#የኢትዮጵያ_ወንጌል_አማኞች_አብያተክርስቲያናት_ካውንስል ጽ/ቤ ሃላፊ መጋቢ ጌትነትለማ #በአረንጉዴ_አሻራ_ዙሪያ ከካውንስሉ ክላስተር አመራሮች ጋር በዋናው ጽ/ቤ ተወያዩ፡፡
የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካውንስል ጽ/ቤ ሃላፊ መጋቢ ጌትነት ለማ ሃምሌ 6 ቀን 2015 ዓ/ም በአረንጉዴ አሻራ ዙሪያ ከካወንስሉ ክላስተር አመራሮች ጋር ሰኞ ሃምሌ 10 ቀን 2015 ዓ/ም 500ሚልዮን ችግኝ በአንድ ጀንበር በሃገር አቀፍ ደረጃ እንደሚተከል በታቀደው እቅድ መሰረት የክላስተር አመራሮች እና አባል ቤተ-እምነቶች በጉለሌ ህጽዋት ማእከል ተገኝተው አረንጓዴ አሻራቸውን ለማኖር እና የወንጌል አማኞች በዚሁ የሃገራዊ ጉዳይ ላይ መሳትፍ እንደሚገባቸው ተወያይተው መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
የካውንስሉ ጽ/ቤ ሃላፊ መጋቢ ጌትነት ለማ ችግኝ የምንተክለው የሃይማኖት ተቋማት ስለሆንን ብቻ ሳይሆን እንደ ዜጋ ለትውልድ የሚጠቅም ስራን መስራት ስለሚገባ ችግኝ መትከል ስላለብን እንተክላለን ብለዋል፡፡ በክላስተሩ የተዋቀሩ የወንጌል አማኞች በሙሉ በአረንጉዴ አሻራ መርሃ ግብር ሊሳተፋ እንደሚገባቸው መጋቢ ጌትነት ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል፡፡
በስብሰባው የተገኙ ከአዲስ አበባ እና ከሸገር ከተማ የመጡ የክላስተር አመራሮች ከመንፈሳዊ አገላግሎት ባሻገር በሃገራዊ ጉዳይ ላይ ቀዳሚ ተሰላፊ መሆናቸውን ገልጸው የወንጌል አማኞች በዚህ ሃግራዊ ጉዳይ ላይ እንዲሳተፋ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል፡፡
ከአዲስ አበባ ሐይማኖት ተቋማት ጉባኤ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ዩሃንስ ግርማ እንደገለጸው ሐምሌ 10 ቀን ለሚከናወነው አረንጉዴ አሻራ ቀን በጉለሌ የህጽዋት ማእከል ከሁሉም ሃይማኖት ተቀማት እንደሚሳተፉ ገልጾ በእለለቱ ከ4000 የሃይማኖት አባቶች 12000 ችግኝ ይተከላል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተናግሯል፡፡