St.Paul's Hospital Millennium Medical College
19K subscribers
2.08K photos
24 videos
12 files
468 links
St. Paul's is a leading public hospital and medical college in Addis Ababa, Ethiopia.
Download Telegram
ዛሬ የነጻ ምርመራው የመጨረሻ ቀን ነው: : የዛሬው የፎቶ ምልከታ
የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም የሕክምና ኮሌጅ በጎፋ ዞን በደረሰ አደጋ ለተጎዱ ወገኖች ድጋፍ አደረገ፡፡

የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም የሕክምና ኮሌጅ በጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ በተከሰተ የመሬት መንሸራተት አደጋ ለተጎዱ ወገኖች ከ2 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ድጋፍ አደረገ።

የኮሌጁ አስተዳደርና ልማት ምክትል ፕሮቮስት ጀማል ሽፋ በጎፋ ዞን በመገኘት ተጎጂዎችን ለማቋቋም የሚደረገውን ጥረት ለማገዝ ግምታቸው ከሁለት ሚሊዮን ብር በላይ የሆኑ ልዩ ልዩ መድኃኒቶች ፡ የምግብ ነክ ቁሳቁስ እና አልባሳት ለዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ኢንጂነር ዳግማዊ አየለ አስረክበዋል፡፡
አቶ ጀማል ሽፋ እርዳታውን ባስረከቡበት ወቅት አንደ ተናገሩት እሳቸውና የኮሌጁ ማህበረሰብ በዚህ በተከሰተው የተፈጥሮ አደጋ እጅግ ልብ የሚሰብር መሆኑንን ገልፀዋል። ወደፊትም ተቋማቸው ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች ድጋፉን እንደሚቀጥልም አቶ ጀማል አስረድተዋል ፡፡
APPLICATION CALL FOR POST GRADUATE PROGRAMS
2024/2025 ACADEMIC YEAR
ST. PAUL'S HOSPITAL MILLENIUM MEDICAL COLLEGE
REGISTRAR OFFICE
Important Note
 All students will join the college after satisfactorily passing Graduate Admission Test (GAT) that will be administered by MoE (follow the announcement from MoE)
 Written and Oral exam will be given by the hosting department. The date will be notified on social media pages.
SCHOOL OF MEDICINE
1. Master of Science in respiratory therapy
2. Master of Science in Medical Microbiology
3. Masters of Science in Medical Radiologic Technology
 CT & MRI Pathway
 Ultrasonography Pathway
 Radiography, Fluoroscopy & Mamography Pathway
 Cath Lab Pathway
SCHOOL OF PUBLIC HEALTH
Modality: Regular and weekend
Programs
1. MPH in General Public Health
2. MPH in Nutrition
3. MPH in Epidemiology
4. MPH in Health communication and promotion
SCHOOL OF NURSING
Modality: Regular
Sponsor: Self/government sponsorship
Programs:
1. MSC in Critical Care Nursing (Residence Type)
2. MSC in Cardiovascular Nursing (Residence Type)
3. MSC in Neonatal Nursing ( Residence Type )
4. MSC in Clinical Oncology Nursing (Residence Type)
5. MSC in Paramedics Science
6. MSC in Cardiothoracic Nursing
General requirement
Registration fee 400 birr (CBE account 1000006577192)
Application date: August 1 to August 18, 2023

Registration Guide
 Click online application link: https://portal.sphmmc.edu.et/Web/Announcement
 Read the instruction carefully
 Click Apply now / Apply for admission
 Choose the program you want to apply and click “Apply”
 Insert basic information and summit. You will get the following message
“Application has been successfully submitted. Your application number is: 00005. Pay your application fee (400 Birr) using SPHMMC bank account number 1000006577192 (CBE) and upload the receipt file. Finally, you can upload your academic documents on this portal.”
You should record your application number. It is required to upload receipt and document
Click “upload receipt” which is located on the left side of the window and upload the receipt. You will get the following message:
“You have successfully uploaded your receipt. Now, you can upload your academic documents.”
Click “upload document” which is located on the left side of the window and upload the document and click Summit document.
የእናት ጡት ወተት
የእናት ጡት ወተት መተክያ የሌለው ንጹህ እና ተስማሚ የህጻናት ምግብ ነው፡፡እስካሁን በተጠኑት ጥናቶች መሰረት የእናት ጡት ወተት መተኪያ የሌለው ንፁህ እና ተስማሚ የህፃናት ምግብ ነው፡፡ስለዝህም ህፃናት ያለምንም ተጨማሪ ምግብ የመጀመሪያዎቹን 6 ወራት የእናት ጡት ወተት ብቻ ማግኘት አለባቸው፡፡
::
የእናት ጡት ወተት ማጥባት ለእናቶች ያለው ጥቅም
አንድ እናት ልጁዋን ጡት በምታጠባበት ወቅት የሚከተሉትን ጥቅሞች ታገኛለች
 ከወሊድ በኃላ የደም መፍሰስ እንዳይከሰት ይከላከላል፡፡
 ከወሊድ በኃላ ክብደትን ለመቀነስ ይረዳል::
 የጡት እና የእንቁላል ማምረቻ ካንሰርን ይከላከላል
 በእድሜ የሚመጡ በሽታዎችን ለምሳሌ ስኳር፣ ግፊት ፣የልብ ህመም እና የመሳሰሉትን በሽታዎችን ይከላከላል
 በእናት እና በልጅ መሃል ያለውን ፍቅር ይጨምራል
 ከወሊድ በኃላ የሚመጣውን ጭንቀት ይቀንሳል
 እናት ስታጠባ ከአዕምሮዋ የሚመነጨው (oxytocin)የሚባል ሆርሞን ደስተኛ እንድትሆን እና ተጨማሪ ወተት እንድታመርት ያደርጋል
 በተፈጥሮ ፀጋ የሚገኝ ስለሆነ ወጪ ቆጣቢ ነው ::
 ለአጭር ጊዜ ቢሆንም እርግዝናን ይከላከላል(እስከ 6 ወር ወይንም የወር አበባ እሰኪመጣ)
 ጊዜ ቆጣቢ እና ለ እናት ቀላል ነው


የእናት ጡት ወተት ለህጻናት ያለው ጥቅም

 ትክክለኛ እና በቂ የሆኑ ንጥረ ነገሮች በውስጡ ስለያዘ ህፃናት በተገቢው ሁኔታ እንዲያድጉ ና ብሩህ አይምሮ እንዲኖራቸው ይረዳል፡፡
 የተለያዩ ኢንፌክሽኖችን ይከላከላል
 ህፃናትን ከ ተቅማጥ እና ተያያዥ በሽታዎች ይከላለላል
 ልጆች ከመጠን ያለፈ ውፍረት እንዳይኖራቸዉ ይከላከላል
 የመጀመርያዉ አይነት የስኳር በሽታን ይከላከላል
 ድንገተኛ የሆነ የጨቅላ ህፃናትን ሞት ይከላከላል
የእናት ጡት ወተት ማጥባት ለቤተሰብ እና ለማህበረሰብ እና ለሀገር ያለው ጥቅም

 ወጪ ቆጣቢ እና በተፈጥሮ የተሰጠ ነው
 የተለያዩ የህፃናት በሽታ በመከላከል የሀገሪቱን የጤና ወጪ ይቀንሳል
 በአጠቃላይ የህፃናትን በሺታዎች በመቀነስ በሀገር ደረጃ የህፃናት ሞትን በእጅጉ ይቀንሳል
 ልጆች ባለ ብሩህ አይምሮ ሆነው እንዲያድጉ በመርዳት በትምህርትም ዉጤታማ እንዲሆኑ ከዛም እንደ ሀገር ጥሩ አበርክቶ እንዲኖራቸዉ ቀላል የማይባል አስተዋፆ አለው::
የሚያጠቡ እናቶች ማወቅ ያለባቸው ነገሮች
ህፃናት ገና በተወለዱ በ 1 ሰአት ዉስጥ ጡት መጥባት መጀመር አለባቸው ከዛ ጀምሮ በ24 ሰአት ዉስጥ ቢያንስ ቢያንስ 8-12 ጊዜ ጡት መጥባት አለባቸው፡፡ ሆኖም በተጨማሪም ሕፃኑ ለመጥባት በሚፈልግበት ጊዜ ሁሉ ማጥባት ተገቢ ነው::
ህፃናት ጡት ለመጥባት ሲፈልጉ የምያሳዩት ምልክቶች
 እጃቸው መጥባት
 በደንብ ነቅተው አፋቸውን ማንቀሳቀስ
 ምላሳቸውን ወጣ ወጣ ማድረግ
 መነጫነጭ
 ማልቀስ
ህጻኑን ለማጥባት እንዲህ አስተካክለው ይያዙ
⇒ አፉ በደንብ ተከፍቶ ጠቆር ያለዉን የጡትዎን ክፍል
አብዛኛዉን መጉረስ አለበት፡፡
⇒ የታችኛዉ ከንፈሩ ወደዉጭ ገልበጥ ማለቱን
⇒ አገጩ ጡትዎን መንካቱን
⇒ ጉንጮቹ ሞላ ማለታቸዉንና
⇒ በመሀል ትንሽ እያረፈ በደንብ መሳቡን ማረጋገጥ ያስፈልጋል፡
Think before you post anything online!

Inappropriate pictures and messages shared in a second can lead to a lifetime of regret.
የባዮ ሜዲካል ኢንጅነሮችና ቴክኖሎጅስቶች በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት የህክምና መሳሪያዎችን የጥገና አገልግሎት ዛሬ በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ ተጀመረ::

የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት አካል የሆነው የባዮ ሜዲካል ኢንጅነሮችና ቴክኖሎጅስቶች የህክምና መሳሪያዎች ጥገና ስራ ዛሬ በይፋ የጤና ሚኒስትርዋ ክብርት ዶር መቅደስ በተገኙበት ተጀምሯል::

የህክምና መሳሪያዎችን ጠግኖ ወደ አገልግሎት ማብቃት ከፍተኛ የገንዘብ ወጪን ከማዳን በተጨማሪ የዕውቀት ሽግግርና ልምድ የሚገኝበት እንደሆነ ክብርት ሚኒስትርዋ በመክፈቻ ሥነ ሥርዓቱ ላይ አስረድተዋል::

ለ23 ቀናት በሚቆየው የበጎ ፈቃድ አገልግሎት 17 አስመጭዎች 7 አምራቾችና 3 መንግስታዊ ድርጅቶች እንዲሁም 179 በጎ ፈቃደኞች ይሳተፋሉ ተብሎ ይጠበቃል::