ ብጤ ደፋርና ሳያዩ ከሚያምኑት ወገን ለመሆን የሚቸገር እልከኛ ኅሊና ያለው በስተምሥራቅ በኩል ባለችው የጸበል ቤቱ ብቸኛ መስኮት ብቅ ብሎ ለአፍታ ማየት ይችላል። የሰማውን በዐይኑ ዐይቶ ለማረጋገጥ።
ታዲያ ጸበሏን ለመቅዳት አይደለም፤ ወደ ጸበል ቤቱ ለመግባት ካህን መሆን ብቻ በቂ አይደለም። መነኮስ መሆንም የፈቃድ ወረቀት ማግኘት ማለት አይደለም። ይልቁንም ሥምረት የተነሣ የማኅበረ መነኮሳቱ አባል መሆን አለበት። ሥምረት ማለት በዋልድባ ገዳም ብቻ ያለ ገዳማዊ ሥርዐት ነው። መነኮሱ ይህ ሥርዐት ሲፈጸምለት ነው የታላቁ ገዳም አባል የሚሆነው። ከማኅበረ መነኮሳቱ የሚቆጠረው፤ ደቀ-ሳሙኤል የሚባለው። ነፍሱን ይማረውና አያቴ አያይ ከዐርባ ዓመት በፊት ወደ ገዳሙ ወርዶ ነበር፡፡ በጊዜው አንድ ያልተፈቀደለት ሰው ወደ ጸበል ቤቱ በመግባቱ ምክንያት ጸበሏ መድረቋንና ከብዙ ምህላ በኋላ እንደገና መፍለቅ እንደጀመረች፣ በዚያ ቀንም በርካቶች እንደተፈወሱ በዐይኑ ያየውን መስክሮልኛል።
🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻
#ዋልድባ_ፀጥታና_ነፍስ_የቆረቡበት_ገዳም!
አብረንታንት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ውስጥ ከሚገኘው አንድ ዛፍ ላይ የተንጠለጠለ ደወል አለ። ደወሉ የትም ቦታም እንደምናገኛቸው ዓይነት ደወሎች ከብረት የተሠራ አይደለም፤ ከጣውላ እንጂ። ይህ ደወል በየባዕታቸው በጸሎት የሚተጉትን፣ ለሥራ የተሰማሩትን መነኮሳት ለጸሎተ ማዕድ፣ ሌሊት ሌሊት ደግሞ ለሰዓታት፣ ለኪዳን የሚጠራ የቤተክርስቲያንዋ ድምፅ ነው።
በዓሉ በሚከበርበት ሳምንትም በየሰዓቱ ከሚደወለው የዚህ ደወል ድምፅና የምእመናኑ ምህላ በቀር ሌላ ጩኸት ከፍ ባለ ድምፅ ሲሰማ አባቶችን አያስደስትም። በበዓሉ የታደመው ምእመን ሁሉ የቆየውን ገዳማዊ አኗኗር ማክበር አለበት። በዙሪያው የተሰወሩ በርካታ ቅዱሳን የሞሉበት ምድር ነውና ያልተለመደ ጩኸት በጸሎት ላይ ያሉ በርካታ መናንያንን ያውካል ተብሎ ስለሚታሰብ ክልክል ነው። ስለዚህ መዝሙር መዘመር ምስጋና ነውና ችግር የለም በሚል እሳቤ ሰብሰብ ብለው ቢጀምሩ የመጀመሪያው የተግሣፅ ቃል የሚመጣብዎት አጠገብዎ ካረፉ ተሳላሚዎች ነው። ይህንን ተግሳጽ ቸል ብለው ቢቀጥሉ ከገዳማዊያኑ አንዳች ክልከላ አይመጣብዎትም። ብቻ ኀዘናቸውን ያበዙታል እንጂ።
በገዳሙ ውስጥ ቅዳሴ እንኳ የሚቀደሰው በዓመት አምስት ጊዜ ብቻ ነው። እነርሱም የመጋቢት መድኃኔዓለም፣ የሆሳዕና፣ የትንሣኤ፣ የጥምቀት እና የሐምሌ አቦ በዓላት ናቸው። ከዚህ ውጭ ኪዳን ይደርስበታል፣ሰዓታት ይቆማል፣ የመነኮሳቱ የማኅበር ጸሎት አይስታጎልም። መቼም የአክሱም ጽዮንን 365 ቀናት የማያቋርጥ የቅዳሴ አገልግሎት የሚያውቅ ሰው በዓመት አምስት ጊዜ ብቻ የሚቀደስበትን የዋልድባን ታሪክ ሲሰማ ሊገረም ይችላል። እውነቱ ግን ይህ ነው። ምክንያቱ ደግሞ ገዳሙ ለተጋድሎና ለጥሞና የተሰበሰቡ መናንያን ባዕት በመሆኑ ነው።
***
አንድ ሽማግሌ የጌታን ሥዕለ አድኅኖ (አክሊለ ሶክ) እና ሥዕለ ማርያም ለአንድ አባት እንድናደርስላቸው አደራ አሉን፡፡ መልእክቱን የምናደርስላቸው አባት ባዕት ከአብረንታንት መድኃኔዓለም ሠላሳ ደቂቃ ያህል ይወስዳል(ስሙን ካልተሳሳትኩ ማይ ሎሚ መሰለኝ የሚባለው)፡፡ አርድእት እንዳንረብሻቸው አስጠንቅቀው መንገዱን አመላከቱን፡፡ ከጓደኞቼ ጋር ሔድን፡፡ የሎሚና የሰርኪን ዛፍ በሚበዛበት ጥቅጥቅ ያለ ደን ውስጥ አንዲት በዓት አገኘን፡፡ በገዳሙ ሥርዐት መሠረት በተወሰነ የጊዜ ክፍተት ውስጥ ሦስቴ አጨበጨብን፡፡ መልስ የለም፡፡
ከአንድ ሰዓት በላይ ጠበቅን፣ ብቅ ያለ ሰው የለም፡፡ በመጠበቅና ቶሎ በመመለስ መካከል እያወላወልን ሳለን አንዲት ሎሚ ከተጠጋናት ዛፍ ተቆርጣ አጠገባችን ወደቀች፡፡ ማጅላን የምንለው ጓደኛችን ተሸቀዳድሞ አነሣት፡፡ “እንዴ ሰሌ!? ይኸ እኮ ገዳም ነው፤ ያውም ዋልድባ፡፡ ወድቆ አግኝቻለሁ ብለህ ብትወስድ በርሐው ውስጥ ወድቀህ ትቀራለህ እንጂ ቤትህ አትገባትም፡፡” ወረጠበ የምንለው(ተፈሪ አበራ) ማጅላንን አስጠነቀቀው፡፡
“