ግጥም ሲጥም - Gitem Sitem
1.84K subscribers
842 photos
55 videos
20 files
394 links
የዘመናችንን ቀለም ያሳያሉ ያልናቸውን የዚህ ትውልድ የስነ ግጥም ውጤቶችን እንጋራ - እናጋራ።
ለማካፈል የፈለጋችሁትን በGitem_Sitem ፣ gitemsitem@gmail.com የጸሃፊ ስም እና ርዕስ አክላችሁ ላኩልን።

We are all about sharing this generation's poetry. Please email us your pieces gitemsitem@gmail.com
Download Telegram
ያ ዕድሜ ላይ

ሰው በተሰበሰበበት
ወይን ጭስ ጨዋታ
ዳንስ ሴት እስክስታ
ዳንኪራ ሁካታ ቡንቧታ
ግርግር ጫጫታ ነገር
ማኪያቶ የቆንጆ ሴት ከንፈር ሲቀራርብ
ተፈለኩ ብዬ
ሰው ጠራኝ ብዬ
ራሴን ገፍትሬ
ራሴን ቀጥሬ
ወደ ቤቴ ምበር
ጫማዬን ከበሬ የ ምወረውር
ከአልጋዬ ትራሴ ስር
ቀዝቃዛ ሙዚቃ ነገር
ከፍቼ ከራሴ ሃሳብ የምቀበር ።
(ያ ዕድሜ ላይ ። )
____
ሰው ሁሉ ጓጉቶ
መንገድ ጉዞ ተዘጋጅቶ
ስንቅ ተዘጋጅቶ
ጠጅ ተይዞ
ቆሎ ተይዞ
ባጋጣሚ ምክነያት
ባለቀ ሰዓት
ጉዞ ተሰርዟል !! ሲባል
ፈገግ የሚያስብለኝ

(ያ ዕድሜ ላይ )
....
ብዙ የፈረሱ ህልሞች _ ከአመድ የገቡ
ከምስጥ ጉድጓድ የጠበቡ
ሰው እየቀነስኩ
ሰው እየቀነሰኝ
አነስኩ ስል ገዝፌ የምገኝ ____( ያ ዕድሜ ላይ )

_
ሴት ቀጥሬ
ከወንበሬ ስትደርስ _ ተነስቼ ስሜ
ከወጠራት ልብስ _ዳሌ
ይልቅ ህልሟ የሚስበኝ
(ያ ዕድሜ ላይ )

ትርጉም በሌላት ዓለም _ ትርጉም የምፈልግ
የክብ ጉዞ የምስብ
ጠፍቼ _ስለመገኘት_ የማስብ
(ያ ዕድሜ ላይ )
_
የሲሲፈስን ርግማን _ኑሮዬ አርጌ የተቀበልኩ
ለራሴው እርድ _ ቢላ ስዬ ያቀረብኩ
በሞቱት የምቀና መኖር የሚያስፈራኝ
_
(ያ ዕድሜ ላይ )
_
ብናኝ መሆኔ የገባኝ
አዋራ መሆኔ የገባኝ
'አውራ ነኝ' የምል
__
ከመሞት ይልቅ
መኖር የሚያስፈራኝ
ሰው ያረገው የሚያስጠላኝ
ራሴው ያደረኩት የሚያስጠላኝ
በትልቁ ተጋድሜ
ትንሹ ነገር የሚያስፈራኝ
_
(ያ ዕድሜ ላይ )
_
የራሴን ህይወት ማሳመር ባልችል
ለማበላሸት የማላንስ
(ካደረኩት ይልቅ
የማደርገው የሚያጓጓኝ
የማያጓጓኝ
ይቅር እንዴ ?
ላርገው እንዴ ?
ልሂድ እንዴ ?
ልምጣ እንዴ ?
ላግባ እንዴ ?
ልውለድ እንዴ ?
ልሙት እንዴ ?
የሚያስብለኝ የማያስብለኝ
(ያ ዕድሜ ላይ )

1ዱ ጌታቸው

#1ዱ #ግጥምሲጥም #ግጥማዊቅዳሜ
...👓
.
የሚያምር ነገር _ለምን ይሞታል ?
የቀረኝ ስባሪ ልብ ነው
ያጣሁሽ ዓይኔ ተሸፍኖ ሲገለጥ
ባለ ቅፅበት - ባለ ቅጥፈት ነው ።
.............
የቡና ፍቅሬን
የጠላ ፍቅርሽ ያህል ብንዋደድ _ብዬ አሰብኩ
ስንለያይ _ እንደ ውሻ አፍንጫ ቀዘቀዝኩ ።
...
ህመሜ እስከማትወጂ ድረስ የወደድሽ ነገር
ትግሌ ነበር ውስጥ እንደልከትሽ ነበር ።
..
አውቃለሁ ግማሽ ሞት ነው _ መርጦ ማሞገስ
አውቃለሁ ግማሽ ሞት ነዉ _በጋራ መውቀስ
ታውቂያለሽ በጣም ረዥሙ መንገድ _ ወደ ኃላ መመለስ ።.
.
.(ወየው .....
ምኞታችን ከግብ _ ግባችን ከስራ አልገጠመ
በርግጥ መውደቅ _ ሁለተኛ ስማችን ሆኖ ቀጠለ ።
.
#1ዱ (2012)


#አንዱ_ጌታቸው #ባዶ_ሰው_በባዶ_ቤ #ግጥምሲጥም #ጥዑምግጥም2 #ግጥማዊቅዳሜ #gietmsitem #poeticsaturdays #Andu_Getachew #DND #artinaddis
የገጣሚ ነፍስ

የገጣሚ ነፍስ፣
ከእውር መንፈስ ነው ጥሏ፣
ከጽጌሬዳ ውበት ይልቅ - ስለ እሾኋ ሲዘምር።
የገጣሚ ነፍስ፣
ከቆሰለ ቀን ነው ጥሏ፣
የሠይፍን መሳል - ለአፎቱ ሲነግር።
ከመፀው ነፋስ ነው ጥሏ፣
በፀሐይ ብርሃን -
የጧፏን ጸዳል ሲሰርቃት፤
የገጣሚ ነፍስ ከአምላክ ነው ጥሏ፣
‘እውነት እኔ ነኝ።’ ሲላት።

የገጣሚ ነፍስ ከተረበበ ቅጠል ነው ጥሏ፣
‘’ዛፉ ላይ እናምጽ” ብላ፤
ከቆራጭ ስትመክር።
ከቸር መጽዋች ነው ጥሏ፣
ከማግኘት ጽዋ አጎንጭቷት ስጸክር።
. . . . . . .
የገጣሚ ነፍስ ከሁሉ ነው ጥሏ !
ከሁሉ !
. . . . . . . ከ. . . ሁ. . . ሉ. . . !

አንዱ ጌታቸው
ከባዶ ሰው በባዶ

#አንዱ_ጌታቸው #1ዱ #ባዶ_ሰው_በባዶ_ቤት #ጥዑምግጥም2 #ግጥማዊቅዳሜ #gietmsitem #poeticsaturdays #Andu_Getachew #DND #artinaddis
በጦቢያ፣ ሰም እና ወርቅ፣ ግጥማዊ ቅዳሜ እና ሌሎች በርካታ መድረኮች ላይ የምታውቁት ሰይፍሻ የበርካታ ጥዑም ግጥሞች ባለጸጋ ነው።

በብዙዎች እንደሚባለው መጽሐፍ ማሳተም እንደመውለድ ከሆነ ይህ ሰው የ 'ባዶ ሰው በባዶ ቤት' አዋላጅ ሳይሆን አይቀርም። መጽሐፏም ከአርትዖት እስከ መግቢያዋ ከዓይን ያውጣሽ እስከተባለላት ምርቃቷም የ'ርሱ ነች!

#ሰይፈ_ወርቅ #Seifu_Worku #አንዱ_ጌታቸው #1ዱ #ባዶ_ሰው_በባዶ_ቤት #ጥዑምግጥም2 #ግጥማዊቅዳሜ #gietmsitem #poeticsaturdays #Andu_Getachew #DND #artinaddis
የዚህ ወር 'ራስ' Andu Getachew ባዶ ሰው በባዶ ቤት የተሰኘች ግሩም የሥነ-ግጥም ስብስብ አለችው። ግድ የላችሁም አንብቧት በዩቱብና ቴሌግራም በምስልና ድምጽ የተቀናበሩ ግጥሞቹንም እንድትቃኟቸው ተጋብዛችኋል!

https://tttttt.me/AndugetachewDnd

https://www.youtube.com/channel/UCJI2mmHpHddlQJabYGekFEw

ስነ-ግጥም፣ ሙዚቃ፣ የእሳት ዳር ጨዋታዎች፣ ምግብና መጠጥ እንዲሁም ሌሎች መዝናኛዎች አሉን።

https://tttttt.me/seifetemam

በገለጥነው የኛው ቀለም
ጥዑም ግጥም እናጣጥም

የ'ራሱ'ንም የራሳቸውንም ግጥም ሊያቀርቡ እንዲሁም ዝግጅቱን ጠዓም ሊዘሩበት የተዘጋጁት አጣሚያን ደግሞ እኚሁላችሁ !
ሰይፉ ወርቁ፣ ዲበኩሉ ጌታ፣ እቴናት አወል፣ ቴዎድሮስ ወንድማገኝ፣ መንበረማርያም ኃይሉ፣ ፍጹም አበራ፣ ባንቺአየሁ አሰፋ፣ ሰይፈ ተማም፣ ሳምራዊት ውለታው እና ሌሎችም

ትጉንጬ ካፌ እና ሬስቶራንት /Tigunche cafe and Resturant
ካዛንቺስ ኢሲኤ መንገድ ከእፎይ ፒዛ ጀርባ
Kazanchis ECA road behind Efoy Pizza

http://shorturl.at/blAUY

#አንዱ_ጌታቸው #1ዱ #ባዶ_ሰው_በባዶ_ቤት #ጥዑምግጥም2 #ግጥማዊቅዳሜ #gietmsitem #poeticsaturdays #Andu_Getachew #DND #artinaddis #poetry #poetrylovers
ጥበቃ

ሲሰማኝ . . . . .
የጸጉር አንዲት ቅንጣት፣
ከመሬት ስታርፍ የምታሰማው ድምጽ፤
ሲትየኝ. . .
ዐይንን በባዶ ቦታ ላይ ሲተክሉ፣
የሚወርደው ቀለም አልባ ቅርጽ፤
. . . . .
ያድቦለቦልኩት የምራቅ ኳስ፣
ከምላሴ ተነስቶ መሬት ላይ ሲደርስ፤
ፍ . . ዝ . . . ዝ ብዬ ሳይ
መቅረትሽ. . .
ያኔ ነው የገባኝ።

አንዱ ጌታቸው

ከባዶ ሰው በባዶ ቤት

https://tttttt.me/AndugetachewDnd

https://www.youtube.com/channel/UCJI2mmHpHddlQJabYGekFEw


#አንዱ_ጌታቸው #1ዱ #ባዶ_ሰው_በባዶ_ቤት #ጥዑምግጥም2 #ግጥማዊቅዳሜ #gietmsitem #poeticsaturdays #Andu_Getachew #DND #artinaddis #poetry #poetrylovers
ሁለተኛው የ Gitem Sitem - ግጥም ሲጥም ግጥም ሲጥም ፪ አንዱ እና ስራዎቹን እየዘከረች በአጃቢ አጣሚዎቹ ዲበኩሉ ጌታ፣ ሰይፉ ወርቁ፣ እቴናት አወል፣ ወንድማገኝ (የኔ አለም) ፣ ባንቺአየሁ አሰፋ፣ መንበረማርያም ኃይሉ፣ ፍጹም አበራ፣ ሳምራዊት ውለታው እና ሰይፈ ተማም

እንዲሁም ምግባር ሲራጅ፣ ቶማስ አድማሱ፣ ማርቆስ ዘመንበረ ልዑል እና ሌሎችም ጥማና ተጣጥማ አልፋላች።

ትጉንጬ ካፌ እና ሬስቶራንት /Tigunche cafe and Resturant ለመልካም መስተንግዶዋችሁ እና ቤታችንን ስላበጃችሁልን ተመስገኑልን!

https://tttttt.me/seifetemam

የቀጣዩ 'ራስ' ማን እንደሚሆን ገምቱ

#አንዱ_ጌታቸው #1ዱ #ባዶ_ሰው_በባዶ_ቤት #ጥዑምግጥም2 #ግጥማዊቅዳሜ #gietmsitem #poeticsaturdays #Andu_Getachew #DND #artinaddis #poetry #poetrylovers
#አንተ_ማነህ ?
ከመፍራት የሚሻል መፍትሄ
ከመትረፍ የሚዘል ህላዊ
ከመትረፍ የሚገዝፍ ፍፃሜ
ከመንገድ የማይጠም መንገድ
ከሰው መስማሚያ መውደድ
ከአገር የሚገዝፍ ጥበብ
ታስሳለህ ?
አንተ ማነህ ?
_
ፈጥሮ ጨርሶኻል ወይስ ራስህን ትፈጥራለህ ?
አንተ ማነህ?
ልብህ ምን ይልሃል
ሰው ሰበረህ ? አሻገረህ ?
አፈዘዘ አደመቀ ?
በሰው ተሰራህ ወይስ ፈረስክ ?
በረርኩ ስትል አነስክ
አንተ ማነህ ?
ምንድነህ ? ወዴት ነው የምትሄድ ?
_
አንተ ማነህ
ተደሰተ ሲሉህ ምትነደው
ፈፀመ ሲሉህ ምጀምረው
አፈረሰ ሲሉ ምትገነባ
ፈገገ ሲሉህ ምትባባ
አንተ ማነህ ?
_
ንጉስ ነኝ ባልክ ማግስት
በጥበቃ ከበር ሚመልሱህ
ዙፋንህን ወንበር የሚሉት
አንተ ማነህ ?

ደምና ላብህን እንዲያልፍልህ ብት. ገብር
ዜና የምትሆነው ስት ሰበር
አንተ ማነህ ?

መደዴ እየጠሉ
ከመደዴው አንሶ መኖር
ብዙ ዘርቶ እፍኝ መልቀም
በክብ ጥያቄ መታነቅ
እፍኙንም ማስነጠቅ
የምር ማነህ ?
_
ብትኖር ትጠቅማለህ ?
ብትሞት ታጎላለህ ?
እህል ከመጨረስ
አልጋ ከመከስከስ
ፍራሽ ከማድቀቅ
ድንጋይ ከማሞቅ
ራስ ከመውቀስ
ትዘላለህ ?
አንተ ማነህ ?
ምንድነህ ?
_
_
ያስፈራሃል ይህ ሁሉ ጥያቄ
ያነድሃል____ ይህ ዕድሜ
እደርሳለሁ ያልከው እንኳ ልትደርስ
መታጠፊያው ራሱ የጠፋህ
አንተ



?
_
_
ግንድ ነኝ ብለህ ስትወጣ
____ሲቲክኒ አከልክ ?
የሰፈር ምላስ መሞረጃ
ጥርስ መጎርጎሪያ ሆንክ ?

ማነው የፈጠረህ
ለምን ነው የገጠመ ታውቀዋለህ ?
ምን ያነድሃል ?
ምን ያፈዝሃል
ምን ያቀዝሃል
ምን ያስሮጥሃል .
_
_
ህልም ምንድነው ? ልብ እያፈሰሰ
ሰላም ምንድነው ? ሩቅ ካላስኬደ
ደም ካፋሰሰ ' ጠላት ' ካስለቀሰ

መንገድ ምንድነው ? ወረት ።
ተጓዥ እያዩ መቅረት
ከራስ መራቅ
ከሰው ለመድረስ
"የሆነ ሰው ለመሆን ' ያልሆነውን ማሰስ ?




ማነህ ?
__
በቸከ ቀን
በቸከ ህይወት
ወረቀት የሚያሰኝህ
መፅሐፍ የሚያስገልጥህ
ውስኪ እንደመቅመስ
ሴት ከንፈር እንደመንከስ
ወገብ እንደመጨረስ
በቸከ ህመም
በቸከ ወረቀት የሚያስቸከችክህ
አንተ ማነህ ?
_
የእሳት ግለት
የበረዶ ብርደት
የፍጥረታት መሞት መራባት
መባላት
የእግዜር ዝም ማለት
የሚያስጨንቅህ ?
አንተ ማነህ
ምንድነህ
ወዴት ነው የምትሄደው ?

#1ዱ
©️አንዱ ጌታቸው