St.Paul's Hospital Millennium Medical College
19K subscribers
2.07K photos
24 videos
12 files
465 links
St. Paul's is a leading public hospital and medical college in Addis Ababa, Ethiopia.
Download Telegram
ʺእንደ ሀገር የተመዘገቡ ስኬቶችን እጅ ለእጅ ተያይዘን ማስቀጠል ይኖርብናልʺ
ክብርት ወ/ሮ ፍሬህይወት አበበ የጤና ሚኒስትር ድኤታ
የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጀ የ2018 ሀገራዊ ልማት እና የጤናው ዘርፍ እቅድ ዙሪያ የኮሌጁ አመራሮችና ሰራተኞች ጋር ውይይት ተደረገ፡፡በዚሁ ወቅት በክብር እንግድነት የተገኙት የጤና ሚኒስቴር ሚንስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ ፍሬህይወት አበበ እንደተናገገሩት በሁሉም ዘርፍ እንደ ሀገር የተመዘገቡ አበረታች ለውጦች ለማስቀጠል ሁላችን በጋራ እጅ ለእጅ ተያይዘን ተባብረን መስራት ይገባል ብለዋል፡፡

በስብሰባው ለውይይቱ መነሻ የሚሆን ሰነድ በአስተዳደር ልማት ም/ዳይሬክተሩ በአቶ ጀማል ሽፋ ዝርዝር ገለፃ በማድረግ የቀረበ ሲሆን በመድረኩም ሀገራዊ የልማትና የጤናው ዘርፍ እቅድ ቀርቦ ሰፊ ውይይት ከተደረገበት በኃላ በውይይቱም ከተሳታፊዎች አስተያየቶች እና ጥያቄዎች በስፋት የተነሱ ሲሆን እንደ ሀገር የመጡ ለውጦችን በማጠናከር ክፍተቶችን አቅዶ መስራት እንደሚያስፈልግም ተገልጿል፡፡
በአገልግሎት አሰጣጥ ሂደት የሚስተዋሉ ችግሮች እና ከጤና ባለሙያው አንፃር የሚነሱ ጥያቄዎችን ለመፍታት በሪፎርም ማዕቀፍ ተካተው በተቋም ደረጃ እንዲሁም በጤና ሚኒስቴር በኩል ታቅዶ እየተሰራ መሆኑንም ሚኒስትሯ አስረድተዋል፡፡
በመጨረሻም የእለቱ የክብር እንግዳ በክብርት ወ/ሮ ፍሬህይወት አበበ ተሰጥቶ ስብሰባው ተጠናቋል፡፡
ለምን የጤና ምርመራ አያደርጉም?
ያውም በነጻ!
ከሐምሌ 21 ጀምሮ እንጠብቅዎታለን!
ይምጡ! ስለ ጤናዎ ይወቁ!
ዛሬ!
በነጻ የጤና ምርመራ የሚያደርጉበት ቀን ነው!
እንጠብቅዎታለን: :
አስቀድመው ጤና ምርመራ ማድረግዎ ብልህነት ነው!
የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ የክረምት የበጎ ፈቃደኝነት ነጻ የጤና ምርመራ አገልግሎት ማስጀመርያ መርሃ ግብር ተካሄደ::

በዚህ የመክፈቻ ሥነ ሥርዓት ክብርት ወ/ሮ ፍሬሕይወት አበበ የጤና ሚኒስቴር ሚንስትር ዴኤታ ተገኝተው የክረምት ነጻ የጤና ምርመራውን መርሐግብር በይፋ ከፍተዋል: : ክብርት ሚንስትርዋ በመክፈቻው ሥነ ሥርዓት ኮሌጁ ማሕበረሰቡን በዚህ መንገድ በተጠናከረ መንገድ ለማገልገል ያለውን ቁርጠኝነት ያሳያል ብለዋል: :

የኮሌጁ ምክትል የልማት ና የአስተዳደር ምክትል ፕሮቮስት አቶ ጀማል ሺፋ በበኩላቸው እንደተናገሩት 50,000 የሚደርሱ ዜጎች በሰሞኑ የጤና አገልግሎት ነጻ ሕክምና እንዲያገኙ እቅድ ተይዟል:: በተጨማሪም ለቀዶ ሕክምና ለማግኘት ይጠባበቁ ከነበሩት መካከል በቁጥር 200 የሚደርሱት በዚህ ሳምንት አገልግሎቱን እንዲያገኙም ይደረጋል ብለዋል : :

በዚህ ለአንድ ሳምንት በሚቆየው የጤና ምርመራ ማንኛውም ሰው አገልግሎቱን ማግኘት እንደሚችል ተገልጿል::
ባለፈው ዓመት ኮሌጁ በሰጠው ተመሣሣይ ነጻ አገልግሎት በሀገር አቀፈ ደረጃ እውቅና ማግኘቱ ይታወሣል: :
St. Paul’s Hospital Millennium Medical College Tree Planting Campaign Officially Launched! 🌱

We are proud to announce the official launch of our Green Legacy Tree Planting Campaign! The event was honored by the presence of H.E. Frehiwot Abebe, State Minister of Health, who officially kicked off the campaign by planting trees within our campus alongside the college management team. 🌿🌼

As part of our commitment to a greener Ethiopia, the St. Paul’s community is set to plant 20,000 trees in the Entoto area — contributing to environmental sustainability and public health.
St. Paul’s College Community Rebuilds Homes for Vulnerable Families

The St. Paul’s Hospital Millennium Medical College community has officially launched a home renewal project to support vulnerable families.

The initiative aims to rebuild and renovate houses for five low-income families, starting today with active participation from students and staff.