ስንክሳር
7.32K subscribers
825 photos
4 videos
37 files
237 links
በስንክሳር channal ስንክሳሩ ተገልጦ ቅዱሳን ይዘከራሉ፣ ወቅቱን የጠበቁ መረጃዎችን ያገኛሉ፡፡ ይከታተሉን!
Download Telegram
Watch ""አባቴ ሚካኤል" - ዘማሪት ፍቅርተ የተሻወርቅ | ልብን ደስ የሚያሰኝ ዝማሬ ||New ethiopian orthodox mezmur 2022" on YouTube
https://youtu.be/9l7rLq_X55g
Watch "የኤፍራጥስ ወንዝ መድረቅ አንድምታዎች - ዲ/ን ከሣቴብርሃን ገ/ኢየሱስ" on YouTube
https://youtu.be/JkKkmVtzYQU
Watch ""ዳሩ ግን ከሩቅ ሆነው አዩትና ተሳለሙት" ዕብ. 11÷13 | መምህር ዲያቆን ከሣቴብርሃን ገ/ኢየሱስ" on YouTube
https://youtu.be/BRhwmDNljgM
Watch ""ትጉኃን የአምኑ ልደቶ - ትጉኃን ልደቱን ያምኑታል" - ሊደመጥ የሚገባው የልደት መልእክት" on YouTube
https://youtu.be/z-d4xuntJBE
#ስለምንታገልለት_ዕውቀት_ይኑረን


ከፊታችን ቅዳሜ ጀምሮ በKesatebirhan Ze Tewahdo Telegram Channel በLive stream በሰሞናዊ የቤተ ክርስቲያን ትኩሳት መነሻነት መታወቅ ያለባቸውን መሠረታዊ ነጥቦች እንማማራለን።

#የሚነሡ_ጉዳዮች

1. ዶግማ ፣ ቀኖና ፣ ትውፊት ምንድናቸው? ዶግማ ፈረሰ ፣ ቀኖና ተጣሰ ፣ ትውፊት ተፋለሰ ሲባል ምን ማለት ነው። ቅጣቱስ ምንድን ነው?

2. ምሥጢር ክህነት ፣ ምን? ለምን? እንዴት? ፣ ክብረ ክህነት።

3. መፈንቅለ ክህነት በዘመነ ሙሴ ፣ የደብተራ ኦሪት ግርግርና መዘዙ

4. አቤሴሎማዊነትና ዖዝያናዊነት በቤተ ክህነት

5. የጵጵስና ታሪክ በኢትዮጵያ

5. የጳጳሳት ስም ፣ ብፁዕ አቡነ እገሌ መባልና የስም ለውጥ የአስኬማ ፣ የጽሕምና የልብሳቸው ፣ የበትራቸውም ምሥጢርና ውክልና

5. ኦርቶዶክስ በኦሮሞ ታሪክና ፖለቲካ መነጽር

6. የአሁኑን ፈተና እንዴት እንመልከተው? እንዴትስ እንመክተው?


#ሰዓት_ከምሽቱ_3_ሰዓት

#ዕለታት_ቅዳሜና_እሑድ

የስሜት ብቻ ሳይሆን የዕውቀትም ጦር ዕቃ ለውጊያው ያስፈልገናል።

#ሊንኩን ተጭነው የChannelu Member በመሆን ይጠብቁ።
👇👇👇👇👇👇👇

https://tttttt.me/KesatebirhanZeTewahdo
Watch "ተዋሕድዋ - የአድዋ ድል እና ተዋሕዷዊ ገድል" on YouTube
https://youtu.be/7_6A_kMAvSs
እኔና የቆሎ ጓደኞቼ የአብነት መምህራችን መጋቤ ምሥጢር አለቃ መሠረት ተሰማን ቢያንስ በወር አንደዜ “ለምን መጽሐፍ አይጽፉም?” የሚል የልጅነት ቅንዓት ፣ ጉጉትና ምኞት የወለደው ሃሳብ በጉባኤ መሃል ወርወር ባደረግላቸው ቁጥር እንዲህ ብለው ይመልሱ ነበር።
“መጽሐፍ ልጻፍ ብል ቤት መቀመጥ ፣ መጻሕፍት ማገላበጥ ግድ ይሆናል። ይህ ደግሞ የእናንተን የትምህርት ጊዜ ይሻማል። ስለዚህ እኔ እናንተው ላይ መጻፉን መርጫለሁ። እናንተ ደግሞ መጽሐፉን ትጽፉታላችሁ።”
ይህ አነጋገራቸው “ሰዎች ሁሉ በሚያውቁትና በሚያነቡት በልባችን የተጻፈ መልእክታችን እናንተ ናችሁ። እናንተም በሕያው እግዚአብሔር መንፈስ እንጂ በድንጋይ ጽላት ያልተጻፈ ፥ በእኛም የተገለገለ የክርስቶስ መልእክት እንደሆናችሁ የተገለጠ ነው።” የሚለው የቅዱስ ጳውሎስን ኃይለ ቃል ይመስላል።
እንዳሉትም እስከ መጨረሻይቱ ሕቅታ ድረስ አንድነትን ሦስትነትን ማመንን የሚያጸና ትምህርት እየጻፉ አረፉ። “መጽሐፉን እናንተ ትጽፉታላችሁ” የሚለው ትንቢትም ከዐሥር ዓመታት በፊት በበኩር የመንፈስ ልጃቸው በዲ/ን ዶ/ር አቤል ኃይሉ “የማእዘን ራስ” መጽሐፍ ተፈጽሟል። እነሆ አሁን ደግሞ የገዛ ብዕራቸው ውጤት “መጽሐፈ መሠረት” በሚል ርእስ ለኅትመት ብርሃን በቃ።

ይኼን መጽሐፍ የማዘጋጀት እድሌን አደንቃለሁ። ከፈቃደ እግዚአብሔር ጋር ይኼ ኃላፊነት ወደ እኔ እንዲመጣና እኔም በልዩ ትኩረት እንድፈጽመው ያደረጉኝ ክስተቶች ግን አሉ። በሕይወተ ሥጋ ሳይለዩን የአብነት ትምህርት የምስክር ወረቀት ከሰጧቸው የመጨረሻ ልጆቻቸው ማካከል አንዱ መሆኔ ፣ የመጨረሻ የጉባኤ ስብከታቸውን ያደግሁበትና በሰ/ት/ቤት አመራርነት ያገለገልኩበት ደብሬ ባዘጋጀው የኅዳር ሚካኤል ጉባኤ ላይ ጋብዣቸው ያስተማሩ መሆኑ ፣ በመጨረሻ በግል ሄጄ የተቀበልኩት የ”ዕዳ አለብህ” ቃላቸው ፣ የጊዜ ዕረፍታቸው የዓይን እማኝነት ዕጣ ከመንፈስ ልጆቻቸው መካከል እኔ ጋር የወደቀ መሆኑ በአጋጣሚ የሆነ አይመስለኝም።

ይልቁንም ዜና ሕይወታቸውንና ሥራዎቻቸውን ይዞ የወጣው የዳረጎት ልዩ ዕትም ዋና አዘጋጅ መሆኔ እኔ በግሌ ካሰባሰብኳቸው ሰነዶች በብዙ እጥፍ የሚበልጡ የልዩ ልዩ ዘመን አበርክቶአቸው እጄ እንዲገባ ምክንያት ሲሆን አንድ ላይ ሰብስቦ መጽሐፍ የማድረግ ሐሳብ ተፀነሰ። በፈቃደ እግዚአብሔርም እዚህ ደረሰ።

መጽሐፉ ሦስት አበይት ምእራፎች ያሉት ሲሆን በመጀመሪያው ምእራፍ ለኮርስ ስልጠና የተዘጋጁ ወጥ ሥራዎች ቀርበዋል። በሁለተኛው ምእራፍ በልዩ ልዩ ጉዳዮች ላይ በጽሑፍ ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች በጽሑፍ የሰጡትን ምላሽ ይዟል። የመጨረሻው ምእራፍ የሕይወት ታሪክ አምድ ሆኖ የግላቸውን የጉባኤ ቤት ቆይታ በወፍ በረር ፣ ለስንክሣርና ግብረ ሕማማት መተርጉም ወዳጃቸው ለሊቀ መዘምራን ላእከ ማርያም ወልደ ኢየሱስ የጻፉትን በቅኔ የተዋዛ ጽሑፍ ፣ እንዲሁም ዜና ሕይወታ ለማርያም ድንግልን አካቷል።
በቅጽ አንድ የተካተቱት ሥራዎቻቸው ለኅትመት በሚበቃ ምሉዕነት ስለተገኙ ብቻ እንጂ በቀጣይ ተሟልተው የሚዘጋጁ ብዛት ያላቸው ርእሰ ጉዳዮች እንደሚኖሩ ይታወቅልኝ።
በተረፈ ስለ ብዕራቸው የሥነ ጽሑፍ ውበት ፣ የምሥጢር ጉልበትና የሐሳብ ፍሰት እየተነተኑ ሊቁን ለእናንተ ማስተዋወቁ አስፈላጊ አልመሰለኝም። “ከፍሬያቸው ታውቋቸዋላችሁ” ይላልና ቃሉ ከፍሬያቸው ዕወቋቸው። የቻልኩትን ያህል ለቅሜ በያዛችሁት ቅርጫት አኑሬላችኋለሁ። የተባረከ ማዕድ ይሁላችሁ።
https://www.instagram.com/p/CqYPYpXIA4T/?igshid=MDJmNzVkMjY=
ፊርማ ለወዳጅ

ለመላው አብሮ አደጎች ፣ አብሮ አገልጋዮች ፣ ክላስ ሜቶች ፣ ወዳጆችና የመንፈስ ልጆች በሙሉ።

አንዳንዶቻችሁ በቅርብ ለገበያ የቀረበውን መጽሐፌን " አዘጋጁ ካልፈረመበት አንገዛም ሙተን እንገኛለን" ማለታችሁን ሰምቻለሁ። ሌሎቻችሁ ደግሞ "ለበዓል መጥተን ሰኞ ፣ ማክሰኞ ሂያጅ ነን። መጽሐፉን አስቀምጥልን" እያላችሁ በውስጥ መስመር እየወተወታችሁኝ ነው። እኔ የሺህ ወዳጅ ወንድማችሁ ወገቤ እስቲንቀጠቀጥ ጥፌ ማዘጋጀቴ አንሶ እናንተን እግር በእግር እየተከተልኩ መጣፍ ማቀብልበት ጊዜውም ጉልበቱም የለኝምና የግቢ ጉባኤ ፣ የዓለም ት/ቤት ፣ የፕሪፕ ፣ የሚካኤልና የሌላም ሌላም የሰፈር ወዳጅ ፣ ጓደኛ ፣ ደቀ መዝሙርና ደቂቀ መዝሙር ሁሉ በትንሣኤ ዋዜማ በቀዳም ሥዑር ዕለት በደብረ መድኃኒት ሰ/ት/ቤት አዳራሽ ከ4 ሰዓት ጀምሮ ከትተህ ላግኝህ። ማኅተምና ፊርማዬን ከስምህ ጋር ከትቤ እንዳስፈላጊነቱም በሥዕል አስውቤ ዘላለማዊ የወዳጅነት ማስታወሻ ይሆን ዘንድ መጽሐፈ መሠረትን አበረክትልሃለሁ። መርኃ ግብር አይደለም ደግሞ መጥቶ መሄድ ነው። አንድ የጋራ መገናኛ ለመፍጠር ያመች ዘንድ ነው። ማን ያውቃል በስንት እግዚኦታ ፣ ሠርግና ምርቃት መገናኘት ያልሆነለትን ጀማ ማገናኛ ሰበብ ይሆናል። ዘር ፣ ቀለም ፣ ጾታ ፣ እድሜ ፣ ባች ፣ ጸባይ ፣ የአመራርነትና የሥራ እርከን አይለይም። "ከሣችን አውቀዋለሁ" የሚል ሁሉ ጎራ ይበል።
https://www.instagram.com/p/Cq8b-10oXh8/?igshid=MDJmNzVkMjY=
የምኩራቡ

የምኩራቡ ቸር መም'ር፥
ቃል ሆኖ ቃል ሚናገር፥
ወንጌል
ሆኖ ወንጌል ሚሰብክ
በሰው ልሣን በፍጡር መልክ።


ለሙሴ ሕግን የሰጠ፥
ቀርቦ ክርታሱን ገለጠ፥
ያናገረውን በነቢይ፥
አስተማረው በቃል ዐቢይ።
"የእግዚአብሔር መንፈስ በእኔ ላይ፥
ወንጌል እንድሰብክ ለነዳይ፥
ምሥራች ሚነገርባት፥
ዓመተ ምሕረት ይቺ ናት።"


ሁሉን ሠርተህ "ምሰሉኝ" ያልህ፥
ትኁት መምህር በልብ የዋህ፥
የሰገደልህም ረቢ፥
ኒቆዲሞስ ያ'ይሁድ መጋቢ።
እንበሌከ ሠራዔ ሕግ፥
ሚሽር ሚያጸና ሚደነግግ፥
"አነ እብለክሙ" ሚል ማነው፥
ሁሉ 'ሚደግም ያንተን ነው።


ምኩራብ ሸመነች ሕግ ሸማን፥
ለበሰችው ቤተ ክርስቲያን።
ምዕመን ፅጌረዳ አቀፈ፥
እሾሁ ለአይሁድ ተረፈ።
ምኩራብ አመጣች ሰደፍን፥
በዕንቁ ባሕርዩ አተረፍን፥
ምኩራብ ምግበ ሕይወት ሰቀለች፥
ምዕመን ቁርባን ተቀበለች።

✍️ከሣቴ ብርሃን
🎼ኤርምያስ በገና
Forwarded from Daregot Media
የኒቆዲሞስ ታላቅነት

በዚያ “አልቦ ዘመድ በጊዜ ተዋርዶ” በተባለበት ፣ ሐዋርያቱ እንኳ ጥለው በሸሹበት ዕለተ ዓርብ የልጇን መለኮት የተዋሐደው ሥጋ ከአርማትያሱ ሰው ከዮሴፍ ጋር ከመስቀል አውርዶ በቀበረ ጊዜ እመቤታችን ለኒቆዲሞስ የመረቀችው ምርቃት “ታላቅ ያድርግህ!”(1) የሚል ነበር።

ይኸውም ሲደርስ ሲፈጸም ሊቁ ቅዱስ ያሬድ የታላቁ አቢይ ጾም ፯ተኛ ሳምንት መጠሪያ አድርጎት ፤ በጾመ ድጓውም “ወሀሎ አሐዱ ብእሲ እምፈሪሳውያን ዘስሙ ኒቆዲሞስ ፣ዘሖረ ኀቤሁ ቀዲሙ ሌሊተ ፣ ወይቤሎ ለኢየሱስ እጓለ አንበሳ ሰከብከ ወኖምከ ፣ አንሥአኒ በትንሣኤከ” (2) እያለ ዘምሮለት በዓመቱ ታሪኩ ሲነገር ታላቅነቱ ሲወሳ ይኖራል።

ሙሉ ጹሑፉን ያንብቡ https://telegra.ph/ዲረጎት-04-05

Join us @daregot
አንዳንድ ነገሮች ስለ “እዩት” መጽሐፍ
(Part 2)



2. የመዝሙር ግጥም መድብል ነው።

እንኳን የመዝሙር ግጥም መድብል ፣ የመንፈሳዊ ግጥም መድብል አቅርቦት እንኳ በጣት ሚቆጠር ነው። በግሌ ከዲያቆን መኩሪያ ጉግሣ የቀደሙ ኅትመቶችና የአሁን “የእኔ መክሊት” የመዝሙር ግጥም ውጭ የታተመ የአንጋፋና አዳዲስ ጸሐፍት መዝሙር ሥራ አልሰማሁም። የመዝሙር ግጥሞች ያለ ዜማቸው ራቁታቸውን ሲቀርቡ የሚነበቡ ፣ የሚስቡ ፣ የሚያስገነዝቡ መሆን አለባቸው ፤ እንደ ቅኔ አባታቸው ብዬ በጽኑ አምናለሁ። በዚህ አንጻር የእኔ የ5 ዓመት የብርዕ ምርት ምን ያህል አጥጋቢ ነው የሚለውን በሕዝባዊና ሙያው ሂስ ሚዛንነት ማስገምገም ስላስፈለኝ 81 የጌታ ሥራዎች ፣ በመጀመሪያው ቅጽ/ ቅጽ ስብሐተ እግዚአብሔር ለንባብ ብርሃን ይበቃሉ። ሌሎቹም ቅጾች ይቀጥላሉ።

__
http://tttttt.me/Andkelem
http://tttttt.me/Andkelem
http://tttttt.me/Andkelem
እንኳን ለብርሃነ ትንአሣኤው በሰላም አደረሳችሁ።
ውዳሴ ትንሣኤ |በዘማሪት ወርቅነሽ ኃይሉ!
https://youtu.be/ua2_FUMuJD0
https://youtu.be/ua2_FUMuJD0
"ዝክረ ኒቅያ" ጀምሯል። የቅኔ መምህሬን መጋቤ ምሥጢር ኃይለ ልዑል ገነትን የፊት መስመር ተሰላፊ ሆነው በማየቴ ካሁኑ ደስ ደስ እያለኝ ነው። ዳሩ ግን "ዝክረ ኒቅያ" አርዮሳዊ መነኮሳትን ፣ ንስጥሮሳዊ ጳጳሳትን የሚያወግዝ ፣ ምን ዋና ፣ ምን አጋዥ ፣ ምን ተወጋዥ መጽሐፍ እንደሆነ የሚያነጽር ጸሎተ ሃይማኖታዊ ረቂቅ የሚያረቅ ፣ 81ዱዋዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጓሜና ቀኖና ውዝግብን የሚያጠራ ሕጋዊ ውሳኔ የሚወስን ካልሆነ የአበል ወጪ የከሰርንበት ኪሳራ ፣ ቁና ሰፍታ እንደለበሰችው "ስም እንዲጠራ" ነው ሚሆነው። የልብ ሕመም ለያዛት ቤተ ክርስቲያን ማስታገሻ የሚወጋ ጉባኤ እንደማይሆን እጠብቃለሁ።

ከሣቴ ብርሃን
___
t.me/andkelem
t.me/andkelem