ግጥም ሲጥም - Gitem Sitem
1.84K subscribers
842 photos
55 videos
20 files
394 links
የዘመናችንን ቀለም ያሳያሉ ያልናቸውን የዚህ ትውልድ የስነ ግጥም ውጤቶችን እንጋራ - እናጋራ።
ለማካፈል የፈለጋችሁትን በGitem_Sitem ፣ gitemsitem@gmail.com የጸሃፊ ስም እና ርዕስ አክላችሁ ላኩልን።

We are all about sharing this generation's poetry. Please email us your pieces gitemsitem@gmail.com
Download Telegram
Forwarded from Poetic Saturdays
ሁለተኛው የአፍሪካ የግጥም ግጥሚያ የመጀመሪያ ዙር ከሰኞ ሐምሌ 12 እስከ ቅዳሜ ሐምሌ 17 ድረስ በኦንላይን ይካሔዳል።

ሀገራችንም በድንቅ ልጃችን "ሰይፈ ተማም" ትወከላለች!

#CASP #CupOfAfricanSlamPoetry #CASP2021 #CASPEthiopia
Forwarded from Poetic Saturdays
የመክፈቻው ቀን ደስ በሚል ሁኔታ ተጠናቅቋል፡፡

የ33 የአፍሪካ ሀገራት ሻምፒዮኖች ይሳተፉበታል፡፡

ከነገ ጀምሮ የሚጀምረው ውድድር ቅደም ተከተል ምድብም ዕጣ ወጥቶ ነበር፡፡

ሻምፒዮናችን Seife Temam 9 ሀገራት ባሉበት የመጨረሻው ቀን ምድብ የደረሰው ሲሆን የመጀመሪያ ውድድሩን አርብ ዕለት ያደርጋል፡፡

ደቡብ ሱዳን ፣ ሞሮኮ ፣ ሞዛምቢክ ፣ ኬፕቬርድ ፣ ማዳጋስካር ፣ ማላዊ ፣ ኒጀር እና ቡሩንዲ በዚህ ምድብ ይገኛሉ፡፡

ቻድ ላይ በተደረገው የመጀመሪያው ውድድር ላይ አሸናፊ ሻምፒዮን የነበረው እና በሞት ያጣነው ሴኔጋላዊው አልፋሩቅ ም ታስቦ ነበር፡፡
________
ውድድሩ ነገ ከምሽቱ 2፡00 ሰዓት ላይ ይጀምራል፡፡ በፌስቡክ ቀጥታ በመግባት እንድትከታተሉን እንጋብዛለን፡፡

በአካል መገኘት የምንችል ደግሞ ቀጥታ ስርጭታችንን ከሽፍታ ነውና የምናደርገው ብቅ ብላችሁ ደመቅ ደመቅ እናድርገው!

Coupe d'Afrique de Slam poésie, CASP Gitem Sitem - ግጥም ሲጥም #casp2021 #CaspEthiopia #slampoetry #Africa #Ethiopia
Forwarded from Poetic Saturdays
የ ሁለተኛው የአፍሪካ የግጥም ግጥሚያ በሁለተኛ ቀን ምሽቱ በመጀመሪያ ምድብ የሚገኙ ሀገራት ተወካዮች ተፋልመውበት ተጠናቅቋል፡፡
በውጤቱም
Diaw Fall - ከ ሞሪታኒያ 🇲🇷- በ 70.2 ነጥብ 1ኛ ደረጃ
DJ Huba - ከ አንጎላ🇦🇴 - በ 64.5 ነጥብ 2ኛ ደረጃ
Bokon - ከ ቶጎ 🇹🇬 - በ 63 ነጥብ - 3ኛ ደረጃ
Aladin - ከ ጋቦን 🇬🇦- በ61 ነጥብ (ከ80) 4ኛ ደረጃ ን

በማግኘት ቅዳሜ ለሚደረገው ሁለተኛ ዙር ግጥሚያ ያለፉ የመጀመሪያዎቹ 4 ተወዳዳሪዎች መሆናቸውን አረጋግጠዋል፡፡
----------------
ነገ ማክሰኞ ሐምሌ 13 በተመሳሳይ ሰዓት (ማታ 2፡00) በሚቀጥለው ውድድር የመጀመሪያው ዙር ሁለተኛ ምድብ ሀገራት ተወካዮች ይፋለማሉ፡፡

በዚህ ምድብ ናይጄሪያ ፣ ቻድ ፣ ሞሪሺየስ ፣ ኬንያ ፣ ሴኔጋል ፣ ካሜሩን ፣ ጋና እና ጊኒ ቢሳው ይገኛሉ፡፡ እነዚህ ሀገራት ያላቸውን ረጅም የግጥም ግጥሚያ ልምድ እና ባህል (poetry slam culture) ስናይ … ነገ ጠንከር ያለ ውድድር የሚታይበት ምሽት እንደሚሆን እንጠብቃለን!

በፌስቡክ ቀጥታ በመግባት ውድድሩን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን!
#casp2021 #CaspEthiopia #slampoetry #Africa #Ethiopia Coupe d'Afrique de Slam poésie, CASP
Forwarded from Poetic Saturdays
በሁለተኛው የአፍሪካ የግጥም ግጥሚያ ኢትዮጵያ የምትገኝበት የመጀመሪያው ዙር የመጨረሻ ምድብ ግጥሚያ ዓርብ ሐምሌ 16 ቀን 2013 ከምሽቱ 130 ጀምሮ መተላለፍ ይጀምራል፡፡

በሽፍታ ሬስቶራንት ሰብሰብ ብለን ሻምፒዮናችን ሰይፈ ተማምን በመጀመሪያ የውድድር ተሳትፎው እንደግፈው!

The final group of the first round matches of the second edition of the African Cup of slam poetry happens on Friday, July 23, 2013 at 1:30pm.

Join us at Shifta Restaurant for a watch party, as our champion Seife Temam performs his first performance of the competition.

#CASP2021 #CASPEthiopia #SlamPoetry #Africa #Ethiopia
Forwarded from Poetic Saturdays
የሁለተኛው የአፍሪካ የግጥም ግጥሚያ ሁለተኛ ዙር ውድድር ቅዳሜ ሐምሌ 17 ቀን 2013 ዓ.ም ከ 9፡00 ጀምሮ በኦንላይን ይካሄዳል፡፡

በመጀመሪያው ዙር ከየምድቦቻቸው ያሸነፉ አራት ሀገራት … በአጠቃላይ 16 ሀገራት በዚህ ዙር ይፋለማሉ!

እስታሁን 12 ሀገራትን ለይተን አውቀናል፡፡ ቀሪዎቹን አራት ሀገራት (ኢትዮጵያ ከምትወዳደርበት ምድብ) ዓርብ ላይ እናውቃለን፡፡

በ GUAC-ON ሬስቶራንት ደመቅ አድርገን እንጠብቃችኋለን! ብቅ ብቅ በሉና አበረን እንከታተል፡

The second round of the African Cup of Slam Poetry Competition will be held online on Saturday, July 24, 2013 starting at 3፡00 pm.

Four countries from each group on the first round, 16 countries will battle in this second round!

So far, we have 12 countries secured their spot on this round. The remaining four will be identified on Friday at the final group of the first rounds.

Join us at GUAC-ON for a viewing party and closing celebration of the virtual rounds of the second edition of the African Cup of Slam Poetry!

#CASP2021 #CASPEthiopia #SlamPoetry #Africa #Ethiopia