እወቅና!
ዶር አብዱ አደም በሙያቸው የካንሰር ሕክምና ስፔሻሊስት ናቸው፡፡በዚህ ዓመት ኮሌጁ ተማሪዎቹን ባስመረቀበት ወቅት በከፍተኛ የስራ አፈጻጸማቸው ልዩ አውቅና ተሰጥቷቸዋል፡፡ ይህን በከፍተኛው የኮሌጁ ቦርድ የተፈቀደውን እውቅና ያገኙት ዶር አብዱ ፡ የስራ አፈጻጸማቸው እጅግ ከፍተኛ በመሆኑ ነው፡፡
ኮሌጁ ለዶር አብዱ በኮሌጁ ለመጀመሪያ ጊዜ የካንሰር ሕክምናን በማደራጀት፡ ወረቀት አልባ የኤሌትሮኒክ የሕክምና መረጃ ኣያያዝ(EMR) በማስጀመር፡፡ የሕክምና አገልግሎት ጥራት ማሻሻያ ክፍል ሃለፊ በመሆን በሰሩበት ወቅትም የላቀ አስተዋጽኦ በማበርከታቸው እና በተለይ አዲሱ የካንሰር ሕክምና ማእከል ሕንጻ በዲዛይንና በግንባታ ወቅት ቅርብ ክትትል በማድረግ ጉልህ ስራዎችን ሰርተዋል፡፡
በአገራችን የመጀመሪያ የሆነውን Adult Hematology and Medical Oncology Fellowship እንዲጀመርና በስርዓተ ትምህርት ቀረጻም ወቅት ሁነኛ አስተዋጽኦ አበርክተዋል፡፡ አሁንም የስልጠናው አስተባባሪ በመሆን እያገለገሉ ይገኛሉ፡፡
የኮሌጁ ቦርድም ዶር አብዱ ላደረጉት መጠነ ሰፊ አስተዋጽኦ በላቀ የስራ አገልግሎት ልዩ ሽልማት ተሸላሚ አድርጓቸዋል፡፡ ይህን ሽልማታቸውን ከጤና ሚኒስትርዋ ከክብርት ዶር መቅደስ ዳባ እጅ ተቀብለዋል፡፡ እንኳን ደስ ያልዎ ዶር አብዱ!
Dr. Abdu Adem, our Clinical Oncologist, has received the prestigious Excellence Award for his outstanding achievements and performance within the college. His accomplishments are numerous, and he was honored with this special award by H.E. Dr. Mekedes Daba, the Minister of Health.
#Recogination_SPHMMC #Recogination_Clinical Oncologist #sphmmc