ለምን አልሰለምኩም?
2.97K subscribers
52 photos
10 videos
42 files
187 links
ይህ ቻነል ቅዱሱ የአምላካችን ቃል በ1ኛ ጴጥ 3:15 ላይ ባዘዘን መሠረት ሙስሊም ወገኖቻችን በክርስትና ላይ ለሚያነሷቸው ጥያቄዎች እና ትችቶች ምላሽ የምንሰጥበት፣ ጥያቄዎቻቸውን ከነመልሳቸው በየጊዜው እያዘጋጀን የምንለጥፍበት፣ ለምን እንዳልሰለምን ፣ እንደማንሰልምም የምንገልጥበት ፣ የኢስላምን የጨለማ መንገድነት በእውነት ብርሀን የሚገልጡ ፅሁፎችን የምናስነብብበት መድረክ ነው።
Download Telegram
"በጀነት ዝሙት እንዴት ሊኖር ቻለ?" ለሚለው ጥያቄ መነሻ ጀነት ውስጥ በሚገኘው ገበያ የጀነት ገቢ ሙስሊም ወንዶች የሚፈጽሙት ልቅ የወሲብ ተግባር ነው፡፡ ነቢዩ ሙሐመድ በገነት የገበያ ሥፍራ ስለመኖሩ ተናግረው በተለያዩ የሐዲስ ዘጋቢዎች ተዘግቧል፡-

ሱና ቲሪሚዚ ቅጽ 4፣ ቁ. 2549
….ከዛ ጌታችን አዘ ወ-ጀል እንዲህ ይላል፡- ተነሱ ስለክብራችሁ ወዳዘጋጀሁላችሁ፤ ያንን የምትፈልጉትንም ውሰዱ፡፡ ከዛም በመላእክት የተከበበ የገበያ ቦታ አገኙ፡፡…

የዚህ የገበያ ሥፍራ ተግባርና የተዘጋጀበት ዋና ዐላማ ምንድን ነው? የሚለውንም ነቢዩ መልሰውታል፡፡ ኢማም ገዛሊ ያንን እንዲህ አስቀምጠውታል፡-

"ጨምረውም እንዲህ አሉ፡- በገነት ገበያ ይኖራል፤ በዛ ምንም አይሸጥበትም አይገዛበትም፤ ነገር ግን ወንዶችና ሴቶች ይኖሩበታል፡፡ ማንኛውም ወንድ ከሴቶቹ ጋር የግብረ ሥጋ ግንኙነት ለማድረግ ከፈለገ በፍጥነት ያደርጋል፡፡…" (Ihya Ulum-Id-Din (Revival of religious learnings), translated by Fazl-ul-Karim, vol 4, page 430.)

ኢማም ቡኸሪም የዚህን ስፍራ አገልግሎት እንደሚከተለው የነቢዩን ንግግር በመውሰድ አስተላልፈዋል፡-

ሳሂህ አል-ቡኻሪ ቅጽ 4፣ 56 ፡ 468
ሳሂህ አል-ቡኻሪ ቅጽ 6፣ 60 ፡ 402
አብዱላህ ቢን ቃኢስ ሲናገር የአላህ መልእክተኛ እንዲህ አሉ፡- በገነት ከአንድ ወጥ ሉል የተሠራ ስፋቱ 60 ማይል የሆነ አዳራሽ አለ፡፡ ከአንዱ ጥግ ያለው በሌላው ጥግ ያለውን በማይመለከትበት በዚህ አዳራሽ ሚስቶች በየጥጉ አሉ፤ አማኞች ይጎበኟቸዋል በእነርሱ ይደሰቱባቸዋል፡፡…

ከዚህ እንደምንገነዘበው ቦታው የሚገዙበት የሚሸጡበት ሳይሆን የገነት ወንዶች ከመኖሪያቸው ወጥተው የሚሰባሰቡበትና ከተሰጧቸው 72 ሚስቶች ውጭ በገበያው አዳራሽ ከሚገኙት ጋር ወሲብ እንደፈለጉ የሚፈጽሙበት ቦታ ነው፡፡ የወሲብ ገበያ አዳራሽ ነው፡፡ በገበያው ያሉት ሴቶች ብቻ ሳይሆኑ ወንዶችም ጭምር እንደሆኑና ከእነርሱም ጋር ፍላጎትን መፈጸም እንደሚቻል የሚከተሉት የነቢዩ ሐዲሳት ያስገነዝባሉ፡-

"ጃብር ኢብን አብደላህ እንዲህ አለ፡- ሁላችን ተሰባስበን እያለን የአላህ መልእክተኛ ወጥተው ወደ እኛ መጡ፡፡ እንዲህም አሉ እናንተ ሙስሊሞች ሆይ በገነት ፎቶዎች ብቻ ያሉበት ምንም የማይሸጥበትና የማይገዛበት የገበያ ቦታ አለ፡፡ የወንድ ወይም የሴቶቹን ፎቶ ያፈቀረ ሰው ወደ ዛው ውስጥ ይገባል፡፡"(The book of the End, page 693)

ሱና ቲሪሚዚ ቅጽ 4፣ ቁ. 2550
ሁሉም እንዳወሩት የአላህ መልእክተኛ እንዲህ አሉ፡- በእርግጥ በገነት የወንዶችና የሴቶች ፎቶ መለጠፊያ እንጅ ማንም የማይሸጥበትና የማይገዛበት ገበያ አለ፡፡ አንድ ሰው ፎቶውን ከወደደው ወደዛው ይገባል፡፡

ጎብኝው የገነት ገቢ ሙስሊም ወንድ የወደደው የወንዱን ፎቶ ቢሆንስ? ሙስሊም ሊቃውንት ለዚህ ሐዲስ የሰጡት ማብራሪያ ምን እንደሚል እስኪ ላስነብባችሁ፡-

ሐዲሱ የሚለን በገነት ምንም የማይሸጥበትና የማይገዛበት የተለየ ዓይነት ገበያ አለ፡፡ በማሳያ ላይ ስፍር ቁጥር የሌላቸው የቆንጆ ወንዶች እና የቆነጃጅት ሴቶች ፎቶ ይኖረዋል፡፡ ወንዶቹ የትኛውንም ፎቶ ለራሳቸው ይመርጡና ይወስዳሉ፤ ሚስቶቻቸውም ወደ መረጡት ፎቶ ይለወጡላቸዋል ማለት ነው፡፡

የተመረጠው የወንድ ፎቶ ቢሆን ሁርዬዋ ወደ ተመረጠው ወንድ ፎቶ ትለወጥለትና የወደደውን ያደርጋል ማለት ነው? ወደ ዛው ይገባል ተባለ እንጂ ወደ ሚስቱ ተመልሶ ትለወጥለታለች አይልም፡፡ ሐዲሱ ምን ዐይነት መልእክ ቢያስተላልፍ ነው እንዲህ ዐይነት የማይገኛኝ ትርጉም የተሰጠው? የሚቀጥለው ግልጽ ያደርገዋልና ተከተሉኝ፡፡ ኢማም ኢብን ከሲር ቀደም ብዬ በጠቀስኩት መጽሀፋቸው የገበያውን ቦታ በተመለከተ የሚለተለውን አስፍረው እናገኛለን፤ ለላይኛው ሐዲስ ማጠናከሪያ ይሆነናል፡-

"በአት-ቲርሚዚ ውስጥ የሚገኝ ሐዲስ አሊ እንዳወራው የአላህ መልእክተኛ እንዲህ አሉ፡- በእውነት በገነት የገበያ ቦታ አለ፤ በዛ ግዥም ሽያጭም አይካሄድም፡፡ በምትኩ የሴቶችና የወንዶች ፎቶ ይገኛል፤ እናም የትኛውም ወንድ ፎቶውን ከወደደው ወደ ፎቶው ባለቤት ይገባል፡፡ (ቲሪሚዚ) ….በምንም ደረጃ ይህ እንዲህ እንደ ማለት ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል ወንዶች መግባት የሚፈልጉት ፎቶው የወንድ ወደ ሆነው ብቻ ነው፤ በተመሳሳይ ሴቶች መግባት የሚፈልጉት ፎቶው የሴት ወደ ሆነ ብቻ ነው፡፡ ስለዚህ ይህ ሐዲስ ከዚህ በፊት ያለው ሐዲስ ማብራሪያ ይሆናል፡፡" (The book of the End, page 693)
ታዲያ በዚህ ላይ እንዲህ የሚሉ ጥያቄዎች ማንሳት ተገቢ አይመስላችሁም፡-

 ፎቷቸው የተለጠፈላቸው ወንዶችና ሴቶች እነማን ናቸው? ከየትስ መጡ? መራጮቹስ ለምን ወንዶቹ ብቻ ሆኑ? ሴቶቹ የተባሉት የትኞቹ ሴቶች ናቸው? የምድር ሴት ምእነናን ማለት ነው? የገበያው ማዕከል የወሲብ ገበያ እንደመሆኑ መጠን ተመሳሳይ ጾታ ያለቸው በወሲብ እዛም ይፈላለጋሉ ማለት ነው?

 የወንድና የሴት ፎቶዎች የሚለጠፉበት ገበያ ከሆነ ወንድ ሁርየዎችም ይፈጠራሉ ማለት ነው?


 መለወጥ የሚለውን አመለካከት እንውሰድ ቢባል ወደ ገበያ የወጣው ሙስሊም የተሳበው በወንዱ ፎቶ ቢሆን ምንድን ነው የሚሆነው? ሁርዬ ወደ ወንድ ተለውጣለት ከወንዱ ጋር ግብረ ሰዶም ይፈጽማል? ወይስ ወደ ወንዱ መልክ ተለውጣለት ወንዱን እያሰበ ወሲብ ይፈጽማል ማለት ነው?

ይህንን ያክል ከከፈትኩላችሁ በሐዲሶቹ ላይ ተመስርታችሁ እናንተው ጥያቄዎችን ጨማምሩበት፡፡ በዚህ መካከል "ሐዲሱ ደኢፍ ነው" የምትል የተለመደች ማስተባበያ ከዘለፋና ከስድብ ጋር መነሳቷ አይቀርም፡፡ ለዚህ ያለኝ ምላሽ አንደኛው የጠቀስኩዋቸው ሐዲሶች የታመኑ የኢስላም ሊቃውንት ያሚያምኑባቸውንና በመጽሐፎቻቸው የከተቧቸውንና ሙስሊሙ በአላህ ዘንድ የተዘጋጁላቸውን ተስፋዎች እንዲያውቁ ያደረጉባቸውን ሐዲሶች እንደሆነ ሊታወቅ ይገባል፡፡ በሁለተኛ ደረጃ እንኳን የሐዲስ ይቅርና የቁርአን ሰሂህ የለም፡፡ ለትክክለኛነቱ አስረጅ ሊቀርብለት የሚችል አንድም ኢስላማዊ ሰነድ አለመኖሩ ሊታወቅ ይገባል፡፡ ማስረጃ አለን የሚል ካለ በዚህም ላይ መነጋገር የሚቻል መሆኑን ላሳስብ እወዳለሁ፡፡

ስጠቀልለው በኢስላም ጀነት ያለው ዝሙት ሳይሆን ከሱ የከፋው ግብረ ሰዶማዊነት ነው፡፡ ይህ ነው "በጀነት ዝሙት እንዴት ሊኖር ቻለ?" ለሚለው ጥያቄ መነሻ የሆነው፡፡ የአምላካችን የእግዚአብሔር ቃል እንደሚነግረን ይህ ክፉ ተግባር እንኳን በገነት ሊኖር ይቅርና በምድር ይለማመዱ የነበሩ ትውልዶች ከሰማይ በዘነበ እሳት ዝክራቸው ከምደር ተደምስሷል፡፡ ስለዚህ ተስፋው ጉም ነው፤ የለም፡፡

የኢስላም ጀነት "ላም አለኝ በሰማይ ወተቷንም አላይ"!

የተጨበጠ አስተማማኝ የዘላለም ሕይወትን መንገድ ትፈልጋለህ? ትፈልጊያለሽ?

የዮሐንስ ወንጌል 14 ፡ 6
ኢየሱስም፦ እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ፤ በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም።

በዚህ መንገድ ለሚጓዙና ሕይወቱን ለተቀበሉ እርግጠኛ እንዲሆኑ እንዲህ የሚል ተጽፎላቸዋል፡-
የኢስላም_ጀነት_ላም_አለኝ_በሰማይ_ወተቷንም_አላይ.pdf
420.2 KB
እውን በጀነት ዝሙት አለን? ለሚለው የኡስታዝ አቡ ይደርና የየሕያ ኢብኑ ኑሕ ዲስኩር ተከፋፍሎ ተሰጥቶ የነበረውን ምላሽ ጠቅለል አድርጌ እነሆኝ ብያለሁ
👍2
ሰላም ሰላም ውድ ጓደኞቼ እንዴት አላችሁልኝ? እኔ በጣም ሰላም ነኝ! እስካሁን እኔ ይጠቅማችኋል ያልኩትን ሳካፍላችሁ ቆይቻለሁ፡፡ አሁን እስኪ ለእናንተ እድል ልስጣችሁና ኢስላምን በተመለከተ ስለምን ማወቅ ትፈልጋላችሁ? ይኸኛው ጥያቄ ሆኖብኛል የምትሉትን፣ ግራ ያጋባችሁን አምጡት እኔ የማውቀውን እኔው ከእኔ እልፍ ያለውን ደግሞ መጽሐፍትን አማክሬ እመልስላችኋለሁ፡፡ ስለዚህ በመልእክት ማስቀመጫው በኩል ላኩት ይደርሰኛል፡፡ እወዳችኋለሁ! የጌታችንና የመድኀኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ሰላምና ፀጋ ይብዛላችሁ ይጠብቃችሁ!!!!
👍4
Forwarded from Good news
የነቢዩ ሙሐመድ ምስክሮች.pdf
1.3 MB
ውድ ክርስቲያን ሙስሊም ጓደኞቼ እንዴት አላችሁልኝ? ሰላማችሁን የሰላሙ ልዑል እንዲያበዛላችሁ እመኛለሁ! ቀደም ብዬ ባቀረብኩት ሐሳብ መሠረት የተወሰኑ ወንድሞች ጥያቄዎቻቸውን ልከውልኛል፡፡ አመሰግናለሁ! በቅርብ መልሶቻቸውን ለዚህ በሚመጥን መልኩ ይዤ ብቅ እላለሁ፡፡ እስከዛው ግን አንዲት በጌታ እርዳታ የጻፍኳት ጥሩ መጽሐፍ አለችኝ፡፡ ከታተመች ትንሽ ቆየት ብላለች፡፡ ከዚህ የተነሳ አሁን ማሻሻያ እያደረግኩባት ነው፡፡ በቅርብ ቀናት ውስጥ እጨርሳለሁ ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ የተሸሻለውን እንዴት ማግኘት እንደምትችሉ ወደ ፊት የምንነጋገርበት ቢሆንም እስከዛው እባካችሁ የሚታረምና የሚስተካከል ያላት ቢሆንም የመጀመሪያዋን ጽሑፍ ተቃመሱልኝ ብያለሁ!!
👍43
መንፈስ ቅዱስ ሁሉን አዋቂ መለኮት ነው!
ለሙስሊም ሰባኪያን ስሁት ሙግት የተሰጠ ምላሽ

http://www.ewnetlehulu.org/am/holy-spirit-omniscient/
Channel photo updated
እውን የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ እና የቁርአኑ ኢሣ አንድ ናቸውን?

በምን ሐሳብ ላይ እንድንወያይ ይፈልጋሉ ብዬ መጠየቄን ታስታውሳላችሁ፡፡ ታዲያ አንድ ወዳጄ "እውን የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ እና የቁርአኑ ኢሣ አንድ ናቸውን?" በማለት ምላሽ እንድሰጥበት ያቀበለኝ ጥያቄ ነው፡፡ ታዲያ ይህንን ጥያቄ በሁለት መንገድ ምላሽ እንዲሰጥበት ቁርአን ይጋብዛል፡፡ የመጀመሪያው ከራሱ ከቁርአን ተልእኮ አንጻር የሚታይ ሲሆን ሁለተኛው ቁርአን ሁለቱን አንድ አድርጎ የሚተርክበት አውድ ስላለ በዛው መነጽር የሚታይ ነው፡፡

1. "እውን የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ እና የቁርአኑ ኢሣ አንድ ናቸውን?" በቁርአን ተልእኮ መነጽር

ቁርአን ጥርት ያለ ተልእኮ ባይኖረውም ተልእኮ ተብለው ከተዘረዘሩት መካከል አንዱ፡-

ሱረቱል ዩኑስ 10 ፡ 37
ይህም ቁርኣን ከአላህ ሌላ (ከሆነ ፍጡር) የተቀጠፈ ሊሆን አይገባውም፡፡ ግን ያንን ከእርሱ በፊት ያለውን (መጽሐፍ) የሚያረጋግጥና በመጽሐፉ ውስጥ ያለውን የሚዘረዝር በእርሱ ጥርጣሬ የሌለበት ሲሆን ከዓለማት ጌታ (የተወረደ) ነው፡፡

وَمَا كَانَ هَٰذَا الْقُرْآنُ أَن يُفْتَرَىٰ مِن دُونِ اللَّهِ وَلَٰكِن تَصْدِيقَ الَّذِي بَيْنَ يَدَيْهِ وَتَفْصِيلَ الْكِتَابِ لَا رَيْبَ فِيهِ مِن رَّبِّ الْعَالَمِينَ [١٠:٣٧]

ሱረቱል አሊ-ዒምራን 3 ፡ 3
ከርሱ በፊት ያሉትን መጻሕፍት የሚያረጋግጥ ሲኾን መጽሐፉን (ቁርኣንን) ባንተ ላይ ከፋፍሎ በእውነት አወረደ፡፡ ተውራትንና ኢንጂልንም አውርዷል፡፡

نَزَّلَ عَلَيْكَ الْكِتَابَ بِالْحَقِّ مُصَدِّقًا لِّمَا بَيْنَ يَدَيْهِ وَأَنزَلَ التَّوْرَاةَ وَالْإِنجِيلَ [٣:٣]

مُصَدِّقًا (ሙሰዲቀን) ሌላውን በንግግሩ ወይም በያዘው መረጃ ማመን መቀበል፣ ለእውነትነቱ ምስክርም መሆን ማለት ነው፡፡ (An Arabic-English Lexicon by Edward William Lane ገጽ 1667)

ታዲያ እንዴት ነው የሚያረጋግጠውና የሚመሰክረው? በምንድን ነው ማመኑንና መቀበሉን የሚያሳየው? ስንል አንዱ ተመሳሳይ መልእክቶችን በመያዝና በአንዱ አምላካዊ ጎዳና በማጠብጠብ ነው፡፡ እንዲህ ስለሆነ ነው ቁርአን እንዲህ የሚለውን አንቀጽ በውስጡ ሊያቅፍ የቻለው፡-

ሱረቱል አል-ኒሳዕ 4 ፡ 26
አላህ (የሃይማኖታችሁን ሕግጋት) ሊያብራራላችሁ ከእናንተ በፊትም የነበሩትን ነቢያት ደንቦች ሊመራችሁ በእናንተም ላይ ጸጸትን ሊቀበል ይሻል፡፡ አላህም ዐዋቂ ጥበበኛ ነው፡፡

ሱረቱል አል-አንአም 6 ፡ 89-92 እንዲሁም ሌላኛው መርህ ሆኖ ሊያገለግለን ይችላል፡፡ ሱራ 5 ፡ 15 ተጨማሪን ፍንጭ ይዟል፡፡ እንዲህ ከሆነ የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስና የቁርአኑ ኢሣ አንድ ናቸው ማለት ካለብን በሁለቱም መጽሐፍት ውስጥ በተመሳሳይ መግለጫዎች እና መልእክቶች ተወክለው ልናገኛቸው ይገባል፡፡ ይህንን ፍለጋ በዚህ ሚዛን ላይ ስናወጣቸው የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ እና የቁርአኑ ኢሣ አንድ አለመሆናቸውን እንመለከታለን፡፡

የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ፡-

ከስሙ እንጀምር፤ የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ ስሙ ስም ብቻ ሳይሆን ተልእኮውን ገላጭም ነበር፡፡ ኢየሱስ ማለት እግዚአብሔር ያድናል፣ ይረዳል ማለት ነው፡፡ መልአኩ ገብርኤልም ለዮሴፍ "በሕልም የሕፃኑን ስም ኢየሱስ ትለዋለህ" ሲለው ትርጉሙንና አገልግሎቱን እንዲህ በማለት ነበር የገለጸው፡-

ማቴ 1 ፡ 21
ልጅም ትወልዳለች፤ እርሱ ሕዝቡን ከኃጢአታቸው ያድናቸዋልና ስሙን ኢየሱስ ትለዋለህ።

ይህ ክፍል የብዙ ቀደምት ነቢያት ትንቢታዊ መልእክት ድጋፍ ያለው መሆኑን ሳላሳስብ አላልፍም፡፡ ወንጌላዊው ዮሐንስም ይህንኑ በሚያደምቅ መልኩ የተልእኮውን ዓላማ እንዲህ ሲል አስፍሮታል፡-

ዮሐ 3 ፡ 16-17
በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና። ዓለም በልጁ እንዲድን ነው እንጂ፥ በዓለም እንዲፈርድ እግዚአብሔር ወደ ዓለም አልላከውምና።

የቁርአኑ ኢሣ ግን እንዲህ አይደለም፡፡ የመጀመሪያው የቁርአንን አውደ ጥበብ ያዘጋጁ ሊቃውንት ኢሣ የመጽሐፍ ቅዱሱን ኢየሱስ የስም ትርጓሜ እንደ ሌለው ሲናገሩ፡- "Īsā, the qurānic form of his name, has no such connotations" (Encyclopedia of Quran, vol 3 page 11) ብለዋል፡፡ ኢሣ ማለት ምን ማለት ነው ለሚለው ይኸው የቁርአን አውደ ጥበብ የነቢዩ ሙሐመድን ቃል ዋቢ በማድረግ የመልኩን ቀለም የሚገልጽ ሆኖ "ነጣ ያለ ቀይ" (a reddish whiteness) ማለት እንደሆነ ይናገራል፡፡ ይህም ስለ አንድ አካል እየተናገረ ያለ ላለመሆኑ ጉልህ ማሳያ ነው፡፡

የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ ማንነቱ፡-

የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ ማንነት ከሙሴ የጀመረ እስከ አብረውት እስከ ወጡ እስከ ገቡ ሐዋርያት ድረስ፣ መላእክትንም ጨምሮ ተርከውለታል፡፡ ሰዎች እየሰሙ አብ ከሰማይ ተናግሮለታል፡፡ ለተገለጠውና የለመሰከረለት ማንነቱም ሰዎች ሕይወታቸውን እስከሞት ድረስ አሳልፈው ሰጥተዋል፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ ሰው ብቻ ሳይሆን ፍጹምም አምላክ ነው፡፡ ለዚህ ለቁጥር የሚያታክቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችን ማቅረብ ይቻላል፤ ይሁንና ለአብነት የሚሆኑ ከተለመዱትና ከምታውቋቸው የተወሰኑትን ላስነብባችሁ፡-

ትንቢተ ኢሳይያስ 9 ፡ 6
ሕፃን ተወልዶልናልና፥ ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና፤ አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል፤ ስሙም ድንቅ መካር፥ ኃያል አምላክ፥ የዘላለም አባት፥ የሰላም አለቃ ተብሎ ይጠራል።

ሐዋርያው ዮሐንስም በወንጌሉ እንዲሁም በመልእክቶቹ አምላክነቱን አብስሯል፡-

ዮሐ 1 ፡ 1-3
በመጀመሪያው ቃል ነበረ፥ ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ፥ ቃልም እግዚአብሔር ነበረ። ይህ በመጀመሪያው በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ። ሁሉ በእርሱ ሆነ፥ ከሆነውም አንዳች ስንኳ ያለ እርሱ አልሆነም።

1ኛ ዮሐ 5 ፡ 20
… እርሱም ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። እርሱ እውነተኛ አምላክና የዘላለም ሕይወት ነው።

ሌላው ጌታ ኢየሱስ ክርሰቶስ የእግዚአብሔር ልጅ ነው፡፡ ለዚህም ከእግዚአብሔር ቃል አስረጅዎቼን እነሆኝ፡፡ መለአኩ ገብርኤል ከተናገረው ልጀምር፡-

ሉቃ 1 ፡ 35
መልአኩም መልሶ እንዲህ አላት፦ መንፈስ ቅዱስ በአንቺ ላይ ይመጣል፥ የልዑልም ኃይል ይጸልልሻል ስለዚህ ደግሞ ከአንቺ የሚወለደው ቅዱስ የእግዚአብሔር ልጅ ይባላል።

ቅዱስ እግዚአብሔር አምላክም ስለ ልጁ በተደጋጋሚ ሰው በጀሮው እየሰማ ልጄ ብሎ መስክሮለታል፡-

ሉቃ 3 ፡ 22
መንፈስ ቅዱስም በአካል መልክ እንደ ርግብ በእርሱ ላይ ወረደ፤ የምወድህ ልጄ አንተ ነህ፥ በአንተ ደስ ይለኛል የሚል ድምፅም ከሰማይ መጣ።

ለመስቀል ሞት ያበቃው ይኸው የእግዚአብሔር ልጅነቱ አልነበረምን?

ማቴ 26 ፡ 63-66
ኢየሱስ ግን ዝም አለ፦ ሊቀ ካህናቱም፦ አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ክርስቶስ የሆንህ እንደ ሆነ እንድትነግረን በሕያው እግዚአብሔር አምልሃለሁ አለው። ኢየሱስም፦ አንተ አልህ ነገር ግን እላችኋለሁ፥ ከእንግዲህ ወዲህ የሰው ልጅ በኃይል ቀኝ ሲቀመጥ በሰማይም ደመና ሲመጣ ታያላችሁ አለው። በዚያን ጊዜ ሊቀ ካህናቱ ልብሱን ቀዶ፦ ተሳድቦአል እንግዲህ ወዲህ ምስክሮች ስለ ምን ያስፈልገናል? እነሆ፥ ስድቡን አሁን ሰምታችኋል፤ ምን ይመስላችኋል? አለ። እርሱም፦ ሞት ይገባዋል ብለው መለሱ።
1👍1
ነቢዩ ሙሐመድና አላህ ይህንን ታሪክ መለኮታዊ መገለጥ ይበሉት እንጂ ከላይ በአንቀጹ እንደ ተመለከተው በዙሪያቸው ከነበሩ ክርስቲያን ተብለው ከሚጠሩ ሰዎች በጀሮ ጠገብ የሰሙት የዛ ዘመን ተረት ነው፡፡ የዚህ ታሪክ ምንጭ አሁንም የአዲስ ኪዳን አዋልድ መጽሐፍ ነው፡፡ ታሪኩ በ "ቶማስ ወንጌል (The Gospel of Tomas)" የኢየሱስ የልጅነት ታሪክ ተብሎ ተጽፎ የሚገኝ ነው፡፡ በነቢዩ ዘመን የነበሩ የመካ ክርስቲያኖች ያወሩት የነበር ታሪክ ነው፡፡ ከዚህ የምንረዳው በፊትም እንደገለጽኩት ቁርአን መለኮታዊ መገለጥ ሳይሆን ጀሮ ሰምቶ ከሞላው እየተቀዳ የተጻፈ የተረቶች ስብስብ ነው፡፡

ስለዚህ የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ እና የቁርአኑ ኢሣ አንድ ሊሆኑ አይችሉም፡፡ ኢሣ ተረት ሲሆች ኢየሱስ ክርስቶስ ግን ሕያው ነው፡፡ ነቢዩ ሙሐመድና ቁርአን ከእውነተኛው አምላክ የተላኩ የመዳን መንገዶች አይደሉም የምንልበት አንዱ ምክንያት ይህ ነው፡፡ በሌሎቹ ጥያቄዎች ተመልሸ እመጣለሁ፡፡

ሳሂህ ኢማን ነኝ፤ ሰላም!!!!
ቁርአን ኢሣ የሚባለው አካል ግን ፍጡር ነው፡፡

ሱራ 4 ፡ 171
… የመርየም ልጅ አልመሲሕ ዒሳ የአላህ መልክተኛ ወደ መርየም የጣላት «የኹን» ቃሉም ከእርሱ የኾነ መንፈስም ብቻ ነው፡፡ …

ሱረቱል አሊ-ዒምራን 3 ፡ 59
አላህ ዘንድ የዒሳ ምሳሌ እንደ አዳም ብጤ ነው፡፡ ከዐፈር ፈጠረው፡፡ ከዚያም ለርሱ (ሰው) «ኹን» አለው፤ ኾነም፡፡

ሱረቱል አሊ-ዒምራን 3 ፡ 47
ጌታዬ ሆይ! ሰው ያልነካኝ ስኾን ለኔ እንዴት ልጅ ይኖረኛል᐀ አለች፡፡ ነገሩ እንዳልሽው ነው፡፡ አላህ የሚሻውን ይፈጥራል፡፡ አንዳችን በሻ ጊዜ ለርሱ ኹን ይለዋል፤ ወዲውኑም ይኾናል አላት፡፡

ሱረቱል አል-በቀራ 2 ፡ 117
ሰማያትንና ምድርን ያለብጤ ፈጣሪ ነው፤ ነገርንም (ማስገኘት) በሻ ጊዜ ለርሱ የሚለው፡- «ኹን ነው፤» ወዲያውም ይኾናል፡፡

ጌታ ኢየሱስ ስቅለቱና ሞቱ፡-

የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ ክርስቶስ እንደ ስሙ ሰዎችን ከኃጢአታቸው ለማዳን እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ በመስቀል ላይ ተሰቅሎ ቤዛ መሆኑና መሞቱ በብዙ ምስክሮች የተጣበበ እውነት ነው፡፡ አይሁዶች፣ አይሁድም ክርስቲያንም ያልሆኑ ወገኖች፣ ክርስቲያኖች፣ ወንጌላውያን፣ ሐዋርያት፣ ወዘተ… ለዚህ እማኝ ናቸው፡፡

ማር 15 ፡ 22-37
ትርጓሜውም የራስ ቅል ስፍራ ወደሚሆን ጎልጎታ ወደተባለ ስፍራ ወሰዱት። ከርቤም የተቀላቀለበትን የወይን ጠጅ እንዲጠጣ ሰጡት፤ እርሱ ግን አልተቀበለም። ሰቀሉትም፥ ልብሱንም ማን ማን እንዲወስድ ዕጣ ተጣጥለው ተካፈሉ። በሰቀሉትም ጊዜ ሦስት ሰዓት ነበረ። … ኢየሱስም በታላቅ ድምፅ ጮኸ ነፍሱንም ሰጠ።

ሞቶ ብቻ አልቀረም፡፡ በሦስተውም ቀን ሞትን ድል ነስቶ ተነስቷል፡፡ ይህም በምስክሮች የተጣበበ እውነት ነው፡-

ማቴ 28 ፡ 2-6
እነሆም፥ የጌታ መልአክ ከሰማይ ስለ ወረደ ታላቅ የምድር መናወጥ ሆነ፤ ቀርቦም ድንጋዩን አንከባሎ በላዩ ተቀመጠ። መልኩም እንደ መብረቅ ልብሱም እንደ በረዶ ነጭ ነበረ። ጠባቆቹም እርሱን ከመፍራት የተነሣ ተናወጡ እንደ ሞቱም ሆኑ። መልአኩም መልሶ ሴቶቹን አላቸው። እናንተስ አትፍሩ የተሰቀለውን ኢየሱስን እንድትሹ አውቃለሁና፤ እንደ ተናገረ ተነሥቶአልና በዚህ የለም፤ የተኛበትን ስፍራ ኑና እዩ።

የቁርአኑ ኢሣ ግን አልሞተም አልተሰቀለም፡፡ ሰዎችን ከኃጢአታቸው ለማዳን የሠራው ምንም ዐይነት የቤዛነት ሥራ የለም፡፡

ሱረቱል አል ኒሳዕ 4 ፡ 157
«እኛ የአላህን መልክተኛ የመርየምን ልጅ አልመሲሕ ዒሳን ገደልን» በማለታቸውም (ረገምናቸው)፡፡ አልገደሉትም አልሰቀሉትምም፡፡ ግን ለእነሱ (የተገደለው ሰው በዒሳ) ተመሰለ፡፡ …

ሱረቱል አሊ-ዒምራን 3 ፡ 55
አላህም ባለ ጊዜ (አስታውስ)፡፡ ዒሳ ሆይ! እኔ ወሳጂህ ወደ እኔም አንሺህ ነኝ፡፡ ከነዚያም ከካዱት ሰዎች አጥሪህ ነኝ እነዚያንም የተከተሉህን እስከ ትንሣኤ ቀን ድረስ ከነዚያ ከካዱት በላይ አድራጊ ነኝ፡፡ ከዚያም መመለሻችሁ ወደእኔ ነው፡፡ በርሱ ትለያዩበትም በነበራችሁት ነገር በመካከላችሁ እፈርዳለሁ፡፡

ስለዚህ በዚህ ሚዛን እና መነጽር የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ ክርስቶስ እና የቁርአኑ ኢሣ አንድ አይደሉም ወደሚል መደምደሚያ ያደርሰናል፡፡ ምንም የሚያመሳስላቸውና የጋራ ውክልና የሌላቸው የተለያዩ አካላት ናቸው፡፡ ይህ ደግሞ ቁርአን መለኮታዊ መጽሐፍ ነቢዩም ሙሐመድም የእውነተኛው አምላክ መልእክተኛ አለመሆናቸውን አጋልጧል፡፡

2. "እውን የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ እና የቁርአኑ ኢሣ አንድ ናቸውን?" አንድ ናቸው በሚለው የቁርአን መነጽር

በዚህኛው መነጽር ቁርአን የመጽሐፍ ቅዱሱን ኢየሱስ እና የቁርአኑን ኢሣ አንድ ለማስመሰል ብዙ ጥሯል፡፡ አልተሳካም እንጂ፡፡ ከጽንሰቱ ጀምሮ ያለውን ታሪክ እግር በእግር እየተከታተለ ለማስመሰል ትርክቶችን አንድ ሁለት ብሎ ተይቧል፡፡ እነዚህም ቢሆኑ ቁርአንን ከማጥ አያወጡትም፤ ቁርአን ውስጥ ስለ ኢሣ የተጻፉት ታሪኮች ሁሉም መለኮታዊ መገለጦች ሳይሆኑ ከተለያዩ የእምነት ተቋማት መጽሐፍት በጀሮ ጠገብ ተለቅመው በራስ አባባል ተቀነባብረው የተሰደሩ ታሪኮች ናቸው፡፡ የትኛው ከየትኛው የሃይማኖት መጽሐፍ እንደተወሰደ መዘርዘር በጣም ቀላል ሥራ ነው፡፡ ይሁንና ከጌታ ኢየሱስ ታሪክ ጋር ከተዘረዘሩ ታሪኮች የተወሰነውን ብቻ ለናሙና አስነብባችኋለሁ፡-

የማርያምና የጽንሰት ታሪክ፡-

ሱረቱል አሊ-ዒምራን ውስጥ የጽንሰትና የአስተዳደግ ትርክት ሰፍሯል፡፡ ይህ ከሌላ የተኮረጀ ስለመሆኑ የመጀመሪያውን ፍንጭ የሚሰጠው "የኢምራን ቤተሰብ" የሚለው የቁርአን ምዕራፍ ነው፡፡ እንደ ቁርአን ኢምራን የኢየሱስ እናት የማርያም አባት እንደሆነ ተገልጿል፡፡ (ሱራ 3 ፡ 33-37) ኢምራን ተብሎ የተጠራው የነ ሙሴ አባት አምራም ነው፡፡ ነቢዩ የትኛዋን ማርያም እየጠቃቀሱ እንዳሉ አሁን ግልጽ ነው፡፡ የአምራም ልጅ የሆነችውንና የነ ሙሴ እህት የሆነችውን ማርያም ነው፡፡ ለዚህም ነው በሱረቱል መርየም 19 ፡ 28 ነቢዩ በአላህ ስም እንዲህ ያሉት፡-

"የሃሩን እኅት ሆይ! አባትሽ መጥፎ ሰው አልነበረም፡፡ እናትሽም አመንዝራ አልነበረችም» አሏት፡፡"

ነቢዩ ሙሐመድና አላህ ከ 1500 ዓመታት በላይ ልዩነት ባለው ዘመን ያሉ የሁለት ሰዎችን ታሪክ በዚህ መልኩ ቀላቅለው ያዋቀሩት እንዴት ነው?

ነቢዩ ታሪኮቹን ያወቁት በጀሮ ጠገብ ነበር፡፡ በጊዜው ስለ ማርያምና ስለ ተወለደው መሲህ የራሳቸው ትርክት የነበራቸው ሁለት ሃይማኖቶች ነበሩ፡፡ እናም ከሁለቱ ሃይማኖት ተከታዮች አንድ የሚመስል ግን የተለያየ ይዘት ያለውን ትርክትን ሰምተዋል፡፡ ከዛም እርሳቸው ይህንን ሁለት ግን አንድ የሚመስል ትርክት በመቀላቀል መለኮታዊ ራዕይ እንደ ወረደላቸው አድርገው ለተከታዮቻቸው አበሰሩት፡፡ ነቢዩ ትርክቱን የሰሙት የአዲስ ኪዳን አዋልድ መጽሐፍትን ይጠቀሙ ከነበሩ ክርስቲያን ነን ከሚሉ ወገኖችና የሳቢያን ሃይማኖት ተከታዮች ከነበሩ ሰዎች ነበር፡፡ ይህን ታሪክ ዛሬም በሃይማኖቶቹ መጽሐፍት ውስጥ ሰፍሮ ታገኙታላችሁ፡፡ የአዲስ ኪዳኑ አዋልዱ "የማርያም የልደት ወንጌል (The Gospel of the birth of Mary)" እና የሳቢያኖቹ ደግሞ "የሃራን-ገወኢታ (Haran-Gawaita)" ይሰኛል፡፡ ይህም ቁርአን የተረታ ተረቶች ስብስብ እንጂ መለኮታዊ መገለጥ ያለመሆኑ አንዱ ማሳያ ነው፡፡

ከኢሣ ታሪክ አንድ ልጨምርላችሁ፡፡ ሱረቱል አሊ-ዒምራን 3 ፡ 49፡-

"ወደ እስራኤልም ልጆች መልክተኛ ያደርገዋል፡፡ (ይላልም)፡- «እኔ ከጌታዬ ዘንድ በተዓምር ወደ እናንተ መጣሁ፡፡ እኔ ለናንተ ከጭቃ እንደ ወፍ ቅርፅ እፈጥራለሁ፡፡ በርሱም እተነፍስበታለሁ፡፡ በአላህም ፈቃድ ወፍ ይኾናል፡፡"

ነቢዩ ይህንን ታሪክ ከየት ነው ያመጡት?

ሱረቱል አል-ነሕል 16 ፡ 103
እነርሱም «እርሱን (ቁርኣንን) የሚያስተምረው ሰው ብቻ ነው» ማለታቸውን በእርግጥ እናውቃለን፡፡ የዚያ ወደርሱ የሚያስጠጉበት ሰው ቋንቋ ዐጀም ነው፡፡ ይህ (ቁርአን) ግን ግልጽ ዐረብኛ ቋንቋ ነው፡፡
👍41
ዒሳ ወፍ ፈጥሯልን?

በቴሌግራም ሰፈር ስዘዋወር "ኢሳ ወፍ ፈጥሯልን?" በሚል ርእስ የተጻፈች መጣጥፍ አየሁ፡፡ የጽሑፉ ዓላማ ኢሳን እንደ ኢየሱስ የሚቆጥሩና የእርሱን አምላክነት በቁርአን ለማረጋገጥ የሚዳዳቸው ወገኖች ለሚያነሱት ሙግት ምላሽ ለመስጠት ታስቦ ይመስላል፡፡

ሱረቱል አሊ-ኢምራን 3 ፥49
ወደ እስራኤልም ልጆች መልክተኛ ያደርገዋል፡፡ (ይላልም)፡- «እኔ ከጌታዬ ዘንድ በተዓምር ወደ እናንተ መጣሁ፡፡ እኔ ለናንተ ከጭቃ እንደ ወፍ ቅርፅ እፈጥራለሁ፡፡ በርሱም እተነፍስበታለሁ፡፡ በአላህም ፈቃድ ወፍ ይኾናል፡፡ በአላህም ፈቃድ ዕውር ኾኖ የተወለደን፣ ለምጸኛንም አድናለሁ፡፡ ሙታንንም አስነሳለሁ፡፡ የምትበሉትንና በቤታችሁ የምታደልቡትንም ሁሉ እነግራችኋለሁ፡፡ የምታምኑ እንደኾናችሁ ለእናንተ በዚህ ውስጥ በእርግጥ ተዓምር አለበት፡፡»

ጸሐፊው ቃላትን በመሰነጣጠቅ ኢሳ እንዳልፈጠረና ከጭቃ በተሠራችው የወፍ ቅርጽ ላይ እፍ ሲልባት አላህ ወፍ እንድትሆን እንዳደረገለት ማሳየትና የሞጋቾቹን ሙግት ስሁት ለማድረግ ተጣጥሯል፡፡ የፈጣሪውን ባለቤትነት ለአላህ ሰጥቷል፡፡ በኢሳና በሙሳ የተሠሩ ተአምራቶችን ለንጽጽር ተጠቅሟል፡፡ ሙግቱ ለሌላ ሙግት ጋባዥና የጠራ ባይሆንም እርሱን ይቆይ፡፡ በተጠቀሰው የቁርአን ታሪክ ላይ ያለው ጥያቄ እንደተባለው ፈጥሯል አልፈጠረም የሚለው ሳይሆን መለኮታዊ መገለጥነቱ ላይ ነው፡፡ መለኮታዊ መገለጥ መሆኑ ላይ የሚነሳውን ጥያቄ ፈች ጽሑፍ ሆኖ ግን አላገኘሁትም፡፡

በአጭሩ ቁርአን መለኮታዊ መገለጥ አይደለም፡፡ ለዚህ የምዕራፍ ስያሜ መለኮታዊ መገለጥ አለመሆኑን ገላጩ ብርሃን ወገግ በማድረግ እዚህ ነኝ ማለት ይጀምራል፡፡ በሁለተኛ ደረጃ 49 ኛው አንቀጽ እንደ ቀትር ፀሐይ ነገሩን ያደምቀዋል፡፡ ነቢዩ ሙሐመድ ኢሳን በተመለከተ ተገለጠልኝ ያሉትንና ያስተላለፉትን አንዱንም በመለኮታዊ መገለጥ አለመቀበላቸው በዚህ ይጋለጣል፡፡ በእርሳቸው ዘመን የነበሩ ሞጋቾቻቸው ይሉት እንደ ነበር በጀሯቼው ይነበብላቸው ከነበረው የወሰዱትን ነው ተገለጠልኝ ብለው በተለያየ ምክንያት ይከተላቸው ለነበረው ሕዝብ ያስተጋቡ የነበረው፡፡ ቁርአን ጀሯቼው ሞልቶ ሲፈስ የተከተበ ነው ማለት ነው፡፡

ሱረቱል አል-ፉርቃን 25 ፡ 4-5
እነዚያም የካዱት ይህ (ቁርኣን ሙሐመድ) የቀጠፈው በእርሱም ላይ ሌሎች ሕዝቦች ያገዙት የኾነ ውሸት እንጂ ሌላ አይደለም አሉ፡፡ በእርግጥም በደልንና እብለትን ሠሩ፡፡ አሉም «የመጀመሪያዎቹ ሰዎች ተረቶች ናት፡፡ አስጻፋት፡፡ እርሷም በእርሱ ላይ ጧትና ማታ ትነበብለታለች፡፡»

እንዲህ ከሆነ ከየትኛው መጽሐፍ ላይ እንደ ተነበበላቼውና እነማን እንዳነበቡላቸው ማስረጃህን አምጣው ትሉኝ ይሆናል፡፡ አዎን መካ ውስጥና መዲና በነቢዩ ሙሐመድ ዙሪያና እርሳቸው ጋር ይገናኙ የነበሩ ክርስቲያን የሚባሉ ሰዎች እንደ ነበሩ ቁርአን ይተርካል፡፡ ለዚህ የዚህኛውን የቁርአን አንቀጽ ተፍሲሮች መመርመር ያቻላል፡-

ሱረቱል አን-ነህል 16 ፡ 103
እነርሱም «እርሱን (ቁርኣንን) የሚያስተምረው ሰው ብቻ ነው» ማለታቸውን በእርግጥ እናውቃለን፡፡ የዚያ ወደርሱ የሚያስጠጉበት ሰው ቋንቋ ዐጀም ነው፡፡ ይህ (ቁርአን) ግን ግልጽ ዐረብኛ ቋንቋ ነው፡፡

ከየትኛው መጽሐፍ ለሚለው ደግሞ የሚከተለውን የአዲስ ኪዳን አዋልድ መጽሐፍ የሆነውን የቶማስ ወንጌልን ድርሳን ላስነብባችሁ፡-

Gospel of Infancy Thomas 2 : 4-7
'But when a Jew saw what Jesus was doing while playing on the sabbath day, he immediately went off and told Joseph, Jesus' father: "See here, your boy is at the ford and "has taken mud and fashioned twelve birds with it," and so has violated the sabbath." So, Joseph went there, and as soon as he spotted him, he shouted, "Why are you doing what's not permitted on the sabbath?" "'But Jesus simply clapped his hands and shouted to the sparrows: "Be off, flyaway, and remember me, you who are now alive!" And the sparrows took off and flew away noisily." 'The Jews watched with amazement, then left the scene to report to their leaders what they had seen Jesus doing.

ታዲያ የትኛው ነው መለኮታዊ መገለጡ? ነቢዩ ሙሐመድ ከጠገበው ጀሯቼው የተናገሩት እንጂ ከመለኮታዊ መገለጥ የተቀበሉት አይደለም፡፡ እና ውድ ሙስሊም እህቶችና ወንድሞች ምን እንዳመናችሁ፣ ምን ላይ እንደቆማችሁ፣ ወዴት እየሔዳችሁ እንዳላችሁ አሁን ቆም ብላችሁ የምታስቡበት ሰዓት አይመስላችሁም? አምላኬ የውስጥ ዐይናችሁን ይክፈተው!
👍10😁2
ሱና ነውና!
ከሰሞኑ በፈረንሳይ የሆነውን መቼም ሁላችን ያየነው ነው። እንዲያው ብዙም ሳንል(ለግዜው ማለቴ ነው) አንድን ሐዲስ ላስነብባችሁና ይህንን መሐመድ ላይ እንዲህና እንዲያ አላችሁ ብሎ በስለት ዘንጥሎ መጣልን እንዴትና ከየት እንደተማሩት ላስታውሳችሁ(ህልቆ መሳፋርት መረጃ ማምጣት ቢቻልም ለግዜው ይበቃል)። በዛውም መሐመድ አበጀህ ማለታቸውን ሳንዘነጋው። ነገሩንም ቅቡል ያደርገዋል ሱና ነውና!

"አብደላ ኢብን አባስ እንደዘገቡት
አንድ አይነስውር የነበረ ሰው ነብዮን የምታንቋሽሽና ስለእርሳቸው መጥፎ ነገርን የምትናገር እናት-ባርያ ነበረችው። እርሱም ይህንን እንዳታደርግ ከለከላት እርሷ ግን አላቆመችም። ነቀፋት ግን እርሷ ይህን ልምዷን አልተወችም። አንድ ምሽት ነብዮን ልትተችና ልታንቋሽሻቸው ጀመረች። እናም እርሱ ጬቤ አፈፋ አድርጎ ከሆድቃዋ ቀበቀበው አጥልቆም ተጫነው፤ ሞተችም። በእግሮቿ መሃል የገባም ልጅ ከርሷ በወጣም ደም ተጥለቀለቀ። ሲነጋም ነብይ ስለሁኔታው ተነገራቸው.......
እርሱም በነብዮ ፊት ተቀመጠ እንዲህም አለ: የአላህ መልእክተኛ ሆይ! እኔ አሳዳሪዋ ነኝ፤ እርሷም እርሶን ታንቋሽሽና ትተች ነበረ። ከለከልኳት አላቆመችም፤ ነቀፋኳትም፤ ነገር ግን ይህንን ልማዷን አላቆመችም። ከርሷም እንቁ የመሰሉ ሁለት ልጆችን አፍርቻለሁ አጋሬም ነበረች። ትላንት ምሽት ክፉ ልትናገርዎና ልታንቋሽሽዎ ጀመረች። እናም እኔ ጬቤ አፈፋ አድርጌ ከሆድቃዋ ቀበቀብኩት አጥልቄም እስክገላት ተጫንኩት፤
ይሄኔ ነብዮ:- 'ምስክር ሁኑ ምንም አይነት የደም ካሳ አይከፈልም።' አሉ።"

ሱና አቡ ዳውድ 4361

"Narrated Abdullah Ibn Abbas:

'A blind man had a slave-mother who used to abuse the Prophet (ﷺ) and disparage him. He forbade her but she did not stop. He rebuked her but she did not give up her habit. One night she began to slander the Prophet (ﷺ) and abuse him. So he took a dagger, placed it on her belly, pressed it, and killed her. A child who came between her legs was smeared with the blood that was there. When the morning came, the Prophet (ﷺ) was informed about it........

He sat before the Prophet (ﷺ) and said: Messenger of Allah! I am her master; she used to abuse you and disparage you. I forbade her, but she did not stop, and I rebuked her, but she did not abandon her habit. I have two sons like pearls from her, and she was my companion. Last night she began to abuse and disparage you. So I took a dagger, put it on her belly and pressed it till I killed her.

Thereupon the Prophet (ﷺ) said: Oh be witness, no retaliation is payable for her blood."

Sunan Abi Dawud 4361
In-book : Book 40, Hadith 11
English translation : Book 39, Hadith 4348
Abu Dawood

ተመከቱ እንግዲህ አንድን "የልጆቹን እናት" የሆነችን ባርያውን፣ አንድን "ነብይ" ተናገርሽ ብሎ በአሰቃቂ ሁኔታ መግደል፤ ገዳይንም አበጀህ ማለት ውሉ ምን ይሆን?
እና እስልምና ምንድር ነበር ያልከው ጃል?

@Jesuscrucified
👍42😱1
ፍቅር እንደዚህ ነው፤

“ፍቅርም እንደዚህ ነው፤ እግዚአብሔር እርሱ ራሱ እንደ ወደደን ስለ ኃጢአታችንም ማስተስሪያ ይሆን ዘንድ ልጁን እንደ ላከ እንጂ እኛ እግዚአብሔርን እንደ ወደድነው አይደለም።” — 1ኛ ዮሐንስ 4፥10

ሐዋርያው አንድን ነገር ተረድቷል፤ አምላክ ሲሆን ሳለ ይህን እንደመቀማት ሳይቆጥር የአባቱን ፈቃድ ራሱን በመስጠት እንደ ባርያ ተገኝቶ ከወነ። ይህም እኔ ባልወደድሁት ጊዜ፣ እነሆ ነገሬን ከነገሩ ላርቅ በምሻ ወቅት፣ የቁጣ ልጅ ሳለሁ እኔ እድን ዘንድ የእርሱም ወንድም የአባቱም ልጅ እባል ዘንድ፤ በዘመኑ ፍፃሜ ከርሱ ጋር እርሱን እያየው፤ በታላቅነቱ እንደልቀቱ፤ በክብሩ እንደ ክብረቱ፤ በምስጋናው እንደ አምልኮቱ በህልውናው እኖር ዘንድ ነው። ዛሬ ለኔ የተዋረደው ጌታዬ አምላክ ሲሆን ስጋ የሆነው ፍቅሩን፤ ያተገባኝን ለኔ ያለውን ፍቅር ይገልጥልኝ በዛም እውነት አርነት እወጣ ዘንድ ነው።
ከዚህ በላይ ሚወደኝ ፣ ሚወድሽ፣ ሚወድክ ማን አለ?

ለኃጥኡ እሚሞት በእውነት ይገኝ ይሆንን?

ፍቅር እንደዚህ ነው! እርሱ ቃል ሰው ሆኖልሀል!

አምላክ ሲሆን ሳለ ፍቅር ግድ ቢለው እርሱ እየሱስ ለመስቀል ሞት እንኳ የታዘዘ ሆነ!

ይህ ፍቅር ከገባህ ቀን አይለፍህ ሰአታትም፥ እየሱስ ይወድሀል። እየሱስ ይወድሻል።

ከኃጥያት አበሳ ነፃ የሚያወጣህን ጌታ እመን ፍቅሩንም ተቀበል።
እነሆ ጊዜው አሁን ነው።

ፍ ቅ ር እንደዚህ ነው።

“This is love: not that we loved God, but that he loved us and sent his Son as an atoning sacrifice for our sins.”
— 1Jn 4፥10

@Jesuscrucified
7
ለምን አልሰለምኩም? pinned «ፍቅር እንደዚህ ነው፤ “ፍቅርም እንደዚህ ነው፤ እግዚአብሔር እርሱ ራሱ እንደ ወደደን ስለ ኃጢአታችንም ማስተስሪያ ይሆን ዘንድ ልጁን እንደ ላከ እንጂ እኛ እግዚአብሔርን እንደ ወደድነው አይደለም።” — 1ኛ ዮሐንስ 4፥10 ሐዋርያው አንድን ነገር ተረድቷል፤ አምላክ ሲሆን ሳለ ይህን እንደመቀማት ሳይቆጥር የአባቱን ፈቃድ ራሱን በመስጠት እንደ ባርያ ተገኝቶ ከወነ። ይህም እኔ ባልወደድሁት ጊዜ፣ እነሆ…»
ሙስሊም ወገኖቻችን ብዙ ጊዜ ክርስቶስ ያስተማረው በአረማይክ ቋንቋ ስለነበረ የአረማይክ ወንጌል አምጡ ይሉናል፡፡ ለዚህ ምክንያታቸው ቁርአን መልእክተኞች ሁሉ በገዛ ቋንቋቸው እንጂ በሌሎች ቋንቋዎች አልተላኩም በማለት ስለሚናገር ነው፡-

“ከመልክተኛ ማንኛውንም፤ ለነርሱ ያብራራላቸው ዘንድ በወገኖቹ ቋንቋ እንጂ በሌላ አልላክንም፤ አላህም የሚሻውን ያጠማል፤ የሚሻውንም ያቀናል፤ እርሱም አሸናፊው ጥበበኛው ነው።” (ሱረቱ ኢብራሂም 14፡4)

ነገር ግን ቁርአን ለዒሳ “ኢንጂል” የተባለ መጽሐፍ እንደተሰጠው ይናገራል፡-

“በፈለጎቻቸውም (በነቢያቶቹ ፈለግ) ላይ የመርየምን ልጅ ዒሳን ከተውራት በስተፊቱ ያለውን አረጋጋጭ ሲሆን፣ አስከተልን፤ ኢንጂልንም በውስጡ ቀጥታና ብርሃን ያለበት በስተፊቱ ያለችውን ተውራትንም የሚያረጋግጥ ለጥንቁቆችም መሪና ገሣጭ ሲሆን ሰጠነው።” (ሱረቱ አል-ማኢዳህ 5፡46)

“ኢንጂል” የሚለው ቃል Εὐαγγέλιον “ኤዋንጌሊዮን” ከሚለው የግሪክ ቃል የተወሰደ መሆኑን ሊቃውንት ይስማማሉ፡፡ ስለዚህ መልእክተኞች ሁሉ በገዛ ሕዝባቸው ቋንቋ ብቻ ተልከው ከነበሩ ለዒሳ ተሰጠ የተባለው መጽሐፍ ቋንቋው ግሪክኛ ሊሆን እንዴት ቻለ? የቁርአን ደራሲ መልእክተኞች በገዛ ቋንቋቸው ብቻ እንደተላኩ ተናግሮ ካበቃ በኋላ በግሪክ ቋንቋ የተጻፈ መጽሐፍ ለዒሳ እንደተሰጠው መናገሩ የአይሁድን ቋንቋ ባለማወቁ መሆኑ ግልፅ ነው፡፡ እንዲህ ያለ የተምታታ ጽሑፍ በዘላለማዊነት በፈጣረ ዘንድ እንደነበረ ማመን መታወር ነው!
👍42🔥1
የሱራ 9፡31 ሁለት መሠረታዊ ችግሮች

“ከርሱ በቀር ሌላ አምላክ የሌለዉን አንድን አምላክ ሊገዙ እንጂ ያልታዘዙ ሲሆኑ ሊቃውንቶቻቸውንና መነኮሳታቸዉን የመርየምን ልጅ አልመሲሕንም ከአላህ ሌላ አማልክት አድርገው ያዙ፤ ከሚያጋሩት ሁሉ የጠራ ነው።” (ሱረቱ አል-ተውባህ 9፡31)

የመጀመርያው የዚህ ጥቅስ ችግር እስላማዊ አስተምህሮን በመጻረር ኢየሱስ አምላክ መሆኑን መናገሩ ነው፡፡ የአማርኛና ብዙ የእንግሊዝኛ ትርጉሞች ከላይ በሚገኘው መንገድ “የመርየም ልጅ አልመሲሕ” የሚለውን “ሊቃውንቶቻቸውንና መነኮሳታቸዉን” ከሚለው ጋር በመደመር ቢተረጉሙትም የአረብኛው ጽሑፍ “አልመሲሕ” የሚለውን ከአላህ በኋላ በማምጣት “ወ” (እና) በሚል መስተጻምር ያያይዛቸዋል፡-

اتَّخَذُوا أَحْبَارَهُمْ وَرُهْبَانَهُمْ أَرْبَابًا مِنْ دُونِ اللَّهِ وَالْمَسِيحَ ابْنَ مَرْيَمَ
“አትተኸዙ አሕባረሁም ወ ሩህባነሁም አርባባን ሚን ዱኒ አላሂ ወ አል-መሲሐ ኢብነ መርየም …”

ቀጥተኛው ትርጉም “ከአላህና ከአልመሲሕ የመርየም ልጅ ሌላ ሊቃውንቶቻቸውንና መነኮሳታቸዉን ጌቶች አድርገው ያዙ…” የሚል ነው፡፡ ለዋናው የአረብኛ ንባብ ሃቀኛ መሆን የፈለጉ አንዳንድ የእንግሊዝኛ ትርጉሞች በዚህ ጉዳይ የተፈተኑ ይመስላሉ፡፡ በዚህም ምክንያት በአረብኛው ጥቅስ ውስጥ የማይታይ የኮማ ስርዓተ ነጥብ በመጠቀም ለማስተካከል ሞክረዋል፡-

They have taken their doctors of law and their monks for lords besides Allah, AND (also) the Messiah son of Marium… (Shakir)

They take their doctors and their monks for lords rather than God, AND the Messiah the son of Mary… (Palmer)

They take their priests and their monks for [their] lords, besides God, AND Christ the son of Mary… (Sale)

ይህ የቁርአን ጥቅስ ክርስቲያኖች ከአላህ እና ከመሲሑ ውጪ ሌሎችን ማምለክ የማይገባቸው ሆነው ሳሉ ሊቃውንቶቻቸውንና መነኮሳታቸዉን ያመልካሉ በማለት ወቀሳ ያቀርባል፤ ስለዚህ በጥቅሱ መሠረት ኢየሱስ አምልኮ የተገባው አምላክ ነው፡፡

ሙስሊም ሰባኪያን ይህንን እውነታ ለማስተባበል “መሲሐ” የሚለው حَ በፈትሃ ስለተጻፈ የዓረፍተ ነገሩ ባለቤት ሳይሆን ተሳቢ በመሆኑ ከሊቃውንትና መነኮሳት ጋር መቆጠር አለበት ይላሉ፡፡ ነገር ግን ይህ አጻጻፍ በቀዳሚያን ማኑስክሪፕቶች ውስጥ ያልነበረ ሲሆን ከጊዜ በኋላ የተጨመረ ነው፡፡ ጥንታዊው የአረብኛ አጻጻፍ አናባቢ ነቁጦች (diacritical marks) ስላልነበረው ከጊዜ በኋላ የተጨመረ ምልክት በመጠቀም መሞገት አሳማኝ አይደለም፡፡ የቁርአን ደራሲ ይህንን ችግር ለማስወገድ ቢፈልግ ኖሮ በቀዳሚያን ማኑስክሪፕቶች መሠረት ክርስቶስ አምላክ መሆኑን በሚያረጋግጥ መንገድ ሐሳቡን ከመግለፅ ይልቅ አላህና መሲሑን ነጣጥሎ “አልመሲሕ” የሚለውን ቃል “ሊቃውንቶቻቸውንና መነኮሳታቸዉን..” ከሚለው በፊት ወይም በኋላ ማስቀመጥ ይችል ነበር፤ ነገር ግን አላደረገውም፡፡

ሁለተኛው የዚህ ጥቅስ ችግር ክርስቲያኖች የሃይማኖት አባቶቻቸውን እንደሚያመልኩ በሐሰት መክሰሱ ነው፡፡ በሙሐመድ ዘመን የነበሩ ሰዎች ይህንን ችግር በመረዳት “ክርስቲያኖች ሊቃውንትና መነኮሳትን አያመልኩም እኮ” በማለት ሙሐመድን ለማረም እንደሞከሩ እስላማዊ ምንጮች ይናገራሉ፡፡ የሙሐመድ ምላሽ የነበረው “አይሁድና ክርስቲያኖች ረበናትና መነኮሳት የተፈቀደውን ሲከለክሏቸው ወይም የተከለከለውን ሲፈቅዱላቸው ይታዘዟቸዋል፤ ይህ አምልኮ ነው” የሚል ነበር፡፡ (Tafsir Ibn Kathir (Abridged), 2000, Volume 4, pp. 409-410)

የተፈቀደውን የሚከለክልና የተከለከለውን የሚፈቅድን ሰው መታዘዝ አምልኮ ከተባለ በቁርአን መሠረት ዒሳ የተከለከለውን የመፍቀድ ሥልጣን እንዳለውና የእርሱን ትዕዛዛት መከተል አስፈላጊ መሆኑ ስለተነገረ በተዘዋዋሪ ቁርአን ኢየሱስን ማምለክ ትክክል መሆኑን ያረጋግጣል ማለት ነው!

“ከተዉራትም ከኔ በፊት ያልለዉን ያረጋገጥሁ ስሆን የዚያንም በናንተ ላይ እርም የተደረገዉን ከፊል ለናንተ #እፈቅድ_ዘንድ፥ (መጣኋችሁ) ከጌታችሁም በሆነ ታምር መጣሁዋችሁ አላህንም ፍሩ፤ #ታዘዙኝም።” (ሱረቱ አሊ-ዒምራን 3:50)

እንደ እስልምና አስተምህሮ ሁሉ ነገር የተምታታበት አስተምህሮ በምድር ላይ ይገኝ ይሆን?
5👍4
አዲስ ጽሑፍ ያንብቡ
ተመሳሳዮቹ ወንጌላት ተጻራሪ ወይስ ተሰባጣሪ?
http://www.ewnetlehulu.org/am/synoptic-gospels/
2
እግረ መንገዴን ቴሌግራም ገብቼ የሰዎችን ውይይት እየሰማሁ፣ አንድ የሙስሊሞች ግሩፕ ውስጥ አንዱ ክርስቲያን ልጅ ስለ እዮብ 33:4 ጠቅሶ መንፈስ ቅዱስ ፈጣሪ መሆኑን እንደሚያሳይ ይነግረዋል። ክፍሉ እንዲህ ይላል:
"4፤ የእግዚአብሔር መንፈስ ፈጠረኝ፥ ሁሉንም የሚችል የአምላክ እስትንፋስ ሕይወት ሰጠኝ።"

ከዛ፣ ሙስሊሙ ልጅ፣ የግሪክ ሰፕቱያጅንቱ እንደዛ አያሳይም። የአረፍተ ነገሩ ባለቤት "እግዚያብሄር" ነው የሚለው። ስለዚህ የእግዚያብሔር መንፈስ ነው እንጂ መንፈሱ እግዚያብሔር አይደለም ይለዋል። probably ልጁ ከኡዝታዞቹ የሰማውን ነው እንጂ ቋንቋውን አያውቅም። ለማንኛውም ክፍሉን እንመልከት።

Job 33:4
[4]πνεῦμα θεῖον τὸ ποιῆσάν με πνοὴ δὲ παντοκράτορος ἡ διδάσκουσά με

ክፍሉን ከግሪኩ በቀጥታ ሲተረጎም "Divine spirit made me መሎኮታዊው መንፈስ ሰራኝ πνεῦμα θεῖον τὸ ποιῆσάν με" ይሆናል። ምክኒያቱም

1. θεῖον የሚለው ቃል "እግዚያብሄር" አይደለም። መሃል ላይ ያለችው iota "ῖ" ትርጉሙን ትለውጠዋለች። ትርጉሙም "መለኮት" ወይም ደግሞ "አማልክት gods" ማለት ነው። ከአውዱ የምንረዳው ግን ብዛትን ሳይሆን ስለ አንዱ መለኮት ስለሆን ትርጉሙ መለኮት ይሆናል ማለት ነው።

2. θεῖον ግዑዝ ፆታ ነው። እግዚያብሔር ግን θεος ሲሆን፣ ግራማቲካሊ ማስኩሊን ፆታ ነው። የመለኮት masculine gender ደግሞ θεῖος ነው። እዚህ ክፍል ላይ ግን አጨራረሱ ተቀይሮ θεῖον የሆነው፣ መንፈስ፣ የሚለው የግሪክ ቃል πνεῦμα በተፈጥሮ grammatically neuter ወይም ግዑዝ ስለሆነ ነው። ስለዚህ፣ "መለኮት" የሚለው ቃል በግሪክ ሰዋሰዋዊ ህግ የዓረፍተ ነገሩን ባለ ቤት ሲገልፅ በ case, gender, number መመሳሰል ስላለበት ወደ ግዑዝ ተቀይሯል። ይህ ማለት #መንፈስ የአረፍተ ነገሩ ባለ ቤት እንጂ ገላጭ አለመሆኑን ያሳያል። ስለዚህ የሙስሊሞቹ ሙግት ውድቅ ነው ማለት ነው። የአማርኛ መፅሐፍ ቅዱሳችንም የትርጉም ጉድለት እንዳለበት ማወቁ አይከፋም።

መልካም ቀን!!

@Jesuscrucified
👍6