ግጥም ሲጥም - Gitem Sitem
1.84K subscribers
842 photos
55 videos
20 files
394 links
የዘመናችንን ቀለም ያሳያሉ ያልናቸውን የዚህ ትውልድ የስነ ግጥም ውጤቶችን እንጋራ - እናጋራ።
ለማካፈል የፈለጋችሁትን በGitem_Sitem ፣ gitemsitem@gmail.com የጸሃፊ ስም እና ርዕስ አክላችሁ ላኩልን።

We are all about sharing this generation's poetry. Please email us your pieces gitemsitem@gmail.com
Download Telegram
#አንተ_ማነህ ?
ከመፍራት የሚሻል መፍትሄ
ከመትረፍ የሚዘል ህላዊ
ከመትረፍ የሚገዝፍ ፍፃሜ
ከመንገድ የማይጠም መንገድ
ከሰው መስማሚያ መውደድ
ከአገር የሚገዝፍ ጥበብ
ታስሳለህ ?
አንተ ማነህ ?
_
ፈጥሮ ጨርሶኻል ወይስ ራስህን ትፈጥራለህ ?
አንተ ማነህ?
ልብህ ምን ይልሃል
ሰው ሰበረህ ? አሻገረህ ?
አፈዘዘ አደመቀ ?
በሰው ተሰራህ ወይስ ፈረስክ ?
በረርኩ ስትል አነስክ
አንተ ማነህ ?
ምንድነህ ? ወዴት ነው የምትሄድ ?
_
አንተ ማነህ
ተደሰተ ሲሉህ ምትነደው
ፈፀመ ሲሉህ ምጀምረው
አፈረሰ ሲሉ ምትገነባ
ፈገገ ሲሉህ ምትባባ
አንተ ማነህ ?
_
ንጉስ ነኝ ባልክ ማግስት
በጥበቃ ከበር ሚመልሱህ
ዙፋንህን ወንበር የሚሉት
አንተ ማነህ ?

ደምና ላብህን እንዲያልፍልህ ብት. ገብር
ዜና የምትሆነው ስት ሰበር
አንተ ማነህ ?

መደዴ እየጠሉ
ከመደዴው አንሶ መኖር
ብዙ ዘርቶ እፍኝ መልቀም
በክብ ጥያቄ መታነቅ
እፍኙንም ማስነጠቅ
የምር ማነህ ?
_
ብትኖር ትጠቅማለህ ?
ብትሞት ታጎላለህ ?
እህል ከመጨረስ
አልጋ ከመከስከስ
ፍራሽ ከማድቀቅ
ድንጋይ ከማሞቅ
ራስ ከመውቀስ
ትዘላለህ ?
አንተ ማነህ ?
ምንድነህ ?
_
_
ያስፈራሃል ይህ ሁሉ ጥያቄ
ያነድሃል____ ይህ ዕድሜ
እደርሳለሁ ያልከው እንኳ ልትደርስ
መታጠፊያው ራሱ የጠፋህ
አንተ



?
_
_
ግንድ ነኝ ብለህ ስትወጣ
____ሲቲክኒ አከልክ ?
የሰፈር ምላስ መሞረጃ
ጥርስ መጎርጎሪያ ሆንክ ?

ማነው የፈጠረህ
ለምን ነው የገጠመ ታውቀዋለህ ?
ምን ያነድሃል ?
ምን ያፈዝሃል
ምን ያቀዝሃል
ምን ያስሮጥሃል .
_
_
ህልም ምንድነው ? ልብ እያፈሰሰ
ሰላም ምንድነው ? ሩቅ ካላስኬደ
ደም ካፋሰሰ ' ጠላት ' ካስለቀሰ

መንገድ ምንድነው ? ወረት ።
ተጓዥ እያዩ መቅረት
ከራስ መራቅ
ከሰው ለመድረስ
"የሆነ ሰው ለመሆን ' ያልሆነውን ማሰስ ?




ማነህ ?
__
በቸከ ቀን
በቸከ ህይወት
ወረቀት የሚያሰኝህ
መፅሐፍ የሚያስገልጥህ
ውስኪ እንደመቅመስ
ሴት ከንፈር እንደመንከስ
ወገብ እንደመጨረስ
በቸከ ህመም
በቸከ ወረቀት የሚያስቸከችክህ
አንተ ማነህ ?
_
የእሳት ግለት
የበረዶ ብርደት
የፍጥረታት መሞት መራባት
መባላት
የእግዜር ዝም ማለት
የሚያስጨንቅህ ?
አንተ ማነህ
ምንድነህ
ወዴት ነው የምትሄደው ?

#1ዱ
©️አንዱ ጌታቸው