የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ የአቢሲኒያ የኢንዱስትሪ ሽልማት የወርቅ ደረጃ ልዩ የዋንጫ ተሸላሚ ሆነ፡፡
የሽልማት ድርጅቱ ለኢትዮጵያዊያን በተሰጠ የ77 ዓመታት አገልግሎት እና በሀገር ደረጃ ዘመናዊ ሕክምናን በመጀመር ስኬታማ ተግባራትን ላከናወነው ተቋማችን አውቅና እና የዋንጫ ሽልማት አበርክቷል፡፡ በተጨማሪም በአመራርና በመካከለኛ ደረጃ ለሚገኙ እና ሌሎች ሰራተኞች ኒሻን እና ሜዳሊያ ሰጥቷል፡፡
የኮሌጁ የህክምና አገልግሎት ምክትል ፕሮቮስት ዶር ውለታው ጫኔ ከአቢሲኒያ የኢንዱስትሪ ሽልማት የበላይ ጠባቂ ከሆኑት ከቀድሞ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፕሬዚዳንት ዶ|ር ሙላቱ ተሾመ እጅ ሽልማቱን ተረክበዋል፡፡
ዶር ውለታው እንዳሉት ሽልማቱ ኮሌጁ በጤና አገልግሎትና እና በጤና ሳይንስ ትምህርት ዘርፍ ያደረገውን አበርክቶ የሚገልፅ ነው፡፡
እንዲህ አይነት ሀገራዊ ሽልማት ኮሌጁ በቀጣይየዘመነ የሕክምና አገልግሎት ለመስጠትና በየዘርፉ ብቁ ባለሙያዎችን ለማሰልጠን ለሚያደርገው የላቀ ተግባራትን ዳር ለማድረስ በእጅጉ ያበረታታዋል ብለዋል፡፡
ዶር ውለታው ለሁሉም የኮሌጁ የሥራ አመራሮች እና ሠራተኞች የእንኳን ደስ አለን መልእክት አስተላልፈዋል፡፡

የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም የሕክምና ኮሌጅ በጎፋ ዞን በደረሰ አደጋ ለተጎዱ ወገኖች ድጋፍ አደረገ፡፡
የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም የሕክምና ኮሌጅ በጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ በተከሰተ የመሬት መንሸራተት አደጋ ለተጎዱ ወገኖች ከ2 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ድጋፍ አደረገ።
የኮሌጁ አስተዳደርና ልማት ምክትል ፕሮቮስት ጀማል ሽፋ በጎፋ ዞን በመገኘት ተጎጂዎችን ለማቋቋም የሚደረገውን ጥረት ለማገዝ ግምታቸው ከሁለት ሚሊዮን ብር በላይ የሆኑ ልዩ ልዩ መድኃኒቶች ፡ የምግብ ነክ ቁሳቁስ እና አልባሳት ለዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ኢንጂነር ዳግማዊ አየለ አስረክበዋል፡፡
አቶ ጀማል ሽፋ እርዳታውን ባስረከቡበት ወቅት አንደ ተናገሩት እሳቸውና የኮሌጁ ማህበረሰብ በዚህ በተከሰተው የተፈጥሮ አደጋ እጅግ ልብ የሚሰብር መሆኑንን ገልፀዋል። ወደፊትም ተቋማቸው ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች ድጋፉን እንደሚቀጥልም አቶ ጀማል አስረድተዋል ፡፡