ግጥም ሲጥም - Gitem Sitem
1.85K subscribers
842 photos
55 videos
20 files
394 links
የዘመናችንን ቀለም ያሳያሉ ያልናቸውን የዚህ ትውልድ የስነ ግጥም ውጤቶችን እንጋራ - እናጋራ።
ለማካፈል የፈለጋችሁትን በGitem_Sitem ፣ gitemsitem@gmail.com የጸሃፊ ስም እና ርዕስ አክላችሁ ላኩልን።

We are all about sharing this generation's poetry. Please email us your pieces gitemsitem@gmail.com
Download Telegram
የኔ ክረምት

የከረረን ጽልመት
በምናቤ ሳክም
በከረረ ክረምት
በነጠላ ሳዘግም
ጽልመቱም አልነጋ ክረምቱም አልባተ
ልቤን ከገላዬ መለየት አቃተ

@seifetemam
#seifetemam
👍1
አንዷ መንገድ

አንዲት መስመርብቻ
በዓይኔ ፊት አለች
ደሞም ከሷ ውጪ
ችክችክ እና ድልዝ
ለንባብ አይመች
ይቺ ደማቅ መስመር
ይቺ ደማቅ መንገድ
እራሷን ዘርግታ
ወደራሷ ምትወስድ
እራሷን አንድዳ
ነድዳ ‘ምትማገድ
ይኧው ከሷ ውጪ
ቅዠት ነው ድንብርብር
ሰልፍ የሳተ ጉንዳን
የማይቀድስ ደብር
ጭስ የሌለው እጣን
የሚያሳስቅ ቀብር
የሚታለም እውን
የሚላፋ ነብር

እውነትን ፈለኳት
እንኋት ደማምቃ
አየኋት ሳልለፋ
በመስመሯ መጥቃ
በጉልህ ተጽፋ

ማተርኩ ወደ ፍቅር
ትታያለች ዘልጋ
ክረምቱንም በጋ
ሌሊቱን ቀን አርጋ
መስመሯን አፍቅራ
ፍቅር መስመር ፈጥራ

ባ’ለም ካለው ሁሉ
በጎውን ተመኘው
በአንድነት አንድ ሁኖ
አንዲት መስመር ላይ ነው
ከዛች መስመር ውጭ
ሁሉ ችክችክ ሁሉ ድልዝ
ለንባብ አይመች
እውን አልባ ውጥንቅጥ
የ’ልም አለም አደንዛዥ
ያለ መስሎ ሚያጥጥ
ሰው በቁም ‘ሚያስቃዥ
ያባይ ስጋ ቅጥቅጥ
የበረሃ ሚራዥ
2008
@seifetemam #seifetemam