ወቅታዊ ጉንፋን እና ጉንፋን መሰል የመተፈንሻ አካላት ህመም
የጉንፋን ሕመም በተፈጥሮ የላይኛውን የመተንፈሻ የሰውነት ክፍሎች ማለትም አፍንጫን፣ ጎሮሮን እና የአየር መተላለፊያ ባንቧን የሚያጠቃ ተላላፊ ሕመም ነዉ።
‘ሪኖ ቫይረስ’ ለጉንፉን መከሰት ዋና ምክንያት ሲሆን፣ ኮሮና፣ ኢንፍሉዌንዛ፣ ፓራ ኢንፍሉዌንዛ፣ አር ኤስ ቪ(RSV) ቫይረሶች ደግሞ ለጉንፉን መሰል ህመሞች መከሰት ዋና ዋና ምክንያቶች ናቸዉ። ከተጠቀሱት ቫይረሶችም ለጉንፋን ሕመም መከሰት 50 በመቶ ድርሻውን የሚይዘው ሪኖ ቫይረስ ነው፡፡ በደረቅ ነፋሳማ ወቅት የአፍንጫ የውስጠኛው ስስ ሽፋን “ሙከስ መምብሬን” ስለሚደርቅ የጉንፋን ሕመም እና ተላላፊነቱ ይጨምራል፡፡ የክረምት ወራት ወይም የዝናብ ወቅት ማብቃቱን ተከትሎ መስከረምን ጨምሮ በጥቅምትና ህዳር ወራት እንደዚህ አይነት ጉንፋን መሰል ህመም የሚጠበቅ ነው፡፡
ሕመሙ ከሰው ወደ ሰው የሚተላለፈውም በቫይረሱ የተጠቃ ሰው በሚያስልበት ወይም በሚያስነጥስበት ጊዜ እንደሆነና በተጨማሪም ሰዎች ቫይረሱ ያረፈበትን የበር እጀታ፣ ጠረጴዛ ወይም በሕመምተኛው የተነካካንን ሰው እጅ ከነኩ በኋላ አፋቸውንና አፍንጫቸውን ሲነካኩ ቫይረሱ ለመተላለፍ በሚፈጠርለት ምቹ ሁኔታ ነው።
የጉንፋን ሕመም የመጀመሪያ ምልክቱ ከመጀመሩ አንድ ቀን በፊት ተላላፊ ሊሆን ይችላል፤ ሕመሙ ከጀመረ ከ 5 እስከ 10 ባሉት ቀናት ደግሞ ሕመምተኛው ቫይረሱን ያስተላልፋል። ህመሙ አብዛኛዉን ጊዜ እስከ 2 ሳምንት ሊቆይ ይችላል። ምልክቶቹም እንደ የአፍንጫ ፈሳሽ መብዛት፣ ሳል፣ ትኩሳት፣ ራስ ምታትና ጉሮሮን መከርከር፣ ማስነጠስ፣ አይን ማሳከክ እና መቅላት፣ ማስታወክ፣ ከፍ ሲልም የትንፋሽ ማጠር፣ ከፍተኛ ድካምና የምግብ ፍላጎት መቀነስ ዋና ዋናዎቹ ናቸዉ።
አስፈላጊው ጥንቃቄ ካልተደረገ በሽታው የመዛመት እድሉ ከፍ ሊል እንደሚችል፤ በተለይ ቀዳሚ ተጎጅ የሚሆኑትህጻናትና አረጋውያን ናቸው፡፡ በተለይ ደግሞ እንደ አስም፣ የስኳር በሽታ፣ ካንሰር እና ሌሎች ሥር የሰደዱ ተጓዳኝ የጤና ችግር ያሉባቸው ሕሙማን ከፍተኛ ጥንቃቄ ልናደርግላቸው እና ወደ ጤና ተቋማት በመሄድ አስፈላጊዉን ምርመራና ህክምና ሊያደርጉ ይገባል፡፡ በተጨማሪም የጉንፋን ሕመም የጆሮ ኢንፌክሽን እና የሳንባ ምች ሕመምን ጨምሮ ለተለያዩ ሕመሞች ተጋላጭ ሊያደርግ ይችላል፡፡
ጉንፋን መሰል በሽታን ከምንከላከልባቸው መንገዶች መካከልም የእጅ ንጽህናን መጠበቅ፣ ሰዎች በተሰበሰቡበት ቦታ የአፍና አፍንጫ ጭምብል(ማስክ) በማድረግና በዕለት ኑሯችን የምንጠቀምባቸውን በከባቢዎቻችን የሚገኙ ቁሳቁሶችን ማጽዳት እና የብዙሃን ማጓጓዣ ትራንስፖርት ላይ መስኮቶችን በመክፈት በቂ የአየር ዝዉዉር እንዲኖር በማድረግ የበሽታዉን የመተላለፍ ዕድል መቀነስ ይቻላል፡፡ የበሽታው ምልክት የሚታይበት ሰው በፍጥነት በአቅራቢያው ወደሚገኝ የጤና ተቋም በመሄድ አስፈላጊውን የህክምና ምክር አና ዕርዳታ ማግኘት አለበት፡፡

The Hospital Donates Vital Nutritional Formula to Support Cancer Patients at SPHMMC
In a generous act of compassion, Silk Road General Hospital has donated Revilife Pepticare, a crucial nutritional formula designed for special medical purposes, to support cancer patients at St. Paul’s.
During the handover ceremony, Dr. Sisay Sirgu, the Provost of SPHMMC, presented Silk Road General Hospital with a Certificate of Recognition. This token of appreciation acknowledges their unwavering commitment to the well-being of those in need.
Revilife Pepticare is specifically tailored to aid patients with eating restrictions, digestion challenges, and metabolic disorders, ensuring they receive the essential nutrition required for their recovery.
This thoughtful donation underscores the hospital's dedication to improving the lives of those battling cancer and other health challenges.

Today, we are joyfully celebrating Ethiopian Christmas with our patients in the wards. It is a time of love, warmth, and togetherness, as we share this special occasion with those who need it most. Through this celebration, we hope to bring comfort and light to their hearts, reminding them that they are not alone. May the spirit of this blessed day fill our hearts with peace and joy, bringing healing and hope to
የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ በ2017 ዓ.ም በአምስት የነርሲንግ ፖስት ቤዚክ ስፔሻሊቲ ማለትም በ Emergency and Critical Care Nursing፣ በ operating Theater Nurse፣ በ neonatal Nursing፣ በ pediatric Nursing እና በ surgical Nursing ለመማር የምትፈልጉ እና መስፈርቱ የምታሟሉ ከ 28/04/201617 - 14/05/2016 ዓ.ም online https://portal.sphmmc.edu.et/Web/Announcement እንድትመዘገቡ እናሳወቃለን፡፡
የመመዝገቢያመስፈርቶች፣
• በነርሲንግ ዲፕሎማ ደረጃ 4 የተመረቀች/የተመረቀ በሁሉም ስፔሻሊቲ ፕሮግራሞች መወዳደር ይችላሉ፣
• የሚድዋይፍሪ ዲፕሎማ ደረጃ የተመረቀች /የተመረቀ በጨቅላ ህፃናት እና በህፃናት ነርሲንግ መመዝገብ ይችላል፣
• ከመስሪያቤታቸው የስፖንሰርሺፕ ደብዳቤ ማምጣት ወይም ከፍሎ መማር የሚችል/የሚትችል፡፡
• ኮሌጅ የሚያዘጋጀውን የቃል እና የፁሑፍ ፈተና ማለፍ የሚችል/የምትችል፣
• ሙሉ ጤነኛ የሆነ/የሆነች
• አንድ ዓመት የስራ ልምድ ያለው/ ያላት
ማሳሰቢያ፡
የመመዝገቢያ የማይመለስ 100 ብር በኮሌጁ ንግድ ባንክ አካዉንት ቁጥር 1000006577192 በማስገባት ደረሰኝ upload ማድረግ
ዲፕሎማ፤ትራንስክሪፕት እና የስራ ልምድ upload ማድረግ
አስፈላጊውን ዶክመንት ያላሟላ ፈተናው ላይ እንደማይቀመጥ በጥብቅ እናሳውቃለን፡፡
ኮሌጁ ማደሪያና ምግብ አያዘጋጅም
ለበለጠ መረጃ 0112756089 ይደዉሉ
ለመመዝገብ ወደ ሲስተሙ ስትገቡ ማድረግ ያለባቹ
ወደ መመዝገቢያ ሊንኩ ከገባቹ በኃላ
Apply now / Apply for admission የሚለውን ሊንክ መጫን
የሚፈልጉትን ፕሮግራም በመምረጥ Apply ማለት
ቀጥሎ basic information በማስገባት summit ሲባል Application has successfully submitted የሚል ኖቲፊኬሽን ከApplication number ጋር አብሮ ይመጣል Application number ለቀጣይ ዶክመንት ለማስገባት ስለሚጠቅም ቁጥሩን መያዝ ግዴታ ነው።
ቀጥሎ upload receipt የሚለውን በመጫን የመመዝገቢያ የተከፈለበትን ደረሰኝ upload ማድረግ
ቀጥሎ upload document ላይ በመግባት ዶክመንታቹን አስገብታቹ ስትጨርሱ Summit document የሚለውን በመጫን ምዝገባውን ታጠናቅቃላቹ።
ሬጅስትራር ጽ/ቤት

Call for Application, PhD in Public Health Program
St. Paul’s Hospital Millennium Medical College, School of public health would like to invite applications for admission in PhD in public health for the 2017 E.C (2025/2026) Academic Year. Prospective interested applicants of the PhD in Public Health under one PhD program for Health Sciences are expected to meet the following requirements:
1. Applicants must first take the University National Graduate Admission Test (NGAT) and fulfill the minimum requirement to pass the exam.
2. Applicants having second degree /MPH or MSc/ with thesis from any recognized higher learning institutes in any Health Science fields
3. Applicants holding non-thesis Master’s degree can also apply based on their Research experiences (at least one published original article as a lead author in peer reviewed journal).
4. Applicants less than 45 years of age are preferable
5. Presentation of a sound preliminary PhD proposal concept note (synopsis)
6. Willingness to participate in teaching activities at SPHMMC when it is necessary.
7. Able to transfer official transcript and copy of the Master’s degree
8. Can bring a proof that there is a budget for conducting the PhD research (signed sponsorship)
9. Recommendation letters from three referees two of which are academicians in a related field of the candidate.
10. Self-sponsored or international students should pay application, registration, tuition fee and other necessary fees based on the SPHMMC’s regulation, while sponsored student should present their letter.
11. Each foreign relevant master degree will be evaluated individually by the Education and training authority (ETA) with regard to the degree equivalence and competences necessary to carry out scientific research.
12. As a medium of training is in English, applicants whose medium of instruction was not English for the first degree and master’s degree would be required to provide a valid English language test score of 6 for ILETS and 70% for TOEFL
13. The applicant assessed as pre-doctoral candidate can be invited to take a pre-doctoral courses.
14. All applicants considered for the PhD candidacy must pass an interview and evaluation of concept note
15. The suitability of the applicant can be further demonstrated with additional
Information (exam results, experience, professional qualifications...).
16. If deemed necessary, the doctoral council can impose an additional entrance exam in the form of a presentation and/or interview.
Document required:
Degree and transcript
Work experience
Recommendation letters
Sponsorship letter (download the form from the application portal)
List of publications
*merge files if necessary
Registration Guide
Click online application link: https://portal.sphmmc.edu.et/Web/Announcement
Read the instruction carefully
Click Apply now / Apply for admission
Choose the program you want to apply and click “Apply”
Insert basic information and summit. You will get the following message
“Application has been successfully submitted. Your application number is: 00005. Pay your application fee (400 Birr) using SPHMMC bank account number 1000006577192 (CBE) and upload the receipt file. Finally, you can upload your academic documents on this portal.”
You should record your application number. It is required to upload receipt and document
Click “upload receipt” which is located on the left side of the window and upload the receipt. You will get the following message:
“You have successfully uploaded your receipt. Now, you can upload your academic documents.”
Click “upload document” which is located on the left side of the window and upload the document and click Summit document.
Application dates
• Application opening date: Jan 6, 2025
• Application closing date: Jan 20, 2025
• Exam/synopsis presentation date: Jan, 27/ 2025 (will be notified on social media if there is any change)
For more information contact the registrar office/school of public health

የሕዝብ ተወካዮች ምክርቤት ያጸደቀው የጤና አገልግሎት አስተዳደር እና ቁጥጥር አዋጅ ቁጥር 1362/2014 ምን ጉዳዮችን ይደስሳል?
በቅርቡየጤና አገልግሎት አስተዳደር እና ቁጥጥር አዋጅ ቁጥር 1362/2017 ምክር ቤቱ ባካሄደው 13ኛ መደበኛ ስብሰባው ላይ የጤና አገልግሎት አስተዳደርና ቁጥጥር ረቂቅ አዋጅን ከጤና፣ ማህበራዊ ልማት፣ ባህል እና ስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የቀረበለትን ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ መርምሮ አጽድቋል።
አዋጁ በጤናው ዘርፍ በተለያዩ ሕጎች በተበታተነ እና ለአፈፃፀም ግልፅ ባልሆነ ሁኔታ የሚገኙ የጤና አገልግሎቶችን የሚመለከቱ ድንጋጌዎች በአንድ ማእቀፍ ሕግ እንዲወጣ አስፈላጊነቱ ስለታመነበት እና ከእነዚሁ ድንጋጌዎች በተጨማሪም አሁን ወቅቱ ከደረሰበት የቴክኖሎጂ ደረጃ የተጣጠመ አዳዲስ የጤና አገልግሎት ለመዘርጋት፣ የማህበረሰባችን ባህልና ሃይማኖትን፣ነባር ህጎችን በጥንቃቄና በጥልቀት በመመልከት እንደዚሁም በስራ ላይ የነበሩት ድንጋጌዎችን በማሻሻል ወጥ የሆነ እና ለአፈፃፀም ግልፅ የሆነ የጤና አገልግሎት አሰጣጥ ተግበራዊ ለማድረግ የሚደግፍ ሲሆን የጤና ባለሙያዎችን ሙያዊ መብትንም ያካተተ አዋጅ ነው፡፡ በዋናነት የዚህ የጤና አገልግሎት አስተዳደር እና ቁጥጥር አዋጅ ዋና ዋና አላማዎቹ፡-
የጤና መመዘኛ መስፈርቶችን በማውጣት እና በመተግበር ተጠያቂነትና ጥራት ያለው እንዲሁም ለሁሉም ተደራሽ የሆነ የጤና አገልግሎት አሰጣጥ ስርዓት ለመዘርጋት፤
የሐገሪቱን የጤና አገልግሎት በማዘመን የሕብረተሰቡን የጤና ፍላጎት ለማሟላት የሚያስችል አሰራር ተግበራዊ ለማድረግ ፤
የጤና ተቋማትና ባለሙያዎች፤እንዲሁም የጤና ነክ ተቋማት ቁጥጥር ሥርዓት ቀልጣፋ ዉጤታማና ወጥነት ያለው እንዲሆን ለማድረግ፤
የጤና አገልግሎት ስርዓቱን ለማሻሻል የሚካሄዱ የጥናትና ምርምር ስራዎች የሚመሩበት እና የሚተገበሩበት አሰራርን ለመዘርጋት፤
የጤና መረጃ ስርዓት በመዘርጋት በመረጃ ላይ የተመሰረተ ውሳኔ አሰጣጥን በማረጋገጥ የጤና እና ጤና ነክ አገልግሎትን ጥራትና ደህንነት፤ ተደራሽነት እና የተገልጋይ ደህንነትን ለማሻሻል ነዉ፡፡
እነዚህን ዓላማዎች ከማሳካት አንጻር አዋጁ አጠቃላይ የጤና አገልግሎት እና ልዩ የጤና አገልግሎቶች የሚሰጡበትን ስርዓት፤ የጤናዉ ዘርፍ የሰዉ ሀብት ልማት እና አስተዳደርን የተመለከቱ፤የጤና ባለሙያዎች፣ ጤና ተቋማት፣ ጤና-ነክ ተቋማት እና የምግብና መጠጥ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ቁጥጥር፤ የጤና ምርምር አተገባበር፤ የጤና መረጃ አያያዝ ስርዓት፤የጤና ፋይናንስ እና የመንግስትና የግል አጋርነት፤ እንዲሁም ይህንን አዋጅ የሚያስፈጽሙ አካላት የሚኖራቸዉ ተግባር እና ሀላፊነትን የተመለከቱ ዝርዝር ድንጋጌዎች ተካተዋል፡፡
በእነዚህ በተጠቀሱ ዋና ዋና የአዋጁ ይዘቶች ዉስጥ የእናቶች እና ህጻናት ጤና አገልግሎት እንደማንኛዉም የጤና አገልግሎት ሽፋን የተሰጠዉ ሲሆን አዋጁ በተለይም የእናቶች እና ህጻናት ጤናን በቀጥታ የሚመለከቱ የተለያዩ ድንጋጌዎችን አካቷል፡፡
ለአብነትም የጤና አገልግሎት አሰጣጥ መርሆች መካከል ሴቶች እና ህጻናትን ለመንከባከብ አዎንታዊ ልዩነት ሊደረግ እንደሚችል፤ ክትባትን በተመለከተ ማንኛዉም ወላጅ፣አሳዳጊ ወይም በህግ ሀላፊነት የተጣለበት ሰዉ ህጻናትን የማስከተብ ግዴታ እንዳለበት፤እንዲሁም በተፈጥሯዊ መንገድ ልጅ ማግኘት ወይም ወላጅ መሆን ያልቻሉና በባለሙያ የተረጋገጠ የትዳር ጥንዶች በቴክኖለጂ በታገዘ ሁኔታ ልጅ ማግኘት የሚችሉበትን አማራጭን በተመለከተ ዝርዝር ስርዓቶችን አስቀምጧል፡፡ ይህ ተግበራዊ ሲሆንም ቀደም ሲል አገልግሎቱን ለማግኘት ከሀገር ውጪ የሚደረግን ጉዞ ፣እንግልት እና ከፍተኛ ወጪ ያስቀራል ማለት ነው፡፡
አዋጁ ማንኛውም የጤና ተቋም እና የጤና ነክ ተቋማት የሚሰጠውን የአገልግሎት ጥራትና ደህንነት እንዲሁም ግልጽነትና ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ የቁጥጥር ስርዓቱ የሚጠናከርበትን ድንጋጌዎች አስቀምጧል ፡፡ ተገልጋዮች በጤና አገልግሎት ሰጪ ተቋማት አገልግሎት ለማግኘት ሲመጡ ጥራቱን የተጠበቀ ፣ፍትኃዊ የሆነ ፈጣንና የተሟላ አገልግሎት የማግኘት መብት እንዳላቸው እና የአገልግሎት ሰጪ ተቋማትን ተጠያቂነት ባመላከተ መልኩ በግልጽ አስቀምጧል፡፡
ሌላው አዋጁ በግልጽ ድንጋጌ ያስቀመጠው ጉዳይ የጤናው ዘርፍ ሰራተኛ መብትን ነው፡፡ለአብነት ፡- በሌሎች የሐገሪቱ ህጎች ስለ ስራ ቦታ ደህንነት የተደነገጉ ድንጋጌዎች እንደተጠበቁ ሆኖ የጤናው ዘርፍ ሰራተኛ በስራው ባህሪ ምክንያት ተጋላጭ ለሚሆንባቸው በሽታዎች ቅድሚያ የጤና አገልግሎት የማግኘት መብት እንዳለው ደንግጓል፡፡የጤናው ዘርፍ የመንግስት ሰራተኛ የጤና መድህን አባልነት ሙሉ መዋጮ በመንግስት እንደሚሸፈንም አስቀምጧል፡፡ ለዚህም ዝርዝር አፈጻጸም የሚኒስትሮች ምክር ቤት በሚያወጣው ደንብ ይወሰናል፡፡
ከዚህ ጋር በተያያዘም በሕክምና አገልግሎት አሰጣጥ አማካይነት በወንጀል የተጠረጠረ ማንኛውም የጤና ባለሙያ በወንጀል ሥነ-ሥርዓት ሕግ ድንጋጌዎች መሠረት በቁጥጥር ስር የሚውለው ባለሙያዉ ወንጀሉን ስለመፈጸሙ ምክያታዊ ጥርጣሬ እንዲኖር የሚያስችል ማስረጃ ሲኖር እንደሆነም አዋጁ ይደነግጋል፡፡
ሌላው አዋጁ በዋናነት ያስቀመጠው የልብ እና የመተንፈሻ አካላት የአሰራር ሥርዓት መመለስ በማይችልበት ደረጃ ሥራቸውን ሲያቆሙ ወይም የአንጎል ሞት ሲረጋገጥ በመሳርያ ላይ የተመሰረተ የአተነፋፈስ ስርዓትን በሶስት አግባነብት ባላቸዉ ባለሙያዎች ዉሳኔ ማቋረጥ እንደሚቻል እና ይህም ቤተሰብን ለማይመለስ ነፍስ ከአላስፈላጊ እንግልትና ወጪ እንደሚታደግ ይታመናል። የዚህ ድንጋጌም ዝርዝር አፈጻጸም ሚኒስቴር መስርያ ቤቱ በሚያወጣው መመሪያ የሚወሰን ይሆናል፡፡
ሌላው በዚህ አዋጅ ላይ ተደነገገው የደም፣ ህዋስ፣ ህብረ ህዋስ፤ የአካል ክፍል ወይም የአካል ልገሳ እና የንቅለ-ተከላ ህክምና አገልግሎትን የተመለከተ ሲሆን በዚሀም ማንኛውም ሰው አግባብነት ባለው አካል ፊት ቀርቦ በሚሰጠው ፈቃድ መሰረት ደም፣ ህዋሱን፣ ህብረ ህዋሱን፣ የአካል ክፍሉን፣ አካሉን መለገስ ይችላል፡፡መለገስ የሚችለውም ለዚሁ ዓላማ ሲባል ለሚቋቋመው ተቋም ብቻ ነው፡፡ ከዚህ ጋር በተያዘዘ ማንኛውም ሰው በሽያጭ ወይም ሌላ ኢኮኖሚያዊ ጥቅም ለማግኘት ሲባል ደም፣ ህዋስ፣ ህብረ ህዋስን፤ የአካል ክፍል እና አካልን መለገስም ሆነ መቀበል የተከለከለ ነው፡፡ ከህጋዊ የልገሳ ስርዓት ውጭ የተገኘ አካል፤ የአካል ክፍል፤ ሕብረ ሕዋስ ወይም ሕዋስ አገልግሎት ላይ ማዋል የተከለከለ ነው፡፡
ከሞት በኋላ ተፈጻሚ ስለሚሆን ልገሳ ማንኛውም ሰው ህይወቱ ሲያልፍ ህዋሱን፣ህብረ ህዋሱን ፤ የአካል ክፍሉን ወይም አካሉን ለመለገስ ፈቃዱን አግባብነት ላለው አካል ሊለግስ ይችላል። ይህንንም በዝርዝር አዋጁ አካቷል፡፡
በአጠቃላይ አዋጁ መንግስት በህገ መንግስቱ የተጣለበትን ጥራት ያለዉ የጤና አገልግሎት ለዜጎች የማቅረብ እና ተደራሽ የማድረግ ግዴታዉን ለመወጣት የሚያስችለዉን የተሻለ መደላድል የሚፈጥር በመሆኑ በቀጣይ ይህንን ሀላፊነት ከመወጣት አኳያ በአዋጁ የተቀመጡ ድንጋጌዎችን ወደ ተግባር ለማዉረድ የሚያስችሉ ዝርዝር ደንቦችና መመሪያዎች የሚወጡ፤ እንዲሁም የአሰራር ስርዓቶች የሚዘረጉ ይሆናል፡፡
(ምንጭ፡ ጤና ሚኒስቴር-ኢትዮጵያ )