ባለፈው ሐምሌ ወር በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ኮሌጅ ከ90 ሺህ ወገኖች ነጻ የሕክምና ምርመራ ባገኙበት ብሄራዊ የክረምት በጎ ፍቃድ ጤና አገልግሎት የተሳተፉ ሠራተኞች የተመሠገኑበት የእውቅና መርሐግብር ዛሬ ተካሄደ: :
በተጨማሪም ለአራት ቀናት ሲካሄድ ቆይቶ ባለፈው ሐሙስ የተጠናቀቀው እና በኤግዚቢሽን በፓናል ውይይቶች የታጀበው እና የክልል የሆስፒታል እና የፌዴራል ሆስፒታሎች ኃላፊዎችንም ጭምር ያሳተፈው 3ኛው የጥራት ጉባዔ ( 3rd Quality Summit ) የመዝጊያ ሥነ ሥርዓትም ተካሂዷል :: ጉባዔው " ልህቀትን መቀበል፡ ለጥራት፣ ለአገልግሎት እና ለዕውቅና የተሰጠ ቁርጠኝነት” በሚል መሪ ቃል ላይ ትኩረት ያደረገ ነው: :
በእነዚህ በኮሌጁ በተከናወኑ ሁለትዓበይት ኩነቶች የእውቅና እና የምሥጋና መርሐ ግብር በአስተዋጽአቸው ጉልህ ተግባር ላከናወኑ ሠራተኞችና የሥራ ክፍሎች የምስክር ወረቀት እና ሽልማት ከኮሌጁ ፕሮቮስት ዶር ሲሳይ ስርጉ እጅ ተቀብለዋል::
በዚሁ መርሐ ግብር ላይ ንግግር ያደረጉት ዶር ሲሳይ ኮሌጁ ወደፊት ለማሕበረሰቡ የሚሠጠውን ነጻ የሕክምና አገልግሎት ብዙኃኑን ተደራሽ ያደርጋል ብለዋል:: በመቀጠልም የሕክምና አገልግሎት በጥራት እና በላቀ ሁኔታ ለመስጠት በሚቻልባቸው መንገዶች ሁሉ እንሠራለን ሲሉ ተናግረዋል : :

Kalkidan selected as a best Adult ICU Nurse of the Year!
Sr. Sr Kalkidan Zerihun, Professional nurse, was selected by the Department of Critical care medicine as a best Adult ICU Nurse of the Year 2016 (2023/24). She is nominated by nursing and others the department staff to honor her for exceptional service over the past year.

ለ National Graduate Admission Test (NGAT) አመልካቾች በሙሉ፦
የመግቢያ ፈተናዉ የሚሰጠዉ ነሀሴ 30 እና ጳጉሜ 01/2016 ዓ.ም ከጧቱ፡ 2፡30 ጀምሮ መሆኑ ይታወቃል፡፡
ስለሆነም ተፈታኞች ከፈተና ሰዓቱ ቀደም ብላችሁ በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ አካዳሚክ ግቢ በመገኘት የፈተና Username and Password መዉሰድ እና የመፈተኛ ክፍላችሁን ማወቅ ይጠበቅባችኋል፡፡
ማሳሰቢያ፡ ለፈተና ስትመጡ ማንነታችሁን የሚገልጽ መታወቂያ መያዝን አትርሱ፡፡
ነሐሴ 29/2016 ዓ.ም፤
በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ
ለወቅታዊ መረጃ ይቀላቀሉን፡
https://tttttt.me/SPMMC

Telegram
St.Paul's Hospital Millennium Medical College
St. Paul's is a leading public hospital and medical college in Addis Ababa, Ethiopia.
St_paul_ngat_Exam_schedule.pdf
638.1 KB
#SPHMMC
ቀን፡ 30/12/2016 ዓ.ም
ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ ለ ‘NGAT’ ፈተና ማዕከል አድርጋችሁ ለመረጣችሁ ተፈታኞች በሙሉ
NGAT የድኅረ ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና ለመውሰድ በኮሌጃችን ለተመደባችሁ ተፈታኞች በሙሉ ፈተናው በተያዘው ዕቅድ መሰረት ዛሬ ነሐሴ 30/2016 ዓ.ም ከ8:00 (ስምንት ሰዓት) ጀምሮ የሚሰጥ መሆኑን እያሳወቅን ሁሉም ተፈታኞች ከ7:00 ጀምሮ የመፈተኛ ክፍላችሁ እንድትገኙ እናሳውቃለን።
በማእከላችን የምትፈተኑ ተማሪዎች ስማችሁ ተያይዟል፡፡
መልካም ዕድል!
በፈተና ወቅት ማንነታችሁን የሚገልጽ መታወቂያ መያዝ አለባችሁ::
ለተጨማሪ መረጃ ይጎብኙን፡ https://tttttt.me/SPMMC
https://www.facebook.com/sphmmc

የድህረ ምረቃ መግቢያ ፈተና(GAT) ተፈታኞች
👉ተፈታኞች ሞባይል፣ ካልኩሌተር እና ሌሎች የኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን ይዘው ፈተና ክፍል ውስጥ መግባት አይችሉም፡፡
👉 ተፈታኞች ወደ መፈተኛ ክፍል ሲመጡ ማንነታቸውን የሚገልጽ መታወቂያ እና Pass Card ብቻ መያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
👉ተፈታኞች ፈተናው ከሚጀምርበት ሰዓት ከ30 ደቂቃ ቀድመው በተመደቡበት መፈተኛ ክፍል መገኘት ይኖርባቸዋል፡፡
👉ተፈታኞች ፤ ፈተናውን የሚያስፈትኑ መምህራን በሚያሳዩት ቦታ ብቻ መቀመጥ አለባቸው።
መልካም ፈተና!!!
መልካም ውጤት!!

እንኳን ለአዲሱ ዓመት 2017 በሰላም አደረሳችሁ !
መጪው ዘመን የሰላም፣ የስኬት እና የደስታ እንዲሆንልንዎ እንመኛለን ።
መልካም አዲስ ዓመት!
#የቅዱስጳውሎስሆስፒታልሚሊኒየምሕክምና_ኮሌጅ
#መልካምአዲስአመት

የብቃት ምዘና ፈተና ለምትወስዱ ጤና ባለሙያዎች በሙሉ
____
ጤና ሚኒስቴር ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በ Medicine, Nursing, Public Health, Pharmacy, Anesthesia, Medical Laboratory Science, Midwifery, Dental Medicine, Medical Radiology Technology, Environmental Health, Psychiatric Nursing, Pediatric & Child Health Nursing እና Surgical Nursing ሙያዎች በመጀመሪያ ዲግሪ ተመርቃችሁ የብቃት ምዘና ፈተናውን ለመውሰድ ምዝገባ ያጠናቀቃችሁ የጤና ባለሙያዎች በሙሉ፤ ፈተናው ከመስከረም 8 - 10/ 2017 ዓ.ም ድረስ የሚሰጥ መሆኑን እየገለፅን፦
1. የፈተናው መርሃ-ግብር
- 8/1/2017 ዓ.ም…… Medicine, Pharmacy, Anesthesia, Dental Medicine, Environmental Health, Psychiatric Nursing and Surgical Nursing
- 9/1/2017 ዓ.ም……… Medical Laboratory Science, Midwifery, Pediatric and Child Health Nursing, Medical Radiology Technology and Public Health
- 10/1/2017 ዓ.ም…………… Nursing
እያንዳንዱ ተፈታኝ ከሚፈተንበት ቀን አንድ ቀን ቀደም ብሎ ማለትም መስከረም 7/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ በ 3፡00 ሰዓት በመፈተኛ ጣቢያ በመገኘት ስለፈተናው አሰጣጥ ቅድመ ገለጻ (orientation) መከታተል፤ የቅድመ ፈተና መለማመጃ ጥያቄዎችን መስራትና፤ የመፈተኛ ክፍሉን መለየት ይኖርበታል::
2. በፈተናው ዕለት ማንነታችሁን የሚገልጽ መታወቂያ (የቀበሌ መታወቂያ፣ ፓስፖርት፣ መንጃ ፍቃድ ወይም ሌላ በግልጽ የሚታይ ህጋዊ መታወቂያ) ይዛችሁ መገኘት ይኖርባችኋል፡፡
3. ከላይ ከተጠቀሱት ነገሮች ውጪ ምንም አይነት የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያ (ስልክ፣ የእጅ ሰዓት፣ መነጽር (የተረጋገጠ የዕይታ ችግር ከሌለ በስተቀር)፣ ቦርሳ እና ሌሎች እቃዎች፣ ምንም አይነት ማጣቀሻዎች እንዲሁም ባዶ ወረቀቶች፣ ምግብ ወይም መጠጥ (የተረጋገጠ የጤና ችግር ከሌለ በስተቀር) ይዞ መግባት አይፈቀድም፡፡
4. በፈተናው ወቅት ተመዛኞች በሁለቱም ክፍለ ጊዜ (ጠዋት እና ከሰዓት በኋላ) አቴንዳንስ ላይ በአግባቡ መፈረማችሁን ማረጋገጥ ይኖርባችኋዋል፣
5. ማንኛውም ተመዛኝ ወደ ፈተና ጣቢያ ሲመጣ ሲስተሙ የሚሰጠውን QR code ያለው የፈተና መግቢያ /ስሊፕ/ print አድርጎ ካልያዘ ፈተናውን መውሰድ የማይችል መሆኑን በጥብቅ እናሳስባለን፡፡
▫ የመፈተኛ ጣቢያ ኦንላይን በመረጣችሁት መሰረት ስም ዝርዝራችሁን ከዚህ በታች ያለውን ማስፈንጠሪያ /Link/ በመጫን መመልከት ይኖርባችኋል፡፡ (https://drive.google.com/drive/folders/17QzuVtjm4Uh3yQhA-teNFt7PRDqBc0Ft?usp=sharing)
▫ ተመዛኞች ስማቸው ከተጠቀሰበት ተቋም ውጪ በፍጹም ፈተናውን መውሰድ የማትችሉ መሆኑን እናሳስባለን፡፡
ማሳሰቢያ፦
- ጎንደር ዩኒቨርሲቲ(ቴዎድሮስ ካምፓስ) የመፈተኛ ጣቢያ የመረጣችሁ ተመዛኞች ወደ ጎንደር ዩኒቨርሲቲ(ጤና ሳይንስ ኮሌጂ) የተዘዋወራችሁ መሆኑን እንገልጻለን፡፡